
በአዳማ ከተማ ከ300 ሺህ ዶላር በላይ ወደ ውጭ ሃገር ለማስወጣት የሞከረ አሽከርካሪ መያዙን የከተማዋ ፖሊስ መመሪያ አስታወቀ። አሽከርካሪው የተያዘው ኮድ 3/89158 ኢ.ት በሆነ ሎቤድ መኪና ገንዘቡን ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ በስውር ደብቆ ሲያጓጉዝ ነው።
በአዳማ ከተማ ዳቤ ክፍለ ከተማ ዳቤ ሶሎቄ ልዩ ቦታው ኬላ ፍተሻ ላይ የተያዘው የገንዘብ መጠንም 302ሺህ 400 የአሜሪካን ዶላር መሆኑን 2015የመመሪያው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ምክትል እንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ገልጸዋል።
በብሔራዊ ደህንነትና በአዳማ ከተማ የፀጥታ ሃይሎች ትብብር በ23/2/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ላይ የተያዘው ይሄ ገንዘብ ወደ ውጭ ሃገር በሚጓዝ የኮንቴይነር ጭነት ስር በስውር ቦታ ተደብቆ መሆኑንና አሽከርካሪውም በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ነው ያስረዱት። (Tikvah)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
እንደዚህ አይነቱን በስቅላት መቅጣት ነበር
ይሄ ወንጀል ሁኖ በስቅላት ከቀጣህ የሚተርፍ ከንቲባና ሚኒስቴር ላይኖረን ነው።በነ አቦይ ስብሀት እስከ 45ቢሊዮን ዶላር ተሻግሯል ነው የሚባለው ስንቱን ትግሬ ልትሰቅል ነው።
ዶላር ከኢትዮጵያ ማውጣት አይደለም ወጥቶ በዉጭ የተከመረው እራሱ ተጭኖ ወደ ኢትዮጵያ መመለሱ አይቀርም!!