የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ እና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ግብራበሮቹ ላይ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ህግ በዛሬው እለት ክስ መስርቷል፡፡
ተከሳሾች 1ኛ አቶ ምትኩ ካሳ ጉትሌ (የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩ) ፣2ኛአቶ አራጋው ለማ (የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የፋይናንስ ዳይሬክተር)፣ 3ኛ አቶ የማነ ወ/ማሪያም (የኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንደ ዴቭሎፕመንት አሶሴሸን ዋና ዳይሬክተር የነበሩ)፣ 4ኛ ዶ/ር ዮናስ ወ/ትንሳይ (የኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንደ ዴቭሎፕመንት አሶሴሸን የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ ናቸው፡፡
በተጨማሪም 5ኛ አቶ ደመውዝ ኃይሉ (ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንደ ዴቭሎፕመንት አሶሴሸን የፋይናንስ ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ) ፣6ኛ ወ/ሮ ሶፊያ ጀማል ሰላሙ (የ1ኛ ተከሳሽ የትዳር አጋር) 7ኛ ወ/ሮ ሚልካ ምትኩ ካሳ (የምትኩ ካሳ ልጅ)፣ 8ኛ አቶ ኢያሱ ምትኩ ካሳ (የምትኩ ካሳ ልጅ)፣ 9ኛ አቶ መብራቱ አሰፋ (የኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንደዴቭሎፕመንት አሶሴሸን የመጋዘን ንብረት መዝጋቢ/ሰቶር ኦፊሰር) ፣ 10ኛአቶ ገ/ሚካኤል አብረሓ (የኤልሻዳይ አሶሴሽን ሰቶር ኦፊሰርና የንብረት ክፍል ሰራተኛ) ፣ 11ኛ ደረጃ አቶ ዮሃንስ በላይ ተድላ፣ 12ኛ አቶ ጌቱ አስራት እና 13ኛ ወ/ሮ ሕይወት ከበደ ላይ ክስ ተመስርቷል፡፡ (ኢፕድ)
የክሱ ዝርዝር እዚህ ላይ ይገኛል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply