ሩስያ የክፉ ቀን ወዳጄ ላለቻት ኤርትራ ድሮኖችን በድጋፍ የሰጠችው ለቀጠናው ሰላም ኤርትራ ወሳኝ ሃገር በመሆኗ እና ሩስያ ቀጣይ በኤርትራ ከምጽዋ 40 ኪ/ሜ ርቅት ላይ በኣፍኣቤት ለምትገነባው የጦር ሰፈር እንደ መጀመርያ ግብአትነት በመቁጠር ነው። የድሮን ድጋፉ የተሰጣት ኤርትራ ለአለፉት 3 ወራት በሩስያ ስልጠና የተሰጣቸውን 26 የድሮን ባለሙያዎቿን ጭምር አቀባበል በማድረግ ዛሬ በባፃ የድሮን ጣብያ በድምቀት ተቀብላለች። በዚህ ርክክብ ወቅት የተገኙት የኤርትራው ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአደረጉት ንግግር "ይህ ከሩስያ የተደረገልን ድጋፍ የኤርትራን የጦር ኃይል በጥራት፣ በልምድ፣ በእውቀትና በታጠቀው የጦር መሳርያ በምስራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪ ያደርገዋል" ሲሉ ተደምጠዋል። ባለፈው ወር የኤርትራው ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ኦስማን ሳሌህ ሩሲያን በጎበኙት ወቅት የሩሲያው ውጭጉዳይ … [Read more...] about ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች
drones
ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው
የኢትጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖኖሊጂ ኢንስቲትዩት ድሮኖችን ለማምረት ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲሁም ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን ወደ ስራ ለመግባት ስምምነት ላይ መደረሱም ተነግሯል፡፡የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር የሽሩን አለማየሁ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ አገሪቱ በራሷ አቅም ድሮኖችን ማምረት የሚያስችል ስራዎች ተጀምረዋል ነዉ ያሉት፡፡ (ምንጭ Tikvah) … [Read more...] about ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው