በአገር ክህደት እና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በነበሩ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው፦
- ኮማንደር ሰለሞን አብርሃ ብስራት
2. ኮማንደር ሀይለማርያም ብርሃኔ ገ/ማርያም
3. ም/ኢ/ር ክብሮም ገብሩ ገ/እግዚአብሄር
4. ም/ኢ/ር አረጋዊ ገ/ሂወት አስፋዉ
5. ረ/ኢንስፔክተር ገዛኢ ገ/ሂወት ገ/ስላሴ
6. ረ/ኢንስፔክተር ተስፋ ኪሮስ ግደይ
7. ረ/ኢንስፔክተር አርአያ ገ/አናንያ ኪዳኑ
8. ረ/ኢንስፔክተር ሰለሞን ወላይ ወ/አብዝጊ
9. ዋ/ሳጅን ሀይላይ ወልዱ ገ/ማርያም
10. ዋ/ሳጅን ሀፍቱ ካህሳይ አብርሃ ናቸው።
በመሆኑም መላው የሃገራችን ህዝቦች በተለይም ደግሞ ሰላም ወዳዱ የትግራይ ህዝብ፤ እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሰራዊት፤ የአገራችን የፖሊስ ሰራዊትና የደህንነት ተቋማት እነዚህን የጁንታው የህዋሃት የጥፋት ቡድን ተፈላጊዎች አባላት አድኖ ለህግ ለማቅረብ እየተደረገ ባለው ተግባር በያላችሁበት የድርሻችሁን እንድትወጡ ኮሚሽኑ ጥሪ እያቀረበ፤ በቀጣይም መቀሌ ከተማ የገባው የኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን በሚያደርጋቸው አሰሳዎችና የተለያዩ ኦፕሬሽን የሚገኙ ውጤቶችን እተከታተለ መረጃዎችን በመገናኛ ብዙሃን በኩል ለህብረተሰቡ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያስታውቃል።
©የኢ.ፈ.ዲ.ሪ. ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን
Leave a Reply