• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

5 ሚሊዮን “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት” ዘመቻ ተጀመረ

September 13, 2021 10:09 am by Editor Leave a Comment

ኢትዮጵያ የያዘችውን እውነታ ለዓለም የማስረዳትና የአሸባሪውን ህወሃት የጥፋት ድርጊት ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳየትን አላማ ያደረገው “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት” ዘመቻ በይፋ ተጀምሯል።

ዘመቻው ይፋ ሲደረግ ሚኒስትሮች፣ የተለያዩ ታዋቂ ግለሰቦችና በርካታ ወጣቶች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

“የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት” ዘመቻ ከዛሬ ጀምሮ አስከ መስከረም 15 ቀን 2014 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል።

“በኢትዮጵያ ላይ በተሳሳተ መልኩ የሚነዛው አሉባልታ ከእውነት የራቀ መሆኑን ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ለማሳየት በዘመቻው ይሰራል” ተብሏል።

በዚሁ ንቅናቄ ኢትዮጵያ የያዘችውን እውነታ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እንዲደርስ ይሰራል ተብሏል።

በዚህ ዘመቻ ከ5 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ኀይል በአማራና በአፋር ክልል የፈጸመውን ግፍ የሚያሳይ መልዕክት ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት የሚላክ መሆኑን የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ከአማራ ሚዲያ አዳሙ ሽባባው ዘግቧል።

የአሸባሪውን ሴራ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና ለፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለማሳወቅ የተዘጋጀው መልዕክት ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት የሚላክ መሆኑን የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አብርሃም አለኽኝ አስታውቀዋል።

አብርሃም አለኽኝ

አሸባሪውና ወራሪው ትህነግ የሀገርና ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን በመጣስ በገባበት ቦታ ሁሉ ምንም ዓይነት የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸውን ንጹሐን ዜጎች እየጨፈጨፈ ነው ብለዋል።

ጭፍጨፋውን ለማሳወቅ ደግሞ እንደ ሀገር 5 ሚሊዮን እንደ ክልል ደግሞ 500 ሺህ ወጣቶች የሚፈርሙበት ደብዳቤ ዛሬ የመፈረም ሥራ ተጀምሯል ነው ያሉት።

እንደ ኀላፊው ገለጻ “በአማራ ሕዝብ ላይ ሒሳብ አወራርዳለሁ” ብሎ አውጆ የተነሳው የሽብርተኛው የትህነግ ወራሪ ቡድን በአማራ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ዘረፋ፣ ግድያ፣ ማፈናቀልምና አስገድዶ መድፈር ተግባራትን ፈጽሟል፤ ዜጎች የሚገለገሉበትን የትምህርት፣ የጤና እና የሃይማኖት ተቋማትንም ዘርፏል፤ ከፍተኛ ውድመትም አድርሷል ብለዋል። አሸባሪ ቡድኑ በአፋር ሕዝብ ላይ ተመሳሳይ ግፍ መፈጸሙን ጠቅሰዋል።

ወደ ነጩ ቤተመንግሥት የሚላከው ደብዳቤም የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን የሠራውን ግፍ ማስረጃ የያዘ መሆኑን አቶ አብርሃም አስታውቀዋል።

ቡድኑ የሠራውን ግፍ እና ወንጀል የበለጸጉ ሀገራት፣ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እና ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በተሳሳተ መንገድ እየተረዱት ነው ብለዋል።

ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት የሚላከው ደብዳቤ ዓለም አቀፍ ብዙኃን መገናኛ ተቋማት ከተጎጂዎች ጎን እንዲቆሙ ጥሪ የሚቀርብበት፣ ወራሪው የፈጸማቸው ግፎች የሚጋለጡበት እንደሆነ ነው አቶ አብርሃም የገለጹት። “ተጽእኖ ፈጣሪ ሀገራት በሽብርተኛው ትህነግ መወረራችንን ሊያውቁ ይገባል” ያሉት አቶ አብርሃም አሸባሪው ትህነግ በወረራቸው የክልሉ አካባቢዎች ሁሉ የዜጎችን በሕይወት የመኖር መብት ጥሷል፤ የተሳሳተ መረጃ በመያዝ የጠላት የክህደት ፖለቲካ አራማጆች እየኾኑ ነው ብለዋል።

የግፉዓንን መልዕክት በያዘው ደብዳቤ ላይ ምሁራን፣ ወጣቶችን እና ሁሉም የክልሉ ነዋሪዎች በመፈረም ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት እንዲላክ መረባረብ እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ አብርሃም እንዳሉት በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘው ጦርነት ራሳችንን ለመከላከል የሚደረግ ነው፤ ጦርነቱ በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል፤ እናሽነፋለንም ብለዋል።

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ጋሻው ተቀባ እንዳስታወቀው ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት የሚላከው ደብዳቤ የፊርማ ሥነ ሥርዓት እስከ መስከረም 10 ይካሄዳል። መስከረም 15 ደግሞ ወደ አሜሪካ ይላካል ብሏል።

በሂደቱም በወረዳ ደረጃ እስከ 1 ሺህ 500፣ በዞን ደረጃ እስከ 2 ሺህ፣ በትልልቅ ከተሞች ደግሞ ከ50 ሺህ እስከ 100 ሺህ ሰዎች ይሳተፋሉ ነው ያለው። በዚህም ሽብርተኛው የትህነግ ወራሪ ቡድን የፈጸመውን ግፍ እና ወንጀል ያልተረዳው የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲገነዘብ የሚደረግበት ነው ብሏል። ይህም ዜጎች በትዊተር የሚያደርጉትን ዘመቻ የሚያጠናክር እንደሆነም ኀላፊው ገልጿል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: Ethiopia, ethiopian terrorists, joe biden, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule