በ1,616 የንግድ ድርጅቶች ላይ ዕርምጃ መወሰዱን ፖሊስ አስታውቋል
ከአሸባሪው ትህነግ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 1,642 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ዘላለም መንግሥቴ እንደገለጹት፣ ከትህነግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ ሰዎችን በማደን በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ እየተደረጉ ናቸው።
እስካሁን ድረስ በተካሄደው የተቀናጀ ምርመራ ከትህነግ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 1,642 ሰዎች፣ በተለያዩ አካባቢዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ አስታውቀዋል።
ከተጠረጠሩት ሰዎች በተጨማሪ ለትህነግ ቡድን ሕገወጥ ተልዕኮ መጠቀሚያ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ የንግድ ድርጅቶች ተዘግተው ምርምራ በመካሄድ ላይ እንደሆነ ገልጸዋል።
ለትህነግ ቡድን መጠቀሚያ የነበሩ ሆቴሎች፣ ሕንፃዎች፣ መጋዘኖች፣ የኢንቨስትመንት እርሻዎች፣ ፋብሪካዎችና ሪል ስቴቶችን ጨምሮ 1,616 ያህል የንግድ ድርጅቶች እንዲዘጉ መደረጉን ጠቅሰዋል።
ፖሊስ ባከናወነው ሥራ 58 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን፣ በተጨማሪም 93 የባንክ ሒሳቦች እንዳይንቀሳቀሱ በማሳገድ የባንክ ሒሳቦቹ ምን ያህል ገንዘብ እንደያዙ በማጣራት ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።
በቀጣይም ከትህነግ ጋር ግንኙነት ያላቸውንና ተልዕኮ ተቀብለው የሚንቀሳቀሱ አካላትን ለማደን የተቀናጀ የምርመራ ሥራና ክትትል የሚደረግ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፣ ለዚህም ተግባር አገር አቀፍ የሆነ የፖሊስ ምርመራ የጋራ ግብረ ኃይል እንዲቋቋም መደረጉን ተናግረዋል።
ግብረ ኃይሉ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚመራ እንደሆነ፣ሁሉንም ክልሎች ከሌሎች አጎራባች ክልሎች ከሚገኙ የወንጀል ምርመራ ዘርፎች ጋር በአንድ ያጣመረ መሆኑ ተገልጿል። ግብረ ኃይሉ በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደሚመራና በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ትህነግ ያሰማራቸውን ሽብርተኞች በመያዝ ለሕግ ከማቅረብ ባሻገር፣ በተደራጁ ወንጀሎችና በሌሎች የሕግ ጥሰቶች ላይ የሚሳተፉ አካላትን በመቆጣጠር የሕግ የበላይነት የሰፈነባትን አገር ለማስቀጠል ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው ተገልጿል። (ሪፖርተር)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
GI.haile says
ሁሉም የቢዝነስ በለቤቶች መነሻ ገንዘቡነረ ያገኙት ከሕወኣት ነው። ስለዚህ ከሚያገኙት ገንዘብ ለድርጅቱ የሚያገቡተሰ ገቢ ኣላቸው። ኣሁን በውጭ የንግድ ዝውውርኑ በማድረገሰ ኣብዛኛው የሕወኣት ቤተሰቦችና የውስጥ ቅርበት ያላቸው በውጭው ዓለም ከአገር ቤት ኣስመጪ ላኪ ጋር ይሰራሉ። ሰዎቹ ዓለም አቀፍ መረብ ዘርግተዋል።