• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

መንግሥት ከዜጎች የተግባር ድጋፍ ጠየቀ

November 5, 2020 03:09 pm by Editor 1 Comment

ባለፉት 29ዓመታት ከተቃዋሚ ፓርቲዎችም ሆነ ከሲቪክና ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተሰምቶ በማያውቅ በሚያስብል ቁመና እና ክብደት፤ ወደፊት በታሪክ በሚጠቀስ መልኩ የዜጎችን የተግባር ድጋፍ የሚጠይቅ መግለጫ ከመንግሥት ተሰምቷል።

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንዲህ ይነበባል፤

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከመንግሥት የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ህዝቦች ከሁለት ዓመታት በፊት ግንባራቸውን ለጥይት፣ ደረታቸውን ለጦር ሰጥተው አደባባይ የወጡት የይስሙላ ፌዴራሊዝም ወገባቸውን አጉብጦት፣ ተስፋቸውን አጨልሞት ነው። ጥቂቶች ዜጎችን እያፈኑና እነርሱ እየከበሩ መምጣታቸው ቁጣቸውን አገዘፈው። ኢትዮጵያዊያን አገራቸው ሆና ለማየት ከሚያልሙት እጅግ እየራቀ መምጣት የቁጣቸውን ኃይል አገዘፈው።

እውነተኛ የፌዴራል ስርዓትን ለመተግበር ጉዞ ከመጀመሩ በፊት ዜጎች በጋራ የሚሳተፉበትና ተጠቃሚ የሚሆኑበት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መሰረቶች ተግባር የራቃቸው የቃል ተረቶች ሆነው መቆየታቸውም የቁጣቸውን ኃይል ከፍ አድርጎታል። ኢህአዴግ በፌዴራሊዝም ካባ ሲንቀሳቀስ ዜጎች በአገራቸው ቀርቶ በራሳቸው ጉዳይ እንኳን መወሰን የሚችሉበትን እድል ተነፍጓቸው ቆይቷል። በዚህም በግንባር ታጥረው፣ በአጋርነት ተገድበው ዓመታትን በቁዘማ አሳልፈዋል።

ለዚህም ነው የህዝብ ብሶት ገንፍሎ፣ በራሱ በኢህአዴግ ውስጥ የለውጥ ፍላጎት ተቀጣጥሎ ከተፈጠረው ለውጥ ማግስት ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በራሳቸውም፣ በአገራቸውም ጉዳይ ተሳታፊና ወሳኝ የሚሆኑበት እውነተኛ ፌዴራሊዝምና ዴሞክራሲ ብርሃን መፈንጠቅ የቻለው።

ይሁን እንጂ ይህን የብርሃን ፍንጣቂ ለዜጎች የብልጽግና መስመርን ሲያመላክት፣ በቃል በታጠረው የኢህአዴግ ፌዴራሊዝም ስም ሲዘርፍ፣ ሲገርፍና ሲገድል የነበረው የህወሃት የጥፋት ቡድን ከሌብነትና ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ተግባሩ ገድቦታል። በህዝብ ሞትና እንግልት የመክበርና የራስ ጥቅምን የማስቀጠል ጉዞንም ዘግቶበታል። ይህ የጥፋት ኃይል ከለውጡ ጋር ተጣጥሞ መጓዝ ባለመቻሉ ራሱን ከለውጡ ጉዞ በማውጣት የቀድሞ የበላይነቱን፣ የዘረፋና የአፈና ሥርዓቱን ለማስቀጠል የሞት ሽረት ትግሉን ሲያካሂድ ቆይቷል፤ እያደረገም ይገኛል።

የተከበራችሁ የአገራችን ህዝቦች

በህውሃት ስም የሚንቀሳቀሰው የጥፋት ቡድን የራሱን የፖለቲካ አጀንዳ በማስቀደም አገርን ለከፋ አደጋ አጋልጧል። በተለይም ሕዝቡን በብሔር በማቧደን፣ እርስ በርሱ እንዳይተማመን በማድረግና በማጋጨት የአገር ሰላም እንዲጠፋ ምክንያት ሆኗል። በማንነት ስም ትልቁን የኢትዮጵያዊነት ምስል እንዲደበዝዝ ድብቅ ሴራ ሲያራምድ ቆይታል፤ እያደረገም ነው። ከአንድነት ይልቅ የብተና ፖለቲካ በማራመድ ህዝብን እርስ በርስ በማጋጨት ለግጭትና መፈናቀል ዳርጓል።

የአገራችን ህዝቦች ለዘመናት የናፈቁት ዴሞክራሲ እንዳይኖርና እንዳይገነባ አድርጓል። ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ለመጠቀም የሚንቀሳቀሱ ዜጎችም እስር፣ እንግልትና ወከባ ተፈጥሮባቸዋል፤ ግርፋትና የኢ-ሰብዓዊ የመብት ጥሰቶች ተዳርገዋል። ቆስለዋል፣ አካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ሞተዋል። ለዚህ ደግሞ በህወሃት ስም የሚንቀሳቀሰው የጥፋት ሃይል ዋነኛ ተጠያቂ መሆኑ ለአገራችን ሕዝቦች የተሰወረ ምስጢር አይደለም።

እንደእውነቱ የአገራችን ህዝቦች ለሰው ልጆች ያላቸው ክብር ዓለም የመሰከረለት ነው። ለዘመናት በታሪካቸው ማህደር ውስጥ የሰፈረው እውነት የሚያረጋግጠው እንግዳ ተቀባይነታቸውና ሰው አክባሪነታቸው፣ ለሰው ልጆች ህይወት ትልቅ ትርጉም የሚሰጡ መሆናቸውን ነው። ይህን ዓለም ያደነቀውን ታላቅ እሴት አክብረውና ጠብቀው ለመኖር ሌት ተቀን የሚታትሩ ህዝቦችም ናቸው።

ለዚህም ነው ዓለምአቀፍ የሰብዓዊነት ድንጋጌዎችን አክብረውና ተቀብለው የሕገ መንግስቱ የማዕዘን ድንጋይ ያደረጉት። እነዚህን ድንጋጌዎች በማክበርና በመጠበቅ ግን ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በርካታ ተግዳሮቶች ገጥሟቸዋል።

የአገሪቱን ህገ መንግስት፣ ዓለም አቀፋዊ የሰብዓዊ መብት ህግጋቶችን የጣሱ ድርጊቶች የህወሃት የጥፋት ቡድን ሲፈጸም ቆይቷል። በህግ ጥላ ስር የነበሩ ዜጎች ተገቢውን ፍርድ ከማግኘት ይልቅ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ሲፈጽምባቸው ቆይተዋል። በጥብቅ ምስጢር ባደራጃቸው የራሱ ቡድኖች አማካኝነት ግፍ ተፈጽሞባቸዋል።

እነዚህ የሰብዓዊነት ሽታ የሌላቸው የህወሃት የጥፋት ቡድን ከራሳቸው ውጭ የሚያዳምጡት ምንም ጩኽት ባለመኖሩ ለዓመታት ከአገሪቷ የተለያዩ አካባቢዎች በሰቆቃ ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ቤት በሃዘን እንዲሞላ አድርገዋል።  ከልክ ያለፈው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቱ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ስሟ እንዲጠለሽ አድርጓታል።

ይሁን እንጂ የለውጡ መንግስት ይህን አሳዛኝና አሳፋሪ ታሪክ ዳግም በኢትዮጵያ ምድር እንዳይመጣ ተግቶ እየሰራ በሚገኝበት በዚህ ወቅት መንግስትን በተለያዩ ጉዳዮች ውጥረት ውስጥ በመክተት ወደኋላ ለመጎተት ያለማቋርጥ ትንኮሳ እየፈጸመ ይገኛል።

የተከበራችሁ የአገራችን ህዝቦች

አገራችን በህዝቦቿ ጥረትና ታታሪነት እየገነባች የመጣችው ኢኮኖሚዋ ከዓመት ዓመት እያሽቆለቆለ መምጣቱን ከሁለት ዓመታት በፊት በነበረው ተጨባጭ ሁኔታ መረዳት ይቻላል። ችግሩ እየሰፋ ድህነቱ እየተባባሰ ዜጎች ከድጡ ወደ ማጡ እየገቡ መጥተው ከጫፍ ላይ ተደርሶ እንደነበር ያደባባይ ምስጢር ነው።

በርግጥ ከለውጡ በፊት እንደ ሀገር ተፈጥሮ ለነበረው የኢኮኖሚ መዋዠቅ በርካታ ምክንያቶች እንዳሉ ቢታመንም፤ ዋነኛው የህወሃት የጥፋት ቡድኑ አባላት የሀብት መቀራመት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። በተለይም  ለታላላቅ አገራዊ ፕሮጀክቶች እንደ ህዳሴ ግድብ፣ የምድር ባቡር፣ ስኳር ፕሮጀክቶችና ማዳበሪያ ፋብሪካዎች እንዲሁም ሜቴክን ለመሳሰሉ ተቋማት ማስፈፀሚያ የተመደበን የህዝብ ገንዘብ በህወኃት ስም የሚንቀሳቀሰው የሌቦች ቡድን ገንዘቡን በመከፋፈል ወደ ውጭ አገሮች በማሸሽ የተገለጠ ነው።

የአገራችን ሕዝቦች እንደሚያውቁት ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ መንገራገጭ ውስጥ በመግባቱ ለመንግስት ሰራተኞች እንኳ ወርሃዊ ደመወዝ መክፈል አዳጋች ሆኖ ነበር። ለሀገር ደህንነት እጅግ ወሳኝ የሆነውን ነዳጅና መድኃኒት እንኳ መግዣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዲያጋጥማት ሆኗል። ከሁሉም በላይ በሚያስደንቅና የዝርፊያውን ወሰን ማጣት በሚያመለክት ደረጃ ከውጭ አገራት ምርቶችን ወደ አገር ውስጥ የሚያሥገቡ ግዝፉ መርከቦች በዚሁ ቡድን አማካኝነት መሸጣቸው ለቡድኑ አባላት የነዋይ ፍቅር መስዋዕት መሆናቸውን መጥቀስ ይቻላል።

የተከበራችሁ የአገራችን ህዝቦች

ይሄን ሁሉ ጥፋት በአገራችን እና በዜጎቻችን ላይ ያደረሰው የህወሓት የጥፋት ቡድን በህዝቦች የለውጥ ሃይል ከተገፋ በኋላ መቀሌ መሽጎ ሌላ ጥፋት እየደገሰና እያደረሰ ይገኛል።

የፌዴራል መንግስት በሆደ ሰፊነት ህጋዊ አካሄድን በማስቀደም ሁኔታዎችን ለማስተካከል ጥረት ቢያደርግም የጥፋት ቡድኑ ከድርጊቱ ሊታቀብ አልቻለም። በተደጋጋሚ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የዜጎችን ህይወት በመቅጠፍ እብሪተኝነቱን በግላጭ አሳይቷል።

የህወሓት የጥፋት ቡድን ከመንግስት አሰራር ውጭ የምርጫ ኮሚሽን በማቋቋም፣ የማዕከላዊ መንግስት ትዕዛዞችን በመጣስ፣ የሰራዊቱን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ጭምር በማስተጓጎል አገራዊ ክህደቱን በተግባር አረጋግጧል።

ይህ የጥፋት ቡድን ከትናንት ወዲያ ምሽትም የአገራችንንና የአህጉራችን ኩራት የሆነው የመከላከያ ኃይላችን ላይ ተኩስ በመክፈት የመንግስትን ቀይ መስመር ጥሷል። የአገር ሉዓላዊነታችን በመዳፈር አፍሪካዊ ወንድሞቻችንን ጭምር አንገት ያስደፋ እኩይ ተግባር ፈፅሟል።

የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ምሁራን

መንግስት በአገራችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የምታበረክቱትን ፋይዳ በሚገባ ይገነዘባል። ቀደም ሲል እንደ ስጋት ይታይ የነበሩትን የአገራችንን ምሁራን በማቅረብ የአገሪቷ የለውጥ እንቅስቃሴ አጋዥ እንዲሆን ማድረግ ተችሏል።

እንደምትገነዘቡት በአሁኑ ወቅት ከሀዲው የህወሃት ቡድን የኩራታችንና የሉዓላዊነት ምንጭ የሆነውን የመከላከያ ሰራዊታችን ባልጠበቀው ሁኔታ በመክበብ ጥፋት ለማድረስ ጥረት አድርጓል። ይህ ቡድን አገራችንን ለማፈራረስ መቼም ቢሆን ወደኋላ እንደማይል በግልጽ አሳይቷል።

ስለሆነም የአገራችን ምሁራን የአገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ በሚደረገው ትግል ከመንግስት ጎን በመቆም አገርነታችሁን እንድታሳዩ መንግስት ጥሪ ያስተላልፋል።

የተከበራችሁ የመንግስት ሰራተኞች

የተከበራችሁ በተለየዩ ተቋማት የምትሰሩ የመንግስት ሰራተኞች የህወሓት የጥፋት ቡድን በመከላከያ ኃይላችን ላይ የፈጸመው እኩይ ተግባርን ተከትሎ መንግስት እየወሰደ ባለው እርምጃ በተለያየ መንገድ አጋርነታችሁን ስላሳያችሁ አክብሮታችን ላቅ ያለ ነው። አሁንም የእለት ተእለት ስራችሁን ሳታስተጓጉሉ በመከወን፣ የጥፋት ኃይሎችን ሴራም አከባቢያችሁን በንቃት በመጠበቅና በመከታተል ከከሀዲው የህወሃት ቡድን ሴራ አገራችንን ለመታደግ የተጀመረውን አገር የማዳን እንቅስቃሴ በመደገፍ ከመንግስት ጎን እንድትሰለፉ ጥሪ ያቀርባል።

የተከበራችሁ የፀጥታና ደህንነት ኃይሎች

ለአገራችሁ ሉዓላዊነት መከበርና ለህዝቦች ሰላም መስፈን የራሳችሁንና የቤተሰባችሁን ህይወት አሳልፋችሁ የሰጣችሁ የፀጥታና ደህንነት ኃይሎች እየከፈላችሁት ያለውን መስዋዕትነት መቼም የምንዘነጋው አይደለም። አሁንም ዜጎችን በመጠበቅና ከጥቃት በመከላከል በተለመደው ጀግንነታችሁ ለአገራችሁ የገባችሁትን ቃል እንደምትጠብቁ፤ የህወኃት ቡድን የማስወገድ ኦፕሬሽን እንደስካሁኑ ሁሉ በአስተማማኝ ድል እንደምትቋጩት ሕዝባችንና መንግስት በጽኑ ይተማመናሉ።

የተከበራችሁ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችና ሴቶች

የአገራችን ወጣቶችና ሴቶች የህወሓት የጥፋት ቡድን ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ከስደትና ከችግር ሳያላቅቃችሁ ይልቁንም በስማችሁ እየነገደ ኪሱን ሲያደልብ እንደኖረ መንግስት ይገነዘባል። መንግስት በዚህ የጥፋት ቡድን የተፈጠረውን ኢ-ፍትሃዊነት ለማስተካከል ጥረት ቢያደርግም በየጊዜው በየአቅጣጫው ቀድሞ ባደራጀቸው አጥፊ ቡድኖች የአገራችንን ሰላም ሲነሳ፤ ወጣቶችና ሴቶችንም የጥፋት ሰለባው ሲያደርግ በግልጽ ታይቷል።

አገራችንን ወደፊት ለማሻገር መንገድ ብንጀምርም ይህ የነፍሰ ገዳይ ቡድን የአገር መከላከያ ሰራዊታችን ላይ ተኩስ በመክፈትና የዘረፋ ሙከራ በማድረግ ኢትዮጵያን በግልጽ ለማፍረስ ተንቀሳቅሷል።

በመሆኑም አገራችን ያለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አገርን እንደ አገር የማስቀጠል መሆኑን በመረዳት ከመንግስታችሁ እና መከላከያ ጎን በመቆም የዜግነት ኃላፊነታችሁን እንደትወጡ መንግስት ጥሪ ያደርጋል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

ጥቅምት 26/2013 ዓ/ም

አዲስ አበባ

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Left Column, Politics Tagged With: Ethiopia, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Ck says

    November 6, 2020 11:28 am at 11:28 am

    ሶሻሊስቱ ደርግ በአንድ ማዕከላዊ ዕዝ ሥር ሰብስቦ ሲያስተዳድር የነበረውን የሀገር ሃብት በጠራራ ፀሐይና በጠፍ ጨረቃ ሲያግዙ፤ …ኢዲዲሲ ፈርሶ ጉና፤ ቡና ፈርሶ ወንዶ፤ ስኳር ፈርሶ ዲንሾ፤ጭማድ ፈርሶ ፋና፤ ሕንጻ ፈርሶ ሱር፤ኩራዝ ፈርሶ ዋልታ፤
    …ወዘተ ሲመሰረቱ፤እንዲያው ባጭሩ እርሻው፤ ማዕድኑ፤ ማምረቻው፤ ትራንስፖርቱ፤ ማከፋፈያው..ወዘተ ከሁሉም ኢትዮጲያዊ ዜጋ ባለቤትነት እጅ ወጥቶ በአንድ ቡድን ባለቤትነት እጅ ሲወደቅ እንዳላየና እንዳልሰማ አልፈናል፡፡

    አንድ የሃገር ሰራዊት ተበትኖ ለለማኝነት ሲዳረግና ከላስቲክ ቤቱ ተገፍቶ በረሃብና በበሽታ እንዲያልቅ ሲፈረድበት እያየን ዝም ብለናል፤ ወጣት ተማሪዎች በሚማሩበት ግቢ ውስጥ፤ ዜጎች በየመንደሩን በየስርቻው ያለጥፋታቸውና ያለዳኝነት ሲረሽኑና ታፍነው የደረሱበት ሲጠፋ ታዝበን አሁንም በዝምታና በለሆሳስ አልፈናል፡፡ ይሄ ሁሉ ገና ክጅምሩ ነው፤ የዛሬ ሰላሳ ዓምት ገደማ፡፡
    ለቀሩት ተከታታይ ሃያ ስምንት ዓመታት አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ የመናገር፤ የመሰብሰብ፤ በነጻ የመንቀሳቀስና ሰርቶ በሰላም የመኖር መብቱ ተገፎ ወንበዴዎቹ በስሙ ሲለምኑና ሲመጸወቱ፤ በስሙ ሲበደሩና በላዩ ላይ ሲደራደሩበት አሁንም በትዝብት አልፈናል፡፡ ዜጎች ያለፍላጎታቸው በተሰፈረላቸው የዘር ጣሳ ተገደው አንዲገቡና የጋራ ቋንቋ፤ የጋራ ባህል፤ የጋራ ህልም እንዳይኖራቸውና በዘመናት አብሮ መኖር ያካበቱት እሴት ጠፍቶ እርስ በርሳቸው እንዲገዳደሉ ሲገፉና በውጤቱ እነኚህ እኩዮች ሲስቁና ሲሳለቁ ታዝበናል፡፡
    የዋና ከተማችን አዲስ አበባ ማስተር ፕላን ፕሮጀክት areal photogrammetry data ገና በጠዋቱ ወደመቀሌ ተግዞ አዲስ አበባ ከመቀሌ ስትሸነሽን፤ ዜጎች ተወልደው ካደጉበት ጎጆ እንደባዕድ ሲባረሩና አዳዲስ በለቁምጣ ኢንቨስተሮች በፎቅ ሲተኳቸው ወይንም በላያቸው ላይ ንብረታቸው ተሸጦና ተለውጦ ባለቁምጣዎቹ በሃያ አራት ሰዓት ሚሊየነር ሲሆኑ ያየነውን እንዳላየ የሰማነውን እንዳልሰማ መስለን በዝምታና በለሆሳስ አልፈናል፡፡
    ሃይማኖት ረክሶ፤ ባህል ተበላሽቶ፤ ተው የሚል ሽማግሌ ጠፍቶ፤ ጉቦና ሌብነት እንደጥበብ፤ መግደል እንደጀብድ፤ መዋሸት እንደዕውቀት በሕግ ተሞግሰው፤ ሦስት አስርተ ዓምታት ተቀልዶብናል፡፡ በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች፤ የጠየቁ ምሁራን፤ ይህ ለምን ይሆናል ያሉ ተቆርቋሪ ዜጎች ሞተዋል፤ ታስረዋል፤ ተሰቃይተዋል፡፡ የስንት እናቶች ቆሽት እስክዛሬ እየነደድ እንደሆን ቤቱ ይቁጠረው፡፡
    የኢትዮጵያ ሕዝብ ምሬቱ በዝቶበትና ገንፍሎ ወግዱ ቢላቸው ከሃምሳ ዓመት በፊት ሴራ ሲጠነስሱ የነበሩበት ጉረኖአቸው ተመልሰው አሁንም ሰላም አየነሱን ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅር ባይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ መሃሪ ነው፡፡ እንደ መሃመድ ጋዳፊ በመጥረጊያ ሳይሸንቆሩ፤ አንደ ሳዳም ሁሴን በገመድ ሳይንጠነጠሉ፡ እንደ ሳሙኤል ዶ በቢላዋ ሳይዘለዘሉ፤ እንደ ቻርለስ ቴይለር ዘብጥያ ሳይወርዱ ወይንም እነሱ ከስልጣን ያስወገዷቸው ኮሎኔሎች ዕጣ ሳይደርሳቸው በክብር ተሽኝተው የሰርቁትን እየበሉ ለመኖር ቢፈቀድላቸው ጥጋባቸው ከልክ አልፎ ሰላም እየነሱን ይገኛሉ፡፡
    እነኚህ ከሃዲ አውሬዎች ከያሉበት ተለቅመው በጥፋታቸው ልክ ካልተቀጡ ኢትዮጵያ ሰላም አታገኝም፡፡ መንግስት የያዘውን እንዲገፋበትና መዥገሮቹን ከነሰንኮፋቸው እንዲነቅል ማበረታታት የሁላችንም የዜግነት ግዴታ ነው፡፡
    እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule