የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች የስነ-ስርዓት ሂደቶች ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡- ባለፈው ሶስት ዓመት ተኩል የፌደራል ፍርድ ቤቶች በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በተገቢው ደረጃ ለማከናወን በርካታ የለውጥ ተግባራትን ሲያከናውኑ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ የለውጥ እርምጃዎች ትኩረት ያደረጉት በተቋማዊ እና በግለሰብ ዳኞች ደረጃ የፍርድ ቤቱን ነጻነት እና ገለልተኝነት ማስከበር ነው፡፡ በተጓዳኝም ለተጠያቂነት ተቋማዊ ስርዓቶች ተዘርግተዋል፡፡ በፍ/ቤቱ አመራሮች እና ዳኞች በኩል ሲደረግ የነበረው ጥረት ዋናው ግብ የሚሰጠው የዳኝነት ዘርፍ ቀልጣፋ፣ ተገማች እና ተደራሽ በማድረግ በፍርድ ቤቱ አገልግሎት ላይ የሕዝብ አመኔታ እንዲጨምር ነው፡፡ በዚህ ወር መጨረሻ በሚዘጋጀው “የፍርድ … [Read more...] about የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች ላይ መግለጫ ሰጠ
Law
የሕግ ያለህ
የወንጀል ክስ ማንሳት እና ማስቀጠል የሚቻለዉ መቼ ነዉ?
የክስ ማንሳት የፍሬ ነገር ይዘትና ስነ ሥርዓት በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 122 ስር በአምስት ንዑስ አንቀጾች ተጠቃሎ ይገኛል፡፡ በይዘቱም፡- • ከከባድ የሰው ግድያ እና ከከባድ ውንብድና ወንጀሎች ውጭ ዐ/ሕግ ከፍርድ በፊት ክስ ማንሳት ይችላል፡፡ • ክስ የሚነሳው በዐ/ህጉ ጥያቄ ወይም በሌላ የመንግስት አካል ትዕዛዝ ሊሆን ይችላል፡፡ • ክሱ የሚነሳው በፍ/ቤት ፈቃድ ሲሆን ፍ/ቤቱ ለመከልከልም ሆነ በመፍቀድ ምክንያቱን ማስቀመጥ አለበት፡፡ • በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 113 መሰረት አዲስ ክስ ካልቀረበ ተከሳሹ ለግዜው ይለቀቃል፡፡ • የክሱ መነሳት ዐ/ሕግ ክስን ከማንቀሳቀስ አያግደውም፡፡ የሚል ሀሳብ ያለው ነው፡፡ የፍትሕና የሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲቲዩት ባዘጋጀው ረቂቅ የወንጀል ስነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 119 ስር ዐ/ሕግ ከፍርድ ቤት በማንኛውም ጊዜ ክስ … [Read more...] about የወንጀል ክስ ማንሳት እና ማስቀጠል የሚቻለዉ መቼ ነዉ?
በማር በበርበሬ በጤፍና በቅቤ ምርት ላይ ለጤና ጠንቅ የሆኑ ባዕድ ነገሮች የቀላቀሉ ተያዙ
በደቡብ ክልል በማር፣ በበርበሬ፣ በጤፍና በቅቤ ምርት ላይ ለጤና ጠንቅ የሆኑ ባዕድ ነገሮች ተቀላቅሎ ሲዘጋጅ መያዙን የደቡብ ክልል ንግድ ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ ከፋ ዞን፣ ቦንጋ ፣ጌዴኦ ዞን ፣ዲላና ሀላባ ዞን ቁሊቶ ከተሞች ላይ ባደረገው የዳሰሳ ጥናት በማር ፤በበርበሬ በጤፍና በቅቤ ምርቶች ላይ ለጤና ጠንቅ የሆኑ ባዕድ ነገሮች ተቀላቅሎ ሲዘጋጅ መያዙን የደቡብ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሽመልስ ዋንጎሬ ተናግረዋል። የጥራት ደረጃቸውን ያልጠበቁ የምግብ ምርቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱና እየተላመዱ መምጣታቸውን በተደረገው የዳሰሳ ጥናት መረዳት ችለናል ያሉት ኃላፊው ህብረተሰቡ ምግብና ምግብ ነክ የሆኑ ነገሮችን ሲሸምት አጢኖ ሊሆን እደሚገባም አሳስበዋል። ፎሼ የተሰኘ የጥራት … [Read more...] about በማር በበርበሬ በጤፍና በቅቤ ምርት ላይ ለጤና ጠንቅ የሆኑ ባዕድ ነገሮች የቀላቀሉ ተያዙ
መስከረም 24 አዲስ መንግሥት ይመሠረታል፤ የቋሚ ኮሚቴ አባላት ከ7 እስከ 13 ሆኖ ይደራጃል
በአዲሱ መንግሥት ምስረታ ውስጥ የቋሚ ኮሚቴ አባላት ከ7 እስከ 13 ሆኖ የሚደራጅ ሲሆን አባላቱም እንደየ ሙያቸው ዘርፎችን እንዲከታተሉ የሚደረግ መሆኑን አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ገለጹ።የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ለመንግሥት ምስረታው እየተደረገ ያለውን ዝግጅት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ የመንግሥት ምስረታ የሚካሄድ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ገልጸዋል። አፈ-ጉባዔው በሕገ መንግስቱ መሰረት መስከረም መጨረሻ ባለው ሰኞ የመንግስት ምስረታው ይካሄዳል ብለዋል። የሕግ አወጣጥ ሂደቱን አስመልክቶ የተካሄደውን ጥናት መነሻ በማድረግ የሕግ አወጣጡን የሚያዘምን መመርያ ተዘጋጅቷል ብለዋል። ምክር ቤቱ የክትትልና ቁጥጥር ስርዓቱን ማዘመን የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ተዘርግቷል ያሉት … [Read more...] about መስከረም 24 አዲስ መንግሥት ይመሠረታል፤ የቋሚ ኮሚቴ አባላት ከ7 እስከ 13 ሆኖ ይደራጃል
በመከላከያ ውስጥ ለትህነግ ሲሰልሉ የነበሩ ጽኑ እስራት ቅጣት ተላለፈባቸው
ከትህነግ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ባላቸው የሰራዊት አባላት ላይ ከ8 ዓመት እስከ 18 ዓመት የሚደርስ የፅኑ እስራት ውሳኔ ተላለፈ። የደቡብ ዕዝ ቀዳማዊ ወታደራዊ ፍርድ ቤት በተለያዩ ወንጀሎች ተሳትፎ በነበራችውና ከትህነግ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ባላቸው የሰራዊት አባላት ላይ ከ8 ዓመት እስከ 18 ዓመት በሚደርስ የፅኑ እስራት ውሳኔ ማስተላለፉ ተገለፀ። ነሐሴ 20 ቀን 2013 ዓ.ም በዕዙ ጠቅላይ መምሪያ በዋለው ችሎት የተሰየመው የዳኞች ምድብ 8 የክስ መዝገቦችን መርምሮ ነው ውሳኔ የሰጠው። በዚህ መሰረት፣ በ1ኛ መዝገብ እነ ኮሎኔል ካህሱ ሀብቱ ፀልይ፣ ኮሎኔል ሀጎስ አሰፋ ወልደንጉሴ እና ሌተናል ኮሎኔል ሀይላይ ገብሩ ገብረተክላይ በ2ኛ መዝገብ ሻምበል ባሻ ክፍሌ ፍስሃ በ3ኛ መዝገብ ኮሎኔል ክፍሌ ፍስሃ በ4ኛ መዝገብ ሃምሳ አለቃ … [Read more...] about በመከላከያ ውስጥ ለትህነግ ሲሰልሉ የነበሩ ጽኑ እስራት ቅጣት ተላለፈባቸው
ከትህነግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ 1,642 ሰዎች ተያዙ
በ1,616 የንግድ ድርጅቶች ላይ ዕርምጃ መወሰዱን ፖሊስ አስታውቋል ከአሸባሪው ትህነግ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 1,642 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ዘላለም መንግሥቴ እንደገለጹት፣ ከትህነግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ ሰዎችን በማደን በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ እየተደረጉ ናቸው። እስካሁን ድረስ በተካሄደው የተቀናጀ ምርመራ ከትህነግ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 1,642 ሰዎች፣ በተለያዩ አካባቢዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ አስታውቀዋል። ከተጠረጠሩት ሰዎች በተጨማሪ ለትህነግ ቡድን ሕገወጥ ተልዕኮ መጠቀሚያ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ የንግድ ድርጅቶች ተዘግተው ምርምራ በመካሄድ ላይ እንደሆነ … [Read more...] about ከትህነግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ 1,642 ሰዎች ተያዙ
በሕገ-ወጡ ብረት ለገበያ እንዲቀርብ ተወሰነ፤ 400 ኩንታል ሲሚንቶና የቴሌ ኬብሎችን ሲያጓጉዙ የነበሩ ተያዙ
በተለያዩ ቦታዎች በሕገ-ወጦች አማካኝነት ተከማችቶ የተገኘ ብረት በሕጋዊ መንገድ ወደ ገበያ ገብቶ እንዲሸጥ እና ለመንግሥት ገቢ እንዲሆን መወሰኑን ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። በ13 የተለያዩ ቦታዎች በህገ-ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘውና በዋጋ አረጋጊ ግብረ-ሀይል በቁጥጥር ስር የዋለው ከ1ሺ በላይ መኪና ብረት በህጋዊ የግብይት ስርዓቱ ውስጥ ገብቶ እንዲሸጥና ገቢው ለመንግስት እንዲገባ መወሰኑን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። በሌላ በኩል በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ሲሚንቶ እና የቴሌ ጥቅል ኬብል በመኪና ሲያጓጉዙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የክፍለ ከተማው የህዝብ ግንኙነት ቢሮ አስታውቋል። ተጠርጣሪዎቹ ትናንት ምሽት በወረዳው አደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ ጨለማን ተገን በማድረግ 400 ኩንታል ሲሚንቶ … [Read more...] about በሕገ-ወጡ ብረት ለገበያ እንዲቀርብ ተወሰነ፤ 400 ኩንታል ሲሚንቶና የቴሌ ኬብሎችን ሲያጓጉዙ የነበሩ ተያዙ
ወደ ኮምቦልቻ ሊገባ የነበረ 49 ሺህ 300 የአሜሪካ ዶላር ተያዘ
በኮምቦልቻ ከተማ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኬላ ኮድ3 የሰሌዳ ቁጥር 89654 የሆነ መኪና መነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ ወደ ኮምቦልቻ ሊገባ ሲል በብሔራዊ ደኅንነት፣ በፓሊስ እና ኬላ በሚጠብቁ ወጣቶች ትብብር በቁጥጥር ሥር መዋሉን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ገልጿል። የጽ/ቤቱ የታክቲክና ወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር አሊ ለአሚኮ እንደገለፁት ተጠርጣሪው ከምሽቱ 2:40 ሰዓት ላይ አሽከርካሪ በኬላው ላይ በነበረ ፍተሻ ከነዶላሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ወጣቶች በኬላ ፍተሻ እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ መሆኑን የገለጹት ኮማንደር አሊ ወጣቶች እየሠሩ ያሉትን አካባቢን በንቃት የመከታተል ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። በኬላ ጥበቃ ላይ አሚኮ ያነጋገረው በጎ ፈቃደኛ ወጣት ሐሰን እንድሪስ አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን ለመቅበር በግንባር … [Read more...] about ወደ ኮምቦልቻ ሊገባ የነበረ 49 ሺህ 300 የአሜሪካ ዶላር ተያዘ
በባሌ ዞን የአሸባሪው ሸኔ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ
በባሌ ዞን ሐረና ቡሉቅ ወረዳ ሦስት የአሸባሪው ሸኔ አባላት በኅብረተሰቡ ተሳትፎ እና በፀጥታ አካላት የተቀናጀ ሥራ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና በሕዝቡ ላይ በመተኮስ ጉዳት ለማድረስ በሞከሩ ሁለቱ ላይ ደግሞ እርምጃ መወሰዱን የባሌ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። የአሸባሪው ሸኔ አባላት በተደጋጋሚ ወደ ዞኑ ለመግባት ሙከራ ሲያደርጉ መቆየታቸውን የባሌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዳይሬክተር ኮማንደር ጄይላን አሚን ተናግረዋል። በቁጥጥር ስር የዋሉት የሽብር ቡድኑ አባላት፣ “የኦሮሞን ሕዝብ ትክክለኛ ፍላጎት እንዳልተረዳን ያወቅነው ሕዝቡ በአንድነት ወጥቶ ቁጥጥር ስር ሲያውለን ነው” ብለዋል። “ሌሎች የተቀሩት ወጣቶችም ይህንኑ ሐቅ ሊረዱ ይገባል” ሲሉ መናገራቸውን ኦቢኤን ዘግቧል። የሐረና ቡሉቅ ወረዳ ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ የኦሮሞን ሕዝብ ለ27 ዓመታት ሲገድል፣ ሲያኮላሽ እና … [Read more...] about በባሌ ዞን የአሸባሪው ሸኔ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ
ትህነግ በሰሜን ወሎ የፈጸመው ጭፍጨፋ የሳተላይት መረጃ
ከሰሞኑን በእንግሊዙ የቴሌግራፍ ጋዜጣ የወጣው የምርመራ ሪፖርት መነጋገሪያ ሆኗል። ሪፖርቱ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ አከባቢ አጋምሳ ተብላ የምትጠራ ከአፋር ክልል የጥቂት ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ መንደር ሙሉ በሙሉ መውደሙን በሳተላይት ምስል በታገዘ ሁኔታ ቀርቧል። ሪፖርቱን ያዘጋጀው ጋዜጠኛ ዘካሪያስ ዘላለም፥ በተደረገው የምርመራ ስራና ከአከባቢው ወደ ደሴ የተፈናቀሉት ንጹሃኖች በማነጋገር የጦር ወንጀል የተፈጸመው በአከባቢው ይንቀሳቀሱ የነበሩት የ "ትግራይ ሃይሎች" መሆኑን ደርሰንበታል ብሏል። በተጠቃው አከባቢ ላይ አብዛኛው ነዋሪ በግብርና ስራ የሚተዳደሩ ሲሆኑ ከሳተላይት ምስሎችን በመመልከት ከ50 በላይ ጎጆ ቤቶች መቃጠላቸውንና ቃጠሎዉ ከሃምሌ 26 እለት ጀምሮ መፈጸሙንም ማረጋገጥ መቻሉን የጋዜጣው ሪፖርት ያስረዳል። ጋዜጠኛው፥ የሳተላይት ምስል … [Read more...] about ትህነግ በሰሜን ወሎ የፈጸመው ጭፍጨፋ የሳተላይት መረጃ