እነ አቶ ስብሃት ነጋ ጉዳያችን በትግራይ ክልል ፍርድ ቤት ይታይልን ሲሉ አቤቱታ አቅርበው ነበር። ይህን አቤቱታ ያቀረቡት ዛሬ (ማክሰኞ) በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው። በችሎት የተገኙት የጠቅላይ አቃቤ ህግ ቡድን በበኩሉላቸው የፌዴራል መንግስትን ስልጣን ለመጣል በሚል የሽብር አዋጁን በመተላለፍ በመላው ሀገሪቱ የተፈጸመ ወንጀል መሆኑን በመጥቀስ ተጠርጣሪዎቹ መቀሌ ሆነው በሰጡት ትዕዛዝ ባህርዳር እና ጎንደርን በሮኬት ማስደብደባቸው አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል። በተጨማሪም ተከሳሾቹ ስልጣን ተከፋፍለው በተለያዩ ቦታዎች የተፈጸመ ወንጀል ነው ያለው አቃቤ ህግ ዶክተር አዲስ አለም ባሌማ የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ሆነው አዲስ አባባ ቁጭ ብለው ሲፈጽሙ የነበረው ወንጀል አንድ ቦታ አለመሆኑን ማመላከቻ ነው ብሏል በምላሹ። ይህ … [Read more...] about እነ ስብሃት ነጋ ጥያቄያቸው ውድቅ ሆነ
Law
የሕግ ያለህ
ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር
እንደምን ሰነበታችሁ! እንኳን በጤና ተገናኘን! “በሚኖሩባት ሰዎች ክፋት የተነሳ ፍሬያማዋን ምድር ጨው አደረጋት” የሚል ቃል በቅዱሱ መጽሀፍ ውስጥ ሰፍሯል።ሕዝብ መቼም ቢሆን ክፉ ሆኖ አያውቅም፤ አይሆንምም። ነገር ግን ከሕዝብ የወጡ ጥቂቶች በዕኩይ ዓላማና ምግባራቸው ምድሪቱን ለጥፋት፣ ሕዝቡንም ለስቃይ ይዳርጋሉ። ይህንን ለማረጋገጥ ባህር ተሻግረን ማሳያ መፈለግ ሳይጠበቅብን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ነኝ ባይ የነበረውን ትህነግን ማየት ይበቃል። ትህነግ ግማሽ ምዕት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ በሕዝብ ትከሻ ላይ ተንጠላጥሎ፤ በሕዝብ ገላ ላይ እንደመዥገር ተጣብቆ የኢትዮጵያ ሾተላይ ሆኖ ኖሮ ሞቷል።ነጻነት ሳያውቅ ህዝብን ነጻ አወጣለሁ ብሎ ደደቢት ላይ የተፈለፈለው እፉኝት በሞቱ ለኢትዮጵያ ነጻነት ታውጇል። “ቀን ያስጎነበሰውን ቀን ቀና ያረገዋል” እንዲሉ የካቲት 11 ቀን … [Read more...] about ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር
ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው
በአገር ክህደት እና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በነበሩ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው፦ ኮማንደር ሰለሞን አብርሃ ብስራት 2. ኮማንደር ሀይለማርያም ብርሃኔ ገ/ማርያም 3. ም/ኢ/ር ክብሮም ገብሩ ገ/እግዚአብሄር 4. ም/ኢ/ር አረጋዊ ገ/ሂወት አስፋዉ 5. ረ/ኢንስፔክተር ገዛኢ ገ/ሂወት ገ/ስላሴ 6. ረ/ኢንስፔክተር ተስፋ ኪሮስ ግደይ 7. ረ/ኢንስፔክተር አርአያ ገ/አናንያ ኪዳኑ 8. ረ/ኢንስፔክተር ሰለሞን ወላይ ወ/አብዝጊ 9. ዋ/ሳጅን ሀይላይ ወልዱ ገ/ማርያም 10. ዋ/ሳጅን ሀፍቱ ካህሳይ አብርሃ ናቸው። በመሆኑም መላው የሃገራችን ህዝቦች በተለይም ደግሞ ሰላም ወዳዱ የትግራይ ህዝብ፤ እንዲሁም የሀገር መከላከያ … [Read more...] about ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው
በመቀሌ መከላከያ የማያውቀው የጦር መሳሪያ ዲፖ ተገኘ
በመቀሌ ከተማ የጥፋት ሃይሉን አባላትና የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል የቤት ለቤት ፍተሻ ተጀምሯል። በዚህም በከተማው የጥፋት ቡድኑ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ዴፖ በብርበራ በሰራዊቱ ተይዟል። በወቅቱም ሶስት ኮንቴነር ጠመንጃ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ ጥይቶች፣ ክላሽንኮብ መሳሪያ፣ ስናይፐር፣ አድማ መበተኛ የጭስ ቦምብ እና ፈንጅዎች ተይዘዋል። በተጨማሪም የትግራይ ልዩ ሃይል መለዮና የአባላት መታወቂያዎች መያዛቸውም ታውቋል። ሰራዊቱ አሁን ላይ በሚያካሂደው የፍተሻና ብርበራ የጥፋት ሀይሉ ሊጠቀምባቸው የሚችሉ በርካታ የጦር መሳሪያዎች እንደሚያገኝም ይጠበቃል ነው የተባለው። ለዚህም የትግራይ ህዝብ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል። በተያያዘ ዜና ከቀናት በፊት በመከላከያ ሰራዊቱ ቁጥጥር ስር በዋለችው መቀሌ ከተማ በተወሰነ መልኩም ቢሆን … [Read more...] about በመቀሌ መከላከያ የማያውቀው የጦር መሳሪያ ዲፖ ተገኘ
ፌዴራል ፖሊስ መቀሌ ገባ፤ በትግራይ ሰላም እያስጠበቀ ነው
የአክሱም ጽዮን ማሪያም ንግስ በዓልም በሰላም ተከናውኗል በጁንታው ላይ የተወሰደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ በድል መጠናቀቁን ተከትሎ የፌዴራል ፖሊስ ነጻ በወጡ አካባቢዎች ገብቶ የኅብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት በማስከበር ላይ እንደሆነ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የጽዮን ማሪያም ንግስም በሰላም መከናወኑ ተገልጿል። ከሀዲው የህወሓት ቡድን የሀገር ሉዓላዊነትን በመዳፈር በሀገር መከላከያ ሰራዊትና በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ በፈፀመው ጥቃት የተጀመረው የህግ ማስከበር ዘመቻ በድል መጠናቀቁን ያስታወሰው ኮሚሽሽኑ፤ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች ላይ የፌዴራል ፖሊስ ገብቶ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት እያስከበር ይገኛል። ህብረተሰቡም መደበኛ የዕለት ተዕለት ኑሮውን መጀመሩ ተገልጿል። ለተመሳሳይ የጸጥታ ማስከበር ስራ ወደ … [Read more...] about ፌዴራል ፖሊስ መቀሌ ገባ፤ በትግራይ ሰላም እያስጠበቀ ነው
በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም በዝግጅት ላይ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም በዝግጅት ላይ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ። የከተማው ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር አየልኝ ታክሎ፤ የከተማው ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ጋር ባደረጉት ክትትል ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል። ግለሰቡ ለሽብር ተግባር ለመጠቀም ካዘጋጃቸው 35 ተቀጣጣይ ቁሳቁስ፣ 216 ማሰልጠኛ ማንዋል፣ ሶስት የተለያዩ ባንኮች ደብተር፣ 20 ገንዘብ ገቢና ወጪ ደረሰኝ እና ከአንድ ላፕቶፕ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉንም ተናግረዋል። በግለሰቡና በግብረ አበሮቹ ላይ የሚደረገው ምርመራ እንደቀጠለ መሆኑን የገለፁት ኮማንደር አየልኝ ስለጉዳዩ ዝርዝር መረጃ እንደሚሰጥም ጠቅሰዋል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም በዝግጅት ላይ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
ህወሓት በማይካድራ በፈፀመው ወንጀል በሽብርተኝነት እንዲፈረጅ ተጠየቀ
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ሕወሓት ዘርን መሠረት አድርጎ በማይካድራ በፈፀመው የንጹሐን ዜጎች የግድያ ወንጀል መንስዔ በሽብርተኝነት እንዲፈረጅ ጠየቁ። አባላቱ ይህንን እና ሌሎች መሰል ወቅታዊ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቅርበዋል። የተደረገው ፍጹም ጭካኔያዊ እና አረመኔያዊ ድርጊት እጅግ እንዳሳዘናቸውም አያይዘው ገልጸዋል። ተግባሩም የጦር ወንጀለኝነት መሆኑንም አበክረው ተናግረዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አክለውም፤ የሀገርን እና የህዝብን አደራ ተቀብለው ግዳጃቸውን እየተወጡ በነበሩት የሰሜን ዕዝ የሠራዊት አባላት ላይ የሕወሓት ጽንፈኛ ቡድን የወሰደው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊትም እጅግ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል። በየትኛውም የህግ መመዘኛ ተቀባይነት እንደሌለውም አስረድተዋል። የፓርላማ አባላቱ በተጨማሪም፤ የኢፌዴሪ የሀገር … [Read more...] about ህወሓት በማይካድራ በፈፀመው ወንጀል በሽብርተኝነት እንዲፈረጅ ተጠየቀ
ዐቃቤ ሕግ በ167 የህወሃት ሰዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱን አስታወቀ
በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በ167 ሰዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱን ይፋ አደረገ። ይህ የተባለው የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ትናንት በጋራ በሰጡት መግለጫ ነው። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ በመግለጫው ላይ በህውሓት ኃይሎች የተፈጸሙት ተግባራት በአገሪቱ የወንጀል ሕግ አንጻር በከፍተኛ ወንጀል የሚያስጠይቁ ናቸው ብለዋል። በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የተፈጸመው ጥቃት 'የመንግሥትን አገሪቱን የመከላከል ኃይል ለማዳከም' በተፈጸመ ወንጀል በሚል የሚያስጠይቅ መሆኑን ጠቁመዋል። በባሕር ዳር እና ጎንደር ከተሞች ላይ የተፈጸሙትን የሮኬት ጥቃቶች በተመለከተም፤ ድርጊቱ በሽብር ወንጀል … [Read more...] about ዐቃቤ ሕግ በ167 የህወሃት ሰዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱን አስታወቀ
መከላከያ ፈጣን ምላሽ የሚሰጡ ሁለት ዕዞች አቋቋመ
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት የሚሰጡኝን ግዳጆች በፍጥነት ማከናወን ያስችሉኛል ያላቸውን ተጨማሪ ሁለት ዕዞች ማደራጀቱን ትላንት አስታውቋል። አዲሶቹ ዕዞች በዚህ ዓመት ወደ ስራ ይገባሉ ተብሏል። ዕዞቹ በውስጥም በውጭም የሚቃጡ ጥቃቶችና ችግሮችን ፈጥነው ለመከላከል እንዲችሉ ታስቦ የተደራጁ እንደሆኑ ተገልጿል። ማዕከላዊና ሰሜን ምዕራብ አዲስ የተደራጁት ዕዞች ሲሆኑ የቀደሙት ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዕዞች መኖራቸው ይታወቃል። ዕዞቹ አዲስ አበባና ባሕር ዳር ላይ እንደሚደራጁ ሁለቱ ጄኔራሎች በመግለጫቸው አስታውቀዋል። (ኢዜአ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about መከላከያ ፈጣን ምላሽ የሚሰጡ ሁለት ዕዞች አቋቋመ
ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከ2.6 ሚሊዮን በላይ ብር በቁጥጥር ሥር ዋለ
የአዲስ አበባ ፖሊስ በህገወጥ መንገድ የተከማቸ ከ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ብር በህዝብ ጥቆማ መያዙን አስታወቀ። በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በአንድ ንግድ ቤት ውስጥ የተከማቸ ከ2 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ በላይ የኢትዮጵያ ብር በህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ኮሚሽኑ ገልጿል። ከባንክ ውጪ የሚገኙ በርካታ ብሮችን ወደ ባንክ እንዲገቡ በማድረግ የኢኮኖሚ ሥርዓቱን ለማስተካከል እና የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር ታሳቢ ባደረገ መንገድ የብር ኖት መቀየሩን ተከትሎ የሚፈፀሙ ህገ- ወጥ ተግባራትን ለመከላከል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በርካታ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ደንበል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ የንግድ ቤት ውስጥ የተከማቸ ገንዘብ ስለመኖሩ ከህዝብ ጥቆማ መምጣቱን የደንበል አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ … [Read more...] about ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከ2.6 ሚሊዮን በላይ ብር በቁጥጥር ሥር ዋለ