
ሩስያ የክፉ ቀን ወዳጄ ላለቻት ኤርትራ ድሮኖችን በድጋፍ የሰጠችው ለቀጠናው ሰላም ኤርትራ ወሳኝ ሃገር በመሆኗ እና ሩስያ ቀጣይ በኤርትራ ከምጽዋ 40 ኪ/ሜ ርቅት ላይ በኣፍኣቤት ለምትገነባው የጦር ሰፈር እንደ መጀመርያ ግብአትነት በመቁጠር ነው።
የድሮን ድጋፉ የተሰጣት ኤርትራ ለአለፉት 3 ወራት በሩስያ ስልጠና የተሰጣቸውን 26 የድሮን ባለሙያዎቿን ጭምር አቀባበል በማድረግ ዛሬ በባፃ የድሮን ጣብያ በድምቀት ተቀብላለች።
በዚህ ርክክብ ወቅት የተገኙት የኤርትራው ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአደረጉት ንግግር “ይህ ከሩስያ የተደረገልን ድጋፍ የኤርትራን የጦር ኃይል በጥራት፣ በልምድ፣ በእውቀትና በታጠቀው የጦር መሳርያ በምስራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪ ያደርገዋል” ሲሉ ተደምጠዋል።
ባለፈው ወር የኤርትራው ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ኦስማን ሳሌህ ሩሲያን በጎበኙት ወቅት የሩሲያው ውጭጉዳይ ሚ/ር ሰርጊዬ ላቭሮቭ “ከኤርትራ ጋር ያለን የሁሉም መስክ ግንኙነት የጠበቀ ነው” ማለታቸውና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታስ የዜና ወኪል መዘገቡ ታወሳል።
“ዛላ ኬ.ዋይ.ቢ” የሩሲያ ድሮን ምን የተለየ ያደርገዋል?
የሶስት ማዕዘን ቅርፅ ያለው ድሮን ተልእኮውን በሚስጥር ጥቃት መፈፀም የሚችል ሲሆን፤ ለዚህም ይመስላል “ገዳዩ” አሊያም “አጥፈቶ ጠፊው” ድሮን የሚል መጠሪያ የተሰጠው።
የድሮኑ የክንፉ ርዝመት ከጫፍ እስከ ጫፍ 1 ነጥብ 21 ሜትር ስፋ ያለው ሲሆን፤ ሽንጡ ደግሞ 0.95 ሜትር እንዲሁም ቁመቱ 0.165 ሜትር መሆኑ ይነገራል።
አነስተኛ መጠን ያለው ድሮኑ የኤሌክትሪክ ሞተር የተገጠመለት ድሮኑ በሰዓት ከ80 እስከ 130 ኪሎ ሜትር መብበር እንደሚችልም ይነገራል።
የአንድ ጊዜ የአየር ላይ ቆይታው እስከ 30 ደቂቃ ነው የተባለለት ዶሮኑ፤ እስከ 40 ኪ.ሜ ርቀት ድረስ በውኃ ላይም ይሁን በምድር ላይ የሚገኝ ኢላማን በቀላሉ መምታት ይችላል። (Eritrea Press Agency Amharic)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply