የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ለሚተገበሩት ሶስት ፕሮጀክትች የሚውል የ907 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ዛሬ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ስምምነት ተፈራርሟል። ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና ዓለም ባንክ ግሩፕ ምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሚ/ር ዲዮን ነው የተፈራረሙት። የገንዘብ ድጋፉ በኢትዮጵያ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ፤ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎትን አሰጣጥንና ተደራሽነትን ለማሳደግ እንዲሁም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ የሚውል ነው ተብሏል። የመጀመሪያው የ200 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት በኢትዮጵያ ውስጥ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የሚውል ነው። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ክፉኛ የተጎዱ እንተርፕራይይች አዋጭ በሆነ መንግድ እንዲቀጥሉና በንግድ ውስጥ እንዲቆዩ ለማድረግ … [Read more...] about የዓለም ባንክ የ907 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለኢትዮጵያ አደረገ
Ethiopia
ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው
የኢትጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖኖሊጂ ኢንስቲትዩት ድሮኖችን ለማምረት ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲሁም ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን ወደ ስራ ለመግባት ስምምነት ላይ መደረሱም ተነግሯል፡፡የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር የሽሩን አለማየሁ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ አገሪቱ በራሷ አቅም ድሮኖችን ማምረት የሚያስችል ስራዎች ተጀምረዋል ነዉ ያሉት፡፡ (ምንጭ Tikvah) … [Read more...] about ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው
በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ
ባሳለፍነው ታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ የገቢና ወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል። በታህሳስ ወር በተካሄደው ቅንጅታዊ የኮንትሮባንድ መከላከል ስራ ግምታዊ ዋጋቸው ብር 274 ነጥብ 8 ሚሊየን የሆኑ የገቢ ኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ህገወጥ ገንዘቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል። በሌላ በኩል ከ70 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ ወጪ የኮንትሮባንድ አይነቶች መያዛቸውን በታህሳስ ወር የኮንትሮባንድ መካከል ስራዎች ሪፖርት ተመላክቷል። በአጠቃላይ በወሩ ብር 344 ነጥብ 8 ሚሊየን የሚያወጡ ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተይዘዋል። በገቢ ኮንትሮባንድ የተያዙት ዕቃዎች በተለይም በጅጅጋ፣ በሀዋሳ፣ በድሬዳዋ፣ በሞያሌና ኮምቦልቻ ቀዳሚውዎቹን ስፍራዎች የሚይዙ … [Read more...] about በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ
መንግሥት ከዜጎች የተግባር ድጋፍ ጠየቀ
ባለፉት 29ዓመታት ከተቃዋሚ ፓርቲዎችም ሆነ ከሲቪክና ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተሰምቶ በማያውቅ በሚያስብል ቁመና እና ክብደት፤ ወደፊት በታሪክ በሚጠቀስ መልኩ የዜጎችን የተግባር ድጋፍ የሚጠይቅ መግለጫ ከመንግሥት ተሰምቷል። የመግለጫው ሙሉ ቃል እንዲህ ይነበባል፤ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከመንግሥት የተሰጠ መግለጫ የኢትዮጵያ ህዝቦች ከሁለት ዓመታት በፊት ግንባራቸውን ለጥይት፣ ደረታቸውን ለጦር ሰጥተው አደባባይ የወጡት የይስሙላ ፌዴራሊዝም ወገባቸውን አጉብጦት፣ ተስፋቸውን አጨልሞት ነው። ጥቂቶች ዜጎችን እያፈኑና እነርሱ እየከበሩ መምጣታቸው ቁጣቸውን አገዘፈው። ኢትዮጵያዊያን አገራቸው ሆና ለማየት ከሚያልሙት እጅግ እየራቀ መምጣት የቁጣቸውን ኃይል አገዘፈው። እውነተኛ የፌዴራል ስርዓትን ለመተግበር ጉዞ ከመጀመሩ በፊት ዜጎች በጋራ የሚሳተፉበትና ተጠቃሚ የሚሆኑበት … [Read more...] about መንግሥት ከዜጎች የተግባር ድጋፍ ጠየቀ
የጆካ ዳኞች ባህላዊ የዳኝነት ሥነ-ሥርዓት
ቒጫ የጉራግኛ ቃል ሲሆን ጥሬ ትርጉሙም ደንብ፣ ስርዓት፣ ህግ ማለት ነው፡፡ የጉራጌ ህዝብ ባህላዊ ስርዓት ህግ ራሱን በራሱ መገልገል የጀመረው በስሙ እየተጠራ ባለበት ሀገር ከሰፈረበት ዘመን ጀምሮ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ይሁን እንጂ ህብረተሰቡ በየክፍሉ የሸንጎ ማእከላት በክፍለ ህዘብ ምድብ ባለበት ሁሉ የስሙ አሰያየሙ ይለያያል፡፡ መደበኛ ህግ ክፍሎች አሉት፡፡ የፍትሃብሄር፣ ወንጀለኛና የቤተሰብ (የጋብቻ) ስነስርዓት (ህግጋት) በውስጡ ይዟል፡፡ ይኽውም፡- የአንቂት ቒጫ - ይህ ደንብ በአጠቃላይ የጋብቻና የፍቺ ስነስርዓት የተደነገገበት ሲሆን የአተጫጨት፣ የቸግ ወይም የኒካ የሰርግ እና ፍቺ አፈጻጸም የሚዳኝበት ስርዓት (ደንብ) ነው፡፡የቅየ ቒጫ - ይህ ደንብ በሁለት ወሰንተኞች መካከል የድንበር መገፋፋት እንዳይኖር በሁለት ወገኞች ስምምነት በሚመረጡ ሽማግሌዎች አማካይነት … [Read more...] about የጆካ ዳኞች ባህላዊ የዳኝነት ሥነ-ሥርዓት
የኢሬቻ በዓልን ለመረበሽ የተዘጋጁ 503 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
መስከረም 23 እና 24 የሚከበረውን የኢሬቻ በአል ለመበጥበጥ የተዘጋጁ 503 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ መሳሪያም ተገኝቶባቸዋል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ኮማንደር አራርሳ መርዳሳ ትላንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት፤ የኢሬቻ በዓል ላይ የሚሳተፉ የበዓሉ ታዳሚዎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ኮሚሽኑ በጥብቅ እየሰራ ነው። የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት በተለያየ አቅጣጫ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሀይሎች እንዳሉና ኮሚሽኑም እንደደረሰባቸው የገለፁት ኮማንደሩ፤ እስካሁን ድረስ 503 ሰዎች፣14 ክላሽ ፣ 26 ቦምብ እና 103 ሽጉጦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡ ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የኢሬቻ በዓል በኮረና ምክንያት እንደ ከዚህ ቀደሙ በርከት ባለ ሰው የማይከበር ሲሆን በገዳ … [Read more...] about የኢሬቻ በዓልን ለመረበሽ የተዘጋጁ 503 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ400 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ400 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ማፅደቁን የገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል። የገንዘብ ድጋፉ በኢትዮጵያ የከተማ የሴፍቲ ኔት ፕሮጀክትን ለመደገፍ ይውላል ተብሏል። ከድጋፉ ውስጥ 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላሩ ስደተኞች ለሚገኙበት አካባቢና እና በኢትዮጵያ ለሚኖሩ ስደተኞች የስራ እድል ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ነው የገንዘብ ሚነስቴር በትዊተር ገፁ ያስታወቀው። ከዚህ በፊት የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ገንዘብ አገደ፤ ከለከለ እየተባለ በተለያየ ሚዲያ ሲወራ ቆይቷል። ይህ ባንኩ የፈቀደው ገንዘብ ኢትዮጵያ ከባንኩ የምታገኘው ሁሉንም የሚጠቀልል ባይሆንም ባንኩ ከኢትዮጵያ ጋር የገባው ውዝግብ እንደሌለውና ቀሪውንም ገንዘብ በወቅቱ እንደሚፈቅድ ጠቋሚ ነው ተብሏል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ400 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ
ከመስከረም 25 በኋላ “መንግሥት የለም” በሚል ትርምስ ለመፍጠር በሚሰሩ አካላት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ – የፌዴራል ፖሊስ
የፌዴራል ፖሊስ ጥብቅ ፍተሻ እያደረገ ያለው ከአማራ ክልል በሚመጡ መንገደኞች ብቻ ሳይሆን ወደ መዲናዋ በሚያስገቡ በሁሉም በሮች ላይ ተመሳሳይ የቁጥጥር ስራ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በአልን ምክኒያት በማድረግ በአዲስ አበባ የሽብር ድርጊት ለመፈጸም እና ይህንኑ ተከትሎ ሁከት እና ግጭት እንዲፈጠር በዝግጅት ላይ የሚገኙ አካላት እንዳሉ ደርሰንበታል ያሉት ኮሚሽነር ጄኔራሉ መረጃውን መሰረት በማድረግ ወደ አዲስ አበባ በሚያስገቡ በሁሉም በሮች ላይ ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል ። የበዓሉን እንቅስቃሴ ለማደፍረስ ዕቅድ ያላቸው ሀይሎች እንዳሉ ፖሊስ በምርመራ እንደደረሰበት ጠቁመው፤ እነዚህ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቀቆጠቡ አሳስበዋል። ከመስከረም … [Read more...] about ከመስከረም 25 በኋላ “መንግሥት የለም” በሚል ትርምስ ለመፍጠር በሚሰሩ አካላት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ – የፌዴራል ፖሊስ
ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ!
የጦር መሳሪያ ጨምሮ ሌሎች ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በዚህም፡- 18 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው ደረቅ ጫት፣ እህል፣ ትምባሆ እና ሌሎች ዕቃዎች በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ እና መቅረጫ ጣቢያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ 13 ሚሊዮን በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለውና 8,980 ኪ.ግ መጠን እንዳለው የተገለጸው ደረቅ ጫት በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ሲጓጓዝ የተያዘ ነው፡፡ ከሱማሌላንድ ወደ ጅጅጋ ሊገቡ የነበሩ ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች እንዲሁም በቀብሪበያህ በኩል በኤፌሳር እና ሚኒባስ ተጭኖ ሊገባ የነበረ የውጭ ሀገር ማሽላ እና ዘይት 3,500,000 ብር አጠቃላይ ግምታዊ ዋጋቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡በኢትዮጵያ ለሚገኙ ለደቡብ ሱዳን … [Read more...] about ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ!
በቦሌ በኩል አሮጌው ብር እየገባ ነው፤ በበረራ ሠራተኞችና መንገደኞች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ተጠየቀ
“ህወሓት ወደ አገር በሚገቡ መንገደኞች ገንዘብ ለማስገባት እየጣረ ነው” በሚል ርዕስ አንድ ዘገባ ካወጣን በኋላ ዛጎል “በአሜሪካ “ገንዘብ – ውሰዱልን” የቅርብ ወዳጆችን ግንኙነት በጠሰ” በሚል ርዕስ የሚከተለውን ዘገባ ለንባብ አብቅቷል። አሁንም የኢትዮጵያን መንግሥት ለማሳሰብ የምንፈልገው ይህንን የተቀናጀ ሥራ እያከናወኑ ያሉት ህወሓቶች መሆናቸውን ነው። ከዚህ ሌላ በተለያዩ የኢትዮጵያ ድንበር ኬላዎች ከጎረቤት አገር ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ ይገባል ከሚለው እሳቤ በተጨማሪ በቦሌ በኩልም እየገባ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባዋል። ስለዚህ በቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮጵላን ማረፊያ በተጓዦች በተለይም በበረራ ሠራተኞች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ሊደረግ ይገባል እንላለን። በአሜሪካ “ገንዘብ – ውሰዱልን” የቅርብ ወዳጆችን ግንኙነት በጠሰ “እንዴት ብትንቁን ነው” ሲል ባለቤት ቁጣ የተሞላ ምላሽ … [Read more...] about በቦሌ በኩል አሮጌው ብር እየገባ ነው፤ በበረራ ሠራተኞችና መንገደኞች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ተጠየቀ