
የአክሱም ጽዮን ማሪያም ንግስ በዓልም በሰላም ተከናውኗል
በጁንታው ላይ የተወሰደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ በድል መጠናቀቁን ተከትሎ የፌዴራል ፖሊስ ነጻ በወጡ አካባቢዎች ገብቶ የኅብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት በማስከበር ላይ እንደሆነ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የጽዮን ማሪያም ንግስም በሰላም መከናወኑ ተገልጿል።
ከሀዲው የህወሓት ቡድን የሀገር ሉዓላዊነትን በመዳፈር በሀገር መከላከያ ሰራዊትና በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ በፈፀመው ጥቃት የተጀመረው የህግ ማስከበር ዘመቻ በድል መጠናቀቁን ያስታወሰው ኮሚሽሽኑ፤ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች ላይ የፌዴራል ፖሊስ ገብቶ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት እያስከበር ይገኛል። ህብረተሰቡም መደበኛ የዕለት ተዕለት ኑሮውን መጀመሩ ተገልጿል።
ለተመሳሳይ የጸጥታ ማስከበር ስራ ወደ አክሱም ከተማ የገባው የፀረ-ሽብር ልዩ ኮማንዶ ሀይል ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ/ም በአክሱም ከተማ የተከበረውን ዓመታዊ የፅዮን ማርያም ንግስ በዓል ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ያለምንም የፀጥታ ችግር ማክበር እንዲችል አድርጓል።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በህግ የሚፈለጉ ተጠርጣሪ የጁንታው አባላትን ከገቡበት ገብቶ በቁጥጥር ስር ለማዋል የፀረ-ሽብር ልዩ ኮማንዶ ሀይል ወደ አካባቢው በማሰማራት የክትትል ስራውን አጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል።
በዚህ ወቅት በተሰራው ጠንካራ የጸጥታ ማስከበር ስራ ከሀዲው የህወሓት ቡድን ለእኩይ ተግባሩ ሊጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ የጦር መሳሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ያለው ኮሚሽኑ፤
ይህ መስዋዕትነት ተከፍሎበት እየተሰራ ያለው የህግ ማስከበር ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል። (መሀመድ ሁሴን፤ ኢ.ፕ.ድ)
በሌላ በኩል የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሀይል ረቡዕ መቀሌ መግባቱን ኮሚሽኑ አስታውቋል።
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ልዩ ኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም መቀሌ ከተማ በመግባትና ከጀግናው ሀገር መከላከያ ጋር በመቀናጀት የጁንታውን ተፈላጊ ወንጀለኛ ቡድን ማደን ጀምሯል።
የኮማንዶ ቡድኑ በከተማዋ በሚያደርጋቸው አሰሳዎችና የተለያዩ ኦፕሬሽኖች የሚገኙ ውጤቶችን በቀጣይ ለህዝባችን ይፋ እያደረግን የምንቀጥል መሆኑን እናስታውቃለን በማለት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply