የክልል መስተዳድሮችም በየደረጃው ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ተነግሯቸዋል ሙስና ሀገርን የሚበላ ነቀዝ ነው፡፡ የሀገርን አንጡራ ሀብት እየቦረቦረ ጥሪቷን ባዶ ለማስቀረት ሌት ተቀን የሚማስን ተባይ ነው። ዋልጌ ባለሥልጣናት፣ በፍቅረ ነዋይ የታወሩ ደላሎች እና ባለሃብቶች አንድ ላይ ሲገጥሙ፤ ከነዚህ የሌብነት ፊታውራሪዎች ጀርባ ብዛት ያላቸው ዜጎች መሰለፍ ሲጀምሩ ሙስና የተባለው ነቀዝ ሀገርን እንደ ወረርሽኝ ያጠቃታል፡፡ ሙስና በየትኛው ቦታና በየትኛውም ዘመን ሊኖር ይችላል፡፡ ነገር ግን የሀገርን ልማት አጥንቱ ድረስ እስከ መጋጥ ከደረሰ ሙስና አንድ አደገኛ ወረርሽኝ ሆኗል ማለት ነው፡፡ ሙስና ሀገርን ሊያፈርስ የሚችል የደኅንነት ሥጋት መሆኑን ያስመሰከሩ ሀገሮችን በዘመናችን አይተናል፡፡ የአደንዛዥ ዕጽ፣ የኮንትሮባንድ፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ንግድ፣ … [Read more...] about በሌብነት “አደገኛ ወረርሽኝ” ላይ አገራዊ ጦርነት ታወጀ
News
ዜና
የወልቃይት-ጠገዴ ትግል መቋጫው ገና ነው
"እናንተ የመለስናችሁ ለእረፍት እንጂ ጥያቂያችን መቋጫ አግኝቶ ትግል ስላበቃ አይደለም ። የወልቃይት-ጠገዴ ነፍጥ ገና ይጠብቃል እንጂ አይወርድም። እኔ በዚህ እድሜዬ ጋቢ ለብሼ ከዘራ ይዤ ቤተክርስቲያን ሲሄድ ነበር የሚያምርብኝ። ነገር ግን አሁንም በዚህ እድሜዬ ጠበንጃ ተሸክሜ የምታዩኝ የወልቃይት-ጠገዴ ትግል መቋጫው ገና ስለሆነ ነው። ጥያቄው እልባት ሲያገኝ እናንተም በሙሉ ልብ ወደ ልማታችሁ እኔም ገዘራ ይዤ ጋቢ ለብሸ የምሄድ ይሆናል"ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱየወ/ጠ/ሰ/ሁ/ዞን ም/አስተዳዳሪና ሰላምና ደህንነት ሃላፊ "የወልቃይት-ጠገዴ ህዝብ ሲኖርም በምክንያት ሲሞትም በምክንያት ነው። አሁን እየተዳደርን ያለነው በምንፈልገው የቤጌምድር አማራ ማንነት ነው። በዚህም እንቀጥላለን። በህግ ጥያቄ ያለው ካለ በህግ ይጠይቀን።በህዝብ ፍላጎት መሰረት እስከሆነ ድረስ አስተዳደራችንም ድሮም … [Read more...] about የወልቃይት-ጠገዴ ትግል መቋጫው ገና ነው
በፓርላማው ውሎ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሾች
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች‼️ የምክር ቤት አባላቱ ፦- የስምምነቱ ሂደት እንደምታውና ፋይዳው ምንድነው ?- በጦርነቱ የተጐዱ አካባቢዎችን ፍትሃዊ በሆነ መልኩ የመልሶ ለመገንባት ምን ዝግጅት ተደርጓል ?- አንዳንዶቹ ስምምነቱ ከTPLF እንጂ ከTDF ጋር አይደለም ? ... ወዘተ የሚሉ የተለያዩ ሃሳቦችን እየሠነዘሩ ይገኛሉ ፤ የእነኚህ አካላት ፍላጎት ምንድን ነው ? ውሳኔዎችንስ ተግባራዊ ለማድረግ እነቅፋት አይሆንም ወይ?- የምክክር ኮሚሽን የእስካሁኑ አፈፃፀም ያለበት ደረጃ እንዲሁም በውይይት ሂደቱ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ምቹ ሁኔታዎችና ስጋቶች ምንድን ናቸው?- ውይይቱ ተሳክቶ መላው የሀገራችን ሕዝቦች ወደ ሚናፍቁት ልማት ፊታቸውን እንዲያዞሩ ከባለድርሻ አካላት ማለትም ከምሁራ፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ ወጣቶችና ከመላው … [Read more...] about በፓርላማው ውሎ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሾች
“ወልቃይቴ፤ ወልቃይቴ ነው፤ ይታወቃል” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
በዛሬው የፓርላማ ውሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ስለ ወልቃይት የተናገሩት፤ “ወልቃይትን በሚመለከት የሚነገሩ ሽረባዎች፣ ሴራዎች፣ conspiracies ብዙ እሰማለሁ። የኢትዮጵያ መንግስት በእነዚህ ሽረባዎች ውስጥ እጁ የለበትም። የወልቃይት ህዝብ እንዲገነዘብ የምንፈልገው፤ የሚወራው፣ የሚናፈሰው አሉባልታ ውስጥ የኢትዮጵያ መንግስት እጁ የለበትም።” “እኛ ደቡብ አፍሪካ የሄድንው ወልቃይት ወደ አማራ ይሁን ወደ ትግራይ ይሁን የሚለውን ለመወሰን አይደለም። የፕሪቶሪያው ‘ሰሚትም’ ይኸን ለመወሰን ስልጣን የለውም። ምን አገባው እና ነው የኢትዮጵያን መሬት እዚያ ሂድ እዚህ ሂድ የሚለው? እኛ እዚያ የሄድንው እንዴት ሰላም አምጥተን በንግግር ችግሮቻችንን እንፍታ ለማለት ነው። ለምን ወልቃይት ተስቦ እዚያ ውስጥ እንደሚገባ አላውቅም።” “ወልቃይት ብቻ አይደለም፤ ሰሜን ሸዋ ላይ ኦሮሚያ … [Read more...] about “ወልቃይቴ፤ ወልቃይቴ ነው፤ ይታወቃል” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
“(ላለፉት 4 ዓመታት) ሪፖርት ባለማቅረባችን ክቡር አፈ ጉባዔውን በግል እወቅሳቸዋለሁ” ወ/ሮ መዓዛ
የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚ አካል የፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ማክበር ካልቻለ ሥርዓት ተሰብሯል ማለት እንደሆነ፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ተናገሩ። ላለፉት አራት ዓመታት ሪፖርት ሊያቀርቡ ባለመቻላቸው አፈጉባዔውን ወቅሰዋል። ፕሬዚዳንቷ ይህን የተናገሩት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ፣ ከፍተኛና ጠቅላይ፣ እንዲሁም የሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን፣ የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድና የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ ክንውን ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በገመገመበት ወቅት ነው። ምክር ቤቱ ባካሄደው የአንድ ቀን የፍርድ ቤቶች ግምገማ ከምክር ቤት አባላትና ከሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች፣ ፍርድ ቤት ከወሰነላቸው በኋላ ውሳኔ የማይከበርላቸውን አካላት በተመለከተ በርካታ ጥያቄዎች ቀርበዋል። የሕግ … [Read more...] about “(ላለፉት 4 ዓመታት) ሪፖርት ባለማቅረባችን ክቡር አፈ ጉባዔውን በግል እወቅሳቸዋለሁ” ወ/ሮ መዓዛ
ስምምነቱን በማይቀበሉ ወይም ዕንቅፋት በሚፈጥሩ ላይ አሜሪካ ዕርምጃ ትወስዳለች
በተጀመረ በአስረኛው ቀን ይፋ የሆነውን የሰላሙን ስምምነት ማክበር ለአሜሪካ ቀዳሚ አጀንዳ እንደሆነ በተለያዩ ኃላፊነት ላይ ያሉ ባለሥልጣኖች ቢናገሩም፣ ስምምነቱ ከመፈረሙ ከቀናት በፊት የስምምነቱን ውጤት በተመለከተ አሜሪካ አስቀድማ ውጤት አመላካች የሆነ ማስጠንቀቂያዋ ከወትሮው የከረረ ነበር። ይኸው ማስጠንቀቂያ ዛሬ የተገላቢጦሽ የሚሠራ መሆኑ ደግሞ ዜናውን ትኩስ አድርጎታል። ለትህነግ ያላትን ወገንተኝነት ያለ ኃፍረት በዓለምአቀፍ መድረኮች ስታስተጋባና አጀንዳ እየተከለች ኢትዮጵያ ላይ ጫናዋን ስታበረታ የነበረችው አሜሪካ፣ የሰላሙ ንግግር ከመጀመሩ ቀናት በፊት ውጤቱን አስመልክታ ያወጣቸውን መግለጫ ወይም አቋም ቁጣ ቀላቅለው ያስታወቁት በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ ነበሩ። ከትህነግ ጋር ቤተሰባዊ ግንኙነት እንዳላቸው በሥፋት በፎቶ … [Read more...] about ስምምነቱን በማይቀበሉ ወይም ዕንቅፋት በሚፈጥሩ ላይ አሜሪካ ዕርምጃ ትወስዳለች
ከ300 ሺህ ዶላር በላይ ወደ ውጭ ሃገር ለማስወጣት የሞከረ አሽከርካሪ ተያዘ
በአዳማ ከተማ ከ300 ሺህ ዶላር በላይ ወደ ውጭ ሃገር ለማስወጣት የሞከረ አሽከርካሪ መያዙን የከተማዋ ፖሊስ መመሪያ አስታወቀ። አሽከርካሪው የተያዘው ኮድ 3/89158 ኢ.ት በሆነ ሎቤድ መኪና ገንዘቡን ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ በስውር ደብቆ ሲያጓጉዝ ነው።በአዳማ ከተማ ዳቤ ክፍለ ከተማ ዳቤ ሶሎቄ ልዩ ቦታው ኬላ ፍተሻ ላይ የተያዘው የገንዘብ መጠንም 302ሺህ 400 የአሜሪካን ዶላር መሆኑን 2015የመመሪያው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ምክትል እንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ገልጸዋል።በብሔራዊ ደህንነትና በአዳማ ከተማ የፀጥታ ሃይሎች ትብብር በ23/2/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ላይ የተያዘው ይሄ ገንዘብ ወደ ውጭ ሃገር በሚጓዝ የኮንቴይነር ጭነት ስር በስውር ቦታ ተደብቆ መሆኑንና አሽከርካሪውም በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ነው ያስረዱት። (Tikvah) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ከ300 ሺህ ዶላር በላይ ወደ ውጭ ሃገር ለማስወጣት የሞከረ አሽከርካሪ ተያዘ
ባለፉት ሦስት ወራት የተያዘ ህገ ወጥ ሲሚንቶና ነዳጅ
በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በህገ ወጥ መልኩ ሲዘዋወር የነበረ ከ71 ሺህ ኩንታል በላይ ሲሚንቶ እና 500,153 ሊትር ነዳጅ ተይዟል። በዚህም መሰረት፦- በአዲስ አበባ 54,976 ኩንታል ሲሚንቶ- በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት 14,094 ኩንታል ሲሚንቶ፣ እና 49,520 ሊትር ነዳጅ- በአማራ ክልላዊ መንግስት 1,914 ኩንታል እና 39,8505 ሊትር ነዳጅ- በሶማሌ ክልላዊ መንግስት 530 ኩንታል እና 12,560 ሊትር ነዳጅ- በደቡብ ምዕራብ 39,568 ሊትር ነዳጅ በድምሩ 71,514 ኩንታል ሲሚንቶ እና 500,153 ሊትር ነዳጅ በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር ተገኘቶ በህገ ወጥ አካላት ላይም አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡ በዚህ ህገ-ወጥ ድርጊት ላይ ተሳተፎ ባደረጉ አካላት ላይ ድርጅት የማሸግ እንዲሁም ምርት የመውረስ … [Read more...] about ባለፉት ሦስት ወራት የተያዘ ህገ ወጥ ሲሚንቶና ነዳጅ
መንግሥት መሠረተ ቢስ ውንጀላዎችን ፈጽሞ እንደማይታገስ አስታወቀ
”የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ኢትዮጵያ ላይ ጫና ማሳደር የተቋቋመ ስብስብ ነው” ሲሉ አምባሳደር ታዬ ኃላፊነት የጎደላቸው አካላት ለአደገኛ የፖለቲካ አጀንዳ ሲባል እየፈጠሯቸው የሚገኙ መሠረተ ቢስ ውንጀላዎችን ኢትዮጵያ ታወግዛለችበምዕራባውያን የተለያዩ አካላት አማካኝነት በኢትዮጵያ ላይ የሚነዙ የሐሰት ስም ማጥፋቶችን የኢትዮጵያ መንግሥት ፈጽሞ አይታገሥም። እነዚህ አካላት ኢትዮጵያ ውስጥ የከፉ ወንጀሎች ሊፈጸሙ ይችላሉ በሚል የሕወሐትን ጊዜ ያለፈበት ፕሮፓጋንዳ እንደ በቀቀንመድገማቸው አሳፋሪ ነው። እነዚህ አካላት የሚከሱት ፍንጮችን ወይም ተጨባጭ ክስተቶችን መሠረት አድርገውአይደለም፤ የመፈጸም ዕድል አለ በሚል ያልተጨበጠ ግምት እንጂ። እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ የተሻለ ስም ያላቸው ተቋማት ሳይቀሩ ይሄንን በኢትዮጵያ ላይ ተቀነባብሮ የሚለቀቅ ፕሮፓጋንዳ ለመቃወም … [Read more...] about መንግሥት መሠረተ ቢስ ውንጀላዎችን ፈጽሞ እንደማይታገስ አስታወቀ
የትህነግ ታጣቂዎችና የጦር አመራሮች የጅምላ መቃብር ስፍራ የተገኘ
በመከላከያ ሰራዊት መስዋዕትነት ከህወሓት እየተላቀቁ በሚገኙት አካባቢዎች የአሸባሪው ህወሓት ድብቅ ገመና መጋለጡን ቀጥሏል። የሽብር ቡድኑ ቁንጮ አመራሮች አስገድደው በጦርነት ላሰለፏቸው ታጣቂዎች እንኳ ምንም አይነት ርህራሄ እንደሌላቸው በጨርጨር የተገኘው ጅምላ መቃብር ለዚህ ማሳያ ነው፡፡ ከጨርጨር ከተማ በስተምስራቅ በኩል በሺዎች የሚቆጠሩ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎችና የጦር አመራሮች የጅምላ መቃብር ስፍራ የተገኘ ሲሆን፥ ይህም የሽብር ቡድኑ ቁንጮ አመራሮች በትግራይ ህዝብ ደም በስልጣን ለመቆየት የማይፈነቅሉት ድንጋይ እንደሌለ ማሳያ ሆኗል፡፡ የጅምላ መቃብር ስፍራው መለያ ኮድ ያለውና በአንዳንዱ መቃብር ከ3 እስከ 5 አስከሬን በጋራ የተቀበረበት ሲሆን፥ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎቹን የቀበራቸው እንደ ኃላፊነታቸው እና ማዕረግ ደረጃቸው በመቃብራቸው ላይ ምልክቶችን በማድረግ … [Read more...] about የትህነግ ታጣቂዎችና የጦር አመራሮች የጅምላ መቃብር ስፍራ የተገኘ










