• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የወንጀል ክስ ማንሳት እና ማስቀጠል የሚቻለዉ መቼ ነዉ?

January 12, 2022 09:27 am by Editor Leave a Comment

የክስ ማንሳት የፍሬ ነገር ይዘትና ስነ ሥርዓት በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 122 ስር በአምስት ንዑስ አንቀጾች ተጠቃሎ ይገኛል፡፡ በይዘቱም፡-

• ከከባድ የሰው ግድያ እና ከከባድ ውንብድና ወንጀሎች ውጭ ዐ/ሕግ ከፍርድ በፊት ክስ ማንሳት ይችላል፡፡

• ክስ የሚነሳው በዐ/ህጉ ጥያቄ ወይም በሌላ የመንግስት አካል ትዕዛዝ ሊሆን ይችላል፡፡

• ክሱ የሚነሳው በፍ/ቤት ፈቃድ ሲሆን ፍ/ቤቱ ለመከልከልም ሆነ በመፍቀድ ምክንያቱን ማስቀመጥ አለበት፡፡

• በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 113 መሰረት አዲስ ክስ ካልቀረበ ተከሳሹ ለግዜው ይለቀቃል፡፡

• የክሱ መነሳት ዐ/ሕግ ክስን ከማንቀሳቀስ አያግደውም፡፡

የሚል ሀሳብ ያለው ነው፡፡

የፍትሕና የሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲቲዩት ባዘጋጀው ረቂቅ የወንጀል ስነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 119 ስር ዐ/ሕግ ከፍርድ ቤት በማንኛውም ጊዜ ክስ ማንሳት የሚችል መሆኑን በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 122 ስር የተመለከተው የፍርድ ቤት ፈቃድና በተወሰኑ የወንጀል ክሶች ላይ የተደረገው ክልከላ ተነስቷል፡፡ አብሮ በተዘጋጀው የህጉ ሀተታ ዘምክንያትም ጉዳዩን ዐ/ሕግ ካልተከታተለው በውጤት ደረጃ ልዩነት የሌለው በመሆኑ በተወሰኑ ወንጀሎች የተደረገው ክልከላ እና የፍ/ቤት ፈቃድ መጠየቅ አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም በሚል አስፍሯል፡፡

የኢ.ፌ.ድሪ. አስፈጻሚ አካላትን ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁ. 691/2003 የፍትሕ ሚኒስቴርን ስልጣንና ተግባር በዘረዝረው አንቀጽ 16 ስር በንዑስ አንቀጽ 6 “… በቂ ምክንያት ሲኖር በህጉ መሰረት ክሱን ያነሳል…” በሚል ያስቀምጣል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ዐ/ሕግ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ. 947/2008 ክስ ማንሳትን አስመልክቶ “… የፌደራል ጠ/ዐ/ሕግ ለህዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ጠ/ሚንስትሩን በማማከር ክስ ያነሳል፡፡ የተነሳም ክስ እንዲቀጥል ያደርጋል፡፡” የሚል ድንጋጌ አካቷል፡፡ የፍትሕ ሚኒስቴር በ2003 ባዘጋጀው የኢትየጲያ የወንጀል ፖሊሲ ላይ በገጽ 37 ክስ ማንሳትን አስመልክቶ “… ዐ/ሕግ የመሰረተውን የወንጀል ክስ ክርክር መቀጠል የህዝብና የመንግስት ጥቅምን አያስጠብቅም ብሎ ካመነ ለፍ/ቤቱ በማስታወቅ ክስን ማቋረጥ ይችላል፡፡ … በዐ/ሕግ ጥያቄ የተነሳ ክስ ለህዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የተቋረጠውን የክስ ሂደት የሚቀጥል መሆኑ…” በሚል አስቀምጧል፡፡

ከላይ የተመለከቱት ህጎች በጥቅሉ ክስ ማንሳት በመቀጠል ላይ ያለ የክርክር ሂደት ለሰፊና ለተሻለ ጥቅም ሊቋረጥ የሚችልበት ሥርዓት መሆኑን ያመለክታሉ፡፡ በአንዳንድ የሕግ ስርኣቶች የወንጀል ክስ ለማስጀመር የግድ የጽሁፍ አቤቱታ መቅረብ ያለበት እንደመሆኑ መጠን (Accusatory principle) በፍ/ቤት ተቀባይነት አግኝቶ የተጀመረን ክርክር ዐ/ሕግ ማንሳት አይችልም፡፡ (Principle of immutability) በሌሎች የሕግ ስርዓቶች ክስን ለማንሳት አሳማኝ የሆነ ምክንያት በማቅረብ በፍ/ቤት ፈቃድ (Up on the consent of the court) ሊፈጸም ይችላል፡፡ የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 122 በሁለቱ የሕግ ስርዓቶች መካከል የተቀመጠ ይመስላል፡፡ በመርህ ደረጃ በፍ/ቤት ፈቃድ በበቂ ምክንያት ክስ ማንሳት የሚቻል ሲሆን በከባድ ወንጀሎች ላይ ግን ክልከላ ተደርጎበታል፡፡

በአጠቃላይ በክስ ማንሳት ወቅት የዐ/ሕግ፤ የመንግስትና የፍ/ቤት ሚና እና ሀላፊነት ምንድን ነው? (ለማስቀጠልም-) ክስ ለማንሳትና ለማስቀጠል ተገቢ ሊሆን የሚችልና ተቀባይነት ሊኖረው የሚገባ ምክንያት የቱ ነው? የሚሉት ነጥቦች በትኩረት መመርመር የሚኖርባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡

ከላይ በተጠቀሱት ህጎች ውስጥ በአንድ በኩል ክስን ለማንሳትና ለማስቀጠል በፍ/ቤት ፍቅድ ስልጣን ላይ ወጥ አቋም ባያንጸባርቁም ክስ ማንሳትና ማስቀጠል በቂ ምክንያት ሊኖረው ወይም የህዝብ ጥቅምን መሰረት ያደረገ ሊሆን እንደሚገባ ያሰምሩበታል፡፡ የቀረበው ምክንያት ተገቢ መሆን አለመሆኑን ደግሞ መመርመር የፍ/ቤት ስልጣን ነው፡፡ በሌላ በኩል ፍ/ቤቱ በጉዳዩ ላይ ብይን ሲሰጥ ምክንያቱን ማስቀመጥ አለበት፡፡ ዐ/ሕግ አቤቱታውን ሲያቀርብም ምክንያት ማቅረብ ያለበት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

በዘፈቀደ ክስን ማንሳትና ማስቀጠል ከፍ/ቤት ነጻነት ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ የፍርድ ቤቶች ነጻነት አንድ ጉዳይ በፍ/ቤት ከቀረበ በኋላ ፍ/ቤቱ በጉዳዩ ላይ ባለሙሉ ስልጣን በመሆኑ በእያንዳንዱ ጉዳይ የመወሰን ስልጣንን ይጎናፀፋል፡፡ እንኳንስ በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር በፍትሐብሔር ጉዳዮች እንኳ ክስ በፍ/ቤቱ ፈቃድ እና ያለፈቃድ ካነሳ በኋላ ማስቀጠሉ ላይ ትልቅ ልዩነት ይፈጥራል፡፡ የፍ/ቤቱን ፈቃድ ለማግኘት ምክንያት ማቅረብ የሚያስፈልግ ሲሆን ከፈቃድ ውጭ ክስን ማንሳት ደግሞ ወደ ፊት በተመሳሳይ ጉዳይ ሌላ አዲስ ክስ ማቅረብ እንዳይችል ያደርገዋል፡፡ (የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 278 – 279) በወንጀል የፍትሕ አስተዳደር ውስጥ በሁሉም መልኩ ሊባል በሚችል መጠን ትኩረትና ጥብቅ ቁጥጥር ያሻል፡፡

የጉዳዩን ጥቅል ይዘት በመመልከት ክስ ለማንሳትም ሆነ የተነሳ ክስ ለማስቀጠል ለህዝብ ጥቅም የተደረጉ መሆናቸውን ፍ/ቤቶች መገምገም አለባቸው፡፡ የክስ ማንሳትና ማስቀጠል ሥርዓት ተገቢ ላልሆነ አላማ እንዳይውል መከልከል አለበት፡፡ በወንጀል የፍትሕ አስተዳደር ላይ የአንድን ሰው የፍትሕ ሥርዓት ግንዛቤ እና እምነት በሚቃረን መልኩ መፈጸም የለበትም፡፡ የህዝብ ጥቅም፤ ፍትሐዊነት ቅንልቦና የሕግ ሥርዓት (ሂደት) (Public interest, Fairness, Good Faith (Bonafide) & Fairness) ታሳቢ ተደርገው የሚፈጸም ሥርዓት ነው፡፡ የማስረጃ ማነስን (Paucity of evidence) የግዜ፤ ገንዘብ እና የውጤታማነት ጉዳዮችን (Time, money & chance of success) ታሳቢ ተደርጎ ክስ የማይነሳ ሲሆን በነዚሁ ታሳቢነትም አይንቀሳቀስም፡፡

በእኛ ሀገር የሕግ ሥርዓት የህዝብ ጥቅም / በቂ ምክንያት የሚሉት የትኞቹን ምክንያቶች ነው የሚለው በግልጽ በሕግ ወይም በፍርድ ተቀምጠው ባይገኙም በዳበሩ የሕግ ስርዓቶች ውስጥ እነዚህ ምክንያቶች በተለመደ ሁኔታ የትኞቹ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም፡-

• ክሶቹ ፖለቲካዊ ወይም ግለሰባዊ በቀልን መሰረት አድርገው ቀርበው ሲገኙ፤ (Political & personal vendetta)

• መንግስታዊ እና ህዝባዊ በሆነ ምክንያት ክስን ለመቀጠል የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች አለመኖር፤

• በሁኔታዎች መቀያየር ምክንያት በክሱ መቀጠል ህዝብና መንግስትን የሚጎዳ ሆኖ ሲገኙ ናቸው፡፡

በክርክር ቀረቦ በተሰማ አንድ ጉዳይ ዐ/ሕግ የክስ ማንሳት አቤቱታ የቀረበ ሲሆን ምክንያቱም “ተጨማሪ ማጣራት የሚገባን ጉዳይ ስላገኘን” የሚል ነበር፡፡ ፍ/ቤቱም የቀረበውን ምክንያት ሳይመረመር በጥቅሉ ተቀብሎት ክሱ ተቋርጧል፡፡ በሌላ ግዜ በተመሳሳይ ጉዳይ ዐ/ሕግ ክስ እንዲንቀሳቀስ አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን የሰጠው ምክንያትም 1ኛው ምስክር ቃሌን አቃናለሁ ያለ በመሆኑ መዝገቡ ይንቀሳቀስ ምስክሮች እንደ አዲስ ይሰሙልኝ በሚል ነው፡፡

በመሰረቱ የቀረበው ምክንያት አሳማኝ እና ለህዝብ ጥቅም የተደረገ ስለመሆኑ ከመመርመሩ በፊት ክስ ለማንሳት የቀረበው ምክንያትና ክስ ለማስቀጠል የቀረበው ምክንያት የተለያዩ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል በክርክሩ ሂደት ተሰምተው የተመለሱ ምስክሮችን ክስን በማቋረጥ እንደገና ቀርበው እንዲሰሙ ማድረግ የክርክር አመራር ስርኣትን ያልተከተለ እና ህገ ወጥ ነው፡፡

በአጠቃላይ የክስ ማንሳትና ማንቀሳቀስ የዐ/ሕግ ያልተሸራረፈ መብት ሳይሆን በሕግ መሰረት በተቋቋሙ ፍ/ቤቶች የሚመራ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት መሆኑን መገንዘብ ያሻል፡፡

አንዋር መሐመድ ~ አቢሲኒያ ሎው

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Law, Left Column Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule