”የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ኢትዮጵያ ላይ ጫና ማሳደር የተቋቋመ ስብስብ ነው” ሲሉ አምባሳደር ታዬ
ኃላፊነት የጎደላቸው አካላት ለአደገኛ የፖለቲካ አጀንዳ ሲባል እየፈጠሯቸው የሚገኙ መሠረተ ቢስ ውንጀላዎችን ኢትዮጵያ ታወግዛለችበምዕራባውያን የተለያዩ አካላት አማካኝነት በኢትዮጵያ ላይ የሚነዙ የሐሰት ስም ማጥፋቶችን የኢትዮጵያ መንግሥት ፈጽሞ አይታገሥም።
እነዚህ አካላት ኢትዮጵያ ውስጥ የከፉ ወንጀሎች ሊፈጸሙ ይችላሉ በሚል የሕወሐትን ጊዜ ያለፈበት ፕሮፓጋንዳ እንደ በቀቀንመድገማቸው አሳፋሪ ነው።
እነዚህ አካላት የሚከሱት ፍንጮችን ወይም ተጨባጭ ክስተቶችን መሠረት አድርገውአይደለም፤ የመፈጸም ዕድል አለ በሚል ያልተጨበጠ ግምት እንጂ።
እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ የተሻለ ስም ያላቸው ተቋማት ሳይቀሩ ይሄንን በኢትዮጵያ ላይ ተቀነባብሮ የሚለቀቅ ፕሮፓጋንዳ ለመቃወም አለመቻላቸው ነው።
ጥቂቶቹም ስለ ኢትዮጵያ የተነገረውን ስምማጥፋት በማመን ሳይሞኙ እንዳልቀሩ ይገመታል። አንዳንዶችም እነዚህን የሐሰት ክሶች ኢትዮጽያን ለማንበርከክ ሊጠቀሙባቸው ይፈልጋሉ።
ይሄን መሰል አስደንጋጭ ክሶችን አቅርቦ የኢትዮጵያ መንግሥትን በማስጨነቅ በሕወሐት ላይ እየወሰደ ያለውን የመከላከል ርምጃ ለማስቀየስ የሚችሉ መስሏቸው ከሆነ ተሳስተዋል።
አንዳንዶችም የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ ይህንን ቡድን ለማዳን እየተረባረቡ ነው። አንዳንድ ምዕራባውያን ባለ ሥልጣናት ጭምር ይሄንን የሐሰት ክስ የሚነዙት ኢትዮጵያ ትእዛዛቸውን አልቀበል ስላለቻቸው መሆኑን በይፋ መናገር ጀምረዋል። ይህ ጊዜ አመጣሽ የሐሰት ክስ መሬት ላይ ያለውን እውነታ ጨርሶ አይቀይረውም።
እነዚህ ጉምቱ ተቋማትና ወሳኝ ተዋንያን፣ በቂ ግንዛቤ ሳይኖራቸው በዚህ የሃሰት ዘመቻ እየተሳተፉ ይገኛሉ። ይሄን የመሰሉ የከፉና ሊወገዙ የሚገባቸው ውንጀላዎች ለፖለቲካ ዓላማ መዋላቸው ኃላፊነት የጎደለውና አሳፋሪ ነው በማለት መንግሥት አስታውቋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ኢትዮጵያ ላይ ጫና ማሳደር ያስችላል በሚል የፖለቲካ ስሌት የተቋቋመ ስብስብ ነው” ሲሉ በተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ገለጹ።
“አንዳንድ አካላት በፖለቲካዊ ጫና እሳቤ በኢትዮጵያ የዳርፉር አይነት ታሪክ መፍጠር እንደሚፈልጉ በግልጽ በመናገር ላይ ናቸው” ብለዋል አምባሳደር ታዬ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
የኮሚሽኑ ሪፖርቶች ኢትዮጵያ ላይ ጨምሮ ለሌሎች የአፍሪካ አገራት ከፈጠራ ታሪክነት የዘለለ ትርጉም እንደሌላቸው አመልክተዋል።
ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ኢትዮጵያ ላይ የበረታ ጫና ማሳደር ያስችላል በሚል የፖለቲካ ስሌት የተቋቋመ ስብስብ እንደሆነ በግልጽ አሳይቷል ነው ያሉት ቋሚ መልዕክተኛው።
የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት በመስከረም ወር 2015 ዓ.ም ባደረገው 51ኛ መደበኛ ስብሰባ የኮሚሽኑን የቆይታ ጊዜ በአንድ ዓመት ያራዘመ ቢሆንም ኢትዮጵያ የውሳኔ ሀሳቡን እንደማትቀበልና እንደምትቃወም መግለጿ ይታወቃል።
በቅርቡ ኢትዮጵያን አስመልክቶ ያወጣውን የሰብአዊ መብት ሪፖርት መንግስት እንደማይቀበለው ማሳወቁም የሚታወስ ነው።
ሪፖርቱ ከደረጃ በታች የሆነ፣ ሙያዊ ይዘት የጎደለውና ግድ የለሽነት የተሞላበት መሆኑን ገልጸዋል።
የኮሚሽኑ ሪፖርት በሰብአዊ መብት ሽፋን ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን የማስፈጸም ተልዕኮ ያለው መሆኑንም መንግስት ለሪፖርቱ በሰጠው ምላሽ መግለጹ የሚታወስ ነው። (ዋልታ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply