ቒጫ የጉራግኛ ቃል ሲሆን ጥሬ ትርጉሙም ደንብ፣ ስርዓት፣ ህግ ማለት ነው፡፡ የጉራጌ ህዝብ ባህላዊ ስርዓት ህግ ራሱን በራሱ መገልገል የጀመረው በስሙ እየተጠራ ባለበት ሀገር ከሰፈረበት ዘመን ጀምሮ እንደሆነ ይነገራል፡፡
ይሁን እንጂ ህብረተሰቡ በየክፍሉ የሸንጎ ማእከላት በክፍለ ህዘብ ምድብ ባለበት ሁሉ የስሙ አሰያየሙ ይለያያል፡፡ መደበኛ ህግ ክፍሎች አሉት፡፡ የፍትሃብሄር፣ ወንጀለኛና የቤተሰብ (የጋብቻ) ስነስርዓት (ህግጋት) በውስጡ ይዟል፡፡
ይኽውም፡-
- የአንቂት ቒጫ – ይህ ደንብ በአጠቃላይ የጋብቻና የፍቺ ስነስርዓት የተደነገገበት ሲሆን የአተጫጨት፣ የቸግ ወይም የኒካ የሰርግ እና ፍቺ አፈጻጸም የሚዳኝበት ስርዓት (ደንብ) ነው፡፡
- የቅየ ቒጫ – ይህ ደንብ በሁለት ወሰንተኞች መካከል የድንበር መገፋፋት እንዳይኖር በሁለት ወገኞች ስምምነት በሚመረጡ ሽማግሌዎች አማካይነት በቃለመሃላ (ጉርዳ) የድንበር ድንጋይ የሚተከልበትና ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ግጭቶች የሚፈታበት አሰራር ደንብ ነው፡፡
- የጉርዳ ቒጫ – ጉርዳ ማለት የቃልኪዳን ስምምነት ሲሆን ስርዓቱ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ሆኑ ወገኖች በመካከላቸው መጠቃቃት፣ መከዳዳት፣ አለመተማማን እንዳይኖርና በመተጋገዝ፣ በመተማመን እና በመግባባት ግጭትን አስወግደው ጉዳያቸው መልካም ፍጻሜ እንዲያገኝ የሚጠቀሙበት እርስበእርሳቸው የሚገቡት ቃልኪዳን ነው፡፡
- የደም ቒጫ – ለጠፉ ህይወት ወይም ለተፈጸመው ወንጀል ማካካሻ የሚሆን በዳይ ወገኖች ቀዩአቸውን በመልቀቅ ለድርድር የሚቀርቡትና በጉርዳ ስርዓት ተመተው የጉዳት ካሳ እንዲከፍሉ የሚያደርግ አሰራር ነው፡፡
- የጀፎረ ቒጫ – ጀፎር በሁለት እና ከዚያ በላይ በሆኑ መንደርተኞች ፊት ለፊት ወይም መካከል የሚገኝ ጉዳና ሲሆን የጀፎረ ቂጫ የአካባቢው ህብረተሰብ ጎዳናዎቹ ለህዝብ ለመተላለፍያነት ከማገልገል ባለፈ እርሻ እንዳይረስባቸው ተገቢውን ቁጥጥርና ክትትል እንዲደረግ የሚያስገድድ ስርዓት (ደንብ) ነው፡፡
የጉራጌ የጆካ ቂጫ የዳኝነት ስርዓት በየእርከኑ በተዋረድ የፍርድ ውሳኔ የሚሰጥ ሲሆን በመጨረሻም የተፈረደበት አካል ትክክለኛ ውሳኔ አላገኙሑም ብሎ ካመነ የስልጣኑ ተዋረድ ተከትሎ ይግባኝ ሊጠይቅ ብሎም እስከ አጠቃላይ የቤተ ጉራጌ ሸንጎ ሊሄድ ይችላል፡፡
ይድነቃቸው ቸሃ
Yirgu Edilu says
ግንዛቤን ለሚያሰፋው ጽሁፍ እናመሰግናለን!!!
Mihret says
እውነት ነው ተጠቅመንበታል
Sile Sangawe says
ባህሌችን የማንነታችን መገለጫ ነው