በአዲሱ መንግሥት ምስረታ ውስጥ የቋሚ ኮሚቴ አባላት ከ7 እስከ 13 ሆኖ የሚደራጅ ሲሆን አባላቱም እንደየ ሙያቸው ዘርፎችን እንዲከታተሉ የሚደረግ መሆኑን አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ገለጹ።የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ለመንግሥት ምስረታው እየተደረገ ያለውን ዝግጅት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ የመንግሥት ምስረታ የሚካሄድ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ገልጸዋል። አፈ-ጉባዔው በሕገ መንግስቱ መሰረት መስከረም መጨረሻ ባለው ሰኞ የመንግስት ምስረታው ይካሄዳል ብለዋል። የሕግ አወጣጥ ሂደቱን አስመልክቶ የተካሄደውን ጥናት መነሻ በማድረግ የሕግ አወጣጡን የሚያዘምን መመርያ ተዘጋጅቷል ብለዋል። ምክር ቤቱ የክትትልና ቁጥጥር ስርዓቱን ማዘመን የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ተዘርግቷል ያሉት … [Read more...] about መስከረም 24 አዲስ መንግሥት ይመሠረታል፤ የቋሚ ኮሚቴ አባላት ከ7 እስከ 13 ሆኖ ይደራጃል
paliament
ኃይለማርያም ከየት ይለቃል? ያልነበረ “ፓርላማ” ወዴት ይበተናል?
ከወራት በፊት የመልቀቂያ ደብዳቤ ያስገባውን አባዱላ ገመዳ የኢህአዴግ ሥራአስፈጻሚ ጥያቄውን አጽድቆለታል ተብሏል። ከዚህ ጋር ተከትሎ በቀጣይ ኃይለማርያም ከ“ሥልጣን” ይወርዳል የሚለው ጉዳይ በስፋት በሁሉም ዓይነት ሚዲያ እየተስተጋባ ነው። በተያያዘ ወሬ አዲስ አበባ ላይ ያለውና ሰሞኑን በመጠኑ ሥራውን መሥራት የጀመረውን “ፓርላማ” ህወሓት ሊበትነው እያቀደ ነው የሚል መረጃ ተሰምቷል። ከዚህ በተጨማሪም ከትግራይና ሌሎች ታማኝ ክልል/ሎች በስተቀር በክልል የሚገኙ ምክርቤቶችን በሙሉ ህወሓት ሊበትናቸው አሢሯል የሚል መረጃ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ እየተሰማ ነው። ከገቢ አንጻር የሰበር ዜና ልክፍት የተጠናወተው ሚዲያ ይህ መሰሉን “መረጃ” ሲያስተላልፍ ከመረጃው ጋር ሕዝብ ማወቅ ያለበት ምንድነው የሚለውን ኃላፊነት የዘነጋው ይመስላል። ኃይለማርያም ደሳለኝ በሟቹ መለስ ተመልምሎ ወደ … [Read more...] about ኃይለማርያም ከየት ይለቃል? ያልነበረ “ፓርላማ” ወዴት ይበተናል?