• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

እነ ስብሃት ነጋ ጥያቄያቸው ውድቅ ሆነ

March 23, 2021 10:23 pm by Editor 1 Comment

እነ አቶ ስብሃት ነጋ ጉዳያችን በትግራይ ክልል ፍርድ ቤት ይታይልን ሲሉ አቤቱታ አቅርበው ነበር።

ይህን አቤቱታ ያቀረቡት ዛሬ (ማክሰኞ) በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው።

በችሎት የተገኙት የጠቅላይ አቃቤ ህግ ቡድን በበኩሉላቸው የፌዴራል መንግስትን ስልጣን ለመጣል በሚል የሽብር አዋጁን በመተላለፍ በመላው ሀገሪቱ የተፈጸመ ወንጀል መሆኑን በመጥቀስ ተጠርጣሪዎቹ መቀሌ ሆነው በሰጡት ትዕዛዝ ባህርዳር እና ጎንደርን በሮኬት ማስደብደባቸው አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ተከሳሾቹ ስልጣን ተከፋፍለው በተለያዩ ቦታዎች የተፈጸመ ወንጀል ነው ያለው አቃቤ ህግ ዶክተር አዲስ አለም ባሌማ የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ሆነው አዲስ አባባ ቁጭ ብለው ሲፈጽሙ የነበረው ወንጀል አንድ ቦታ አለመሆኑን ማመላከቻ ነው ብሏል በምላሹ።

ይህ የሚያሳየው በሃገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች መፈጸማቸውን ስለሆነ በአካባቢ ስልጣን ሳይገደብ ጉዳያቸው መታየት ያለበት በፌዴራል ፍርድ ቤት ነው ሲል በጠበቆቻቸው ያነሱት መከራከሪያ ውድቅ እንዲደረግ ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች ቀዳሚ ምርመራ መደረግ የለበትም አቃቤ ህግም ቀዳሚ ምርመራ እንዲደረግ ያዘዘው ትዕዛዝ አግባብነት የለውም የቀዳሚ ምርመራ ህጉ ተሽሯል ብለው ያነሱት መቃወሚያ በተመለከተም፤ አቃቤ ህግ በቂ ምክንያት ካለው በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ አንቀጽ 38 ቀዳሚ ምርመራ ማድረግ ይችላል ብሏል።

እንዲሁም በአንቀጽ 80 ንዑስ አንጽ 2 ስር ህጉን ተከትሎ የቀዳሚ ምርመራ የመወሰን ስልጣን እንዳለው ያስቀምጣል ሲል አብራርቷል።

የቀዳሚ ምርመራ ህግ ሙሉ ለሙሉ አልተሻረም በስራ ላይ ይገኛል ሲል ምላሽ የሰጠው አቃቤ ህግ፤ የውንብድና ወንጀል እና የግፍ ግድያ የተፈጸመ ከሆነ ቀዳሚ ምርመራ ሊደረግ እንደሚችል በህጉ ያስቀምጣል ሲል የአቃቤ ህግ ቡድን ምላሽ ሰጥቷል።

በተጨማሪም የቀዳሚ ምርመራ ምስክሮች ስምና ዝርዝሩ አልተገለጸም እዚህ ላይ ትዕዛዝ ይሰጥልን ሲሉም ላቀረቡት አቤቱታ አቃቤ ህግ የምስክር ጥበቃ አዋጅን ተከትሎ ለምስክሮች ደህንነት ሲባል የስም ዝርዝራቸው እንደማይሰጥ አብራርቷል።

ከዚሀም ባለፈ የተጠርጣሪ ጠበቆች ዳኛው ከዚህ በፊት በነበረ የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይን ሲመለከቱ መዝገባችን ተለይቶ ይቅረብ ብለን የጠየቅነው ጥያቄ ሳይታይ አልፏል የሚል ምክንያት በማንሳት ዳኛው ከዚህ ከቀዳሚ ምርመራ መዝገብ ይነሱልን ሲሉም አመልክተዋል።

እንዳጠቃላይ በተነሱ መከራከሪያ ነጥቦች ላይ ፍርድቤቱ ምርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለመጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን፤ በትናንትናው እለት ችሎት ከደንበኞቻቸን ጋር ባልተመካከርንበት ሁኔታ ምስክር መሰማቱ ተገቢ አይደለም ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠን ብለው ያቀረቡት አቤቱታን መርምሮ ችሎቱ የመመካከሪያ በቂ የ7 ቀን ጊዜ ሰጥቻለሁ ሲል ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጓል።

ችሎቱ ስብሃት ነጋ በግል ሃኪም እንዲታከሙ የታዘዘው ትዕዛዝ ተፈጻሚ እንዲሆን አዟል።

አባይ ወልዱ ለዐይናቸው ህመም በግል እንዲታከሙ ያቀረቡት አቤቱታን ተቀብሎ ትዕዛዝ ሰጥቷል። (ፋና)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Law, Left Column Tagged With: operation dismantle tplf, sibhat, tplf, ችሎት

Reader Interactions

Comments

  1. gihaile says

    April 3, 2021 12:09 am at 12:09 am

    እነዚህ ወንጀለኞች መታየትና መመርመር የነበረባቸው በወታደራዊ የጦር ፍርድ ቤት እንጂ በሲቪል ፍርድ ቤት ኣልነበረም። እነዚህ ግለሰቦች የጦር ወንጀለኞችና የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የአገር ሐብትን የመዝረፍ ሕገወጥ ተግባር ጋር የተገናኘ ነው።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule