የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ በሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ ጭና ተክለሃይማኖት በነሃሴ 26ና 27 ሁለት ቀን ብቻ ከመቶ ሃያ በላይ ንጹሃንን መጭፍጨፉ ከአካባቢው መረጃ እየወጣ ይገኛል። ትህነግ ለምን ጭፍጨፋውን እንደፈጸመ መረጃዎቹ እስካሁን ዝርዝር አላቀረቡም። ይሁን የቀብር ስፍራዎችን በፎቶ ማስረጃ ይፋ እየሆኑ ሲሆን፤ በጅምላ የተጨፈጨፉት ወገኖች ማንነት እየተለየ መሆኑ ታውቋል። ትህነግ የአማራና የአፋር ክልልን ከወረረ በሁዋላ በርካታ የጅምላ ጭፍጨፋና የነብስ ወከፍ ግድያ መፈጸሙ ይፋ እየሆነ ነው። መረጃዎች መሰራጨት ከጀመሩ በሁዋላ ክልሉ የሚከተለውን በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በኩል ገልጿል። እንዳለ አቅርበነዋል። የጀግኖቻችንን የተቀናጀ ጥቃት ሲቀምስ፣ በየጫካው እየተፋለሙት ያሉትን ጀግኖችን መቋቋም ያልቻለው ወራሪ በየቤታቸው የነበሩ አዛውንቶችን፣ ህፃናትንና … [Read more...] about ትህነግ በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ መቶዎችን ጨፍጭፏል
News
ዜና
ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የሪፐብሊካን ጋርድ አባላት አስመረቀ
በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ስር የሚገኘው ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ከሪፐብሊካን ጋርድ የተመለመሉ በቪአይፒ እና በቁልፍ መሰረተ ልማት ጥበቃ የሰለጠኑ መኮንኖችን አስመርቋል። የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የሪፐብሊካን ጋርድ አባላት ትልቅ ሃላፊነትና እምነት የተጣለባቸው ሲሆን፤ የሀገርን ብሔራዊ ደህንነት በማረጋገጥ ረገድም ከፍተኛ ሚና ሲያበረክቱ እንደነበር ገልጸዋል። በተለይ ከሀገራዊ ለውጡ ጋር ተያይዞ ያጋጠሙ ፈተናዎችን በከፍተኛ ወኔና ትዕግስት በመፍታት ያበረከቱት አስተዋጽኦ አስቸጋሪ ጊዜዎችን ለማለፍ እንዳስቻለ ያስታወሱት አቶ ተመስገን፤ በቀጣይ ተልዕኳቸውን በብቃትና ጥብቅ በሆነ የስራ ዲሲፒሊኒ ለመወጣት የሚስችላቸውን ስልጠና ከዩኒቪርሲቲ ኮሌጁ … [Read more...] about ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የሪፐብሊካን ጋርድ አባላት አስመረቀ
በሱዳን ስደተኛ ካምፕ የነበሩት ሳምሪዎች ለትህነግ ተዋግተዋል
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) ከትግራይ ክልል ወጥተው በሱዳን መጠለያ ጣቢያ የነበሩ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በጦርነት መሳተፋቸውን ባወጣው መግለጫ አመለከተ። ዩኤንኤችሲአር ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው በሱዳን መጠለያ ጣቢያ የሚገኙና ድጋፍ የሚደረግላቸውን ስደተኞች የመረጃ ሁኔታን ከልሷል። በዚሁ መሰረት በመጠለያ ጣቢያው ተመዝግበው የነበሩ ስደተኞች ቁጥር ከቅርብ ወራት ወዲህ መቀነሱንና በስደተኛነት ተመዝግበው የነበሩ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ ይመለሱ ወይም የት ይሂዱ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ይፋ አድርጓል። በግጭት ውስጥ የተሳተፈን ሰው በስደተኛነት የማይቀበለው ዩኤንኤችሲአር በስደተኛነት ተመዝግቦ በግጭት ውስጥ የተሳተፈ ማንኛውንም ሰው ዳግም እንደማይቀበል አድርጓል። ከኢትዮጵያ ግጭት ሸሽተው በሱዳን መጠለያ ጣቢያ ውስጥ … [Read more...] about በሱዳን ስደተኛ ካምፕ የነበሩት ሳምሪዎች ለትህነግ ተዋግተዋል
የዳያስፖራ ትህነጎች ቀጣይ አጀንዳ
የትግራይ ዲያስፖራ የሳይበር ቡድን (Diaspora Cyber Team) ትላንት (Sep 5) ስብሰባ ነበራቸው።የእኛ ሰዎችም የሳይበር ውይይታቸውን ሰብረው በመግባት ታድመው ወጥተዋል። አጀንዳዎቹ:- 1- አለም አቀፍ ጫናዎችን በድጋሜ በአዲስ መልክ እንዴት እንፍጠር? 2- ትግራይ ውስጥ ቤተሰቦቻችን በርሃብ እያለቁ ነው። ለዚህስ መፍትሄው ምንድነው? 3- ህወሓት/የትግራይ መንግስት ምን ማድረግ አለበት? የሚሉ ናቸው። የተስማሙባቸው ነጥቦች:- 1ኛ) ጦርነቱ ትግራይ መሬት ላይ በነበረበት ወቅት ተዘረፍን ፣ ሴቶች ተደፈሩ ፣ በጅምላ ተገደልን ... ብለን የአለም አቀፍ መንግስታት ጫና እንዲፈጥሩ አድርገናል። አሁን ያንን መንገድ መከተል አዋጭ ስላልሆነ 5.2 ሚሊዮን ህዝብ በርሃብ እየተጎዳና እየሞተ እንደሆነ ፣ ወደ ትግራይ እየገባ ያለው የእርዳታ እህልም እጅግ … [Read more...] about የዳያስፖራ ትህነጎች ቀጣይ አጀንዳ
በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ከተማ ከ31 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይት ተያዘ
በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ ከ31 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶችን ከሁለት ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉን የምዕራብ ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። ህገ-ወጥ ጥይቶቹን በአይሱዙ የጭነት መኪና ሲጓጓዝ በተደረገ ክትትልና ፍተሸ መያዙን በምዕራብ ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የአከባቢ ጸጥታና ደህንነት ምክትል ዳይሬክተር ሳጅን ምትኩ ብርሃኑ ገልጸዋል። ዳይሬክተሩ ህብረተሰቡ ህገ-ወጥ ተግባራትን በማጋለጥና ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት እያደረገ ያለውን ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ከተማ ከ31 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይት ተያዘ
“የማንነታችን መገለጫዎች ማሰሪያው ኢትዮጵያዊነት ነው”- ዶ/ር ዲማ ነገዎ
ዛሬ (ሰኞ) በሸራተን አዲስ እየተከበረ በሚገኘው የኢትዮጵያዊነት ቀን የመወያያ ጽሑፍ ያቀረቡት ዶ/ር ዲማ ነገዎ የማንነታችን መገለጫዎች ማሰሪያው ኢትዮጵያዊነት ነው ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ የህዝቦች የተለያዩ የማንነት መገለጫዎች መኖራቸውን የገለጹት ዶ/ር ዲማ እነዚህን ሁሉ አጠቃሎ አንድ ዓይነት አገራዊ ማንነት የሚሰጠን ኢትዮጵያዊነታችን ማንነት ነው ብለዋል፡፡ አሁን ያለው ኢትዮጵያዊ ማንነት አንድነትን በብዝሀነት አጣምሮ ሁሉንም ህዝብ በእኩልነት የሚያስተናግድ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ አገሪቷ አሁን ያለችበትን ውስብስብ ፈተና እንድትሻር ለማስቻል በህግ ማስከበር እና በሌሎች በሚወሰዱ እርምጃዎች የአገርን አንድነት እና ኢትዮጵያዊነትን እንዳይሸረሽር ጥንቃቄ መደረግ አለበት ብለዋል፡፡ (ኢብኮ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ማስታወሻ፤ የኦሮሞ መብት አቀንቃኝ ነን ለሚሉትና … [Read more...] about “የማንነታችን መገለጫዎች ማሰሪያው ኢትዮጵያዊነት ነው”- ዶ/ር ዲማ ነገዎ
ስለ አገር ሰላምና አንድነት የ5 ቀናት ፀሎትና ምህላ ታወጀ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በጳጉሜ ወር ለሀገር ሰላም እና አንድነት በመላው ዓለም በምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፀሎት እና ምህላ ወስኗል። ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ፣ ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፥ ቋሚ ሲኖዶሱ 5ቱን የጳጉሜ ቀናት በፀሎትና ምህላ እንዲታሰብ መወሰኑን ገልፀዋል። ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፥ 2013 ዓ.ም ብዙ ችግሮችን ያሳየ መሆኑን ያነሱ ሲሆን "በፈተናው ውስጥም ቢሆን ግን ብዙ በረከቶችን ያሳየን ነገሮች አሉ" ብለዋል። እንደሀገር፤ እንደዓለምም የተከሰቱ ችግሮች ወደቀጣይ ዓመት አብረው እንዳይተላለፉ እግዚአብሔርን በፀሎት መጠየቅ ስላለብን ይህ ውሳኔ ተላልፏል ሲሉ አስረድተዋል። አክለውም፥ "ቤተክርስቲያን በሀገራችን ውስጥ ያለው ጦርነቱ፣ ረሃቡ፣ ስደቱ፣ … [Read more...] about ስለ አገር ሰላምና አንድነት የ5 ቀናት ፀሎትና ምህላ ታወጀ
የስደተኛ መታወቂያ የያዙ የትህነግ ተዋጊዎች ተይዘዋል፤ ተመድ እያጣራ ነው ብሏል
“የስደተኞች መታወቂያን ይዘው ተገኝተዋል” የተባሉ ታጣቂዎችን ጉዳይ እያጣራ እንደሆነ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ከፍተኛ የስደተኞች ጉዳይ ኤጀንሲ ገለጸ። ኤጀንሲው “በሱዳን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የነበሩና የተመድ ስደተኞች ኤጀንሲ መታወቂያ የያዙ ታጣቂዎች ተገኙ” የሚሉ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወሩና በተለያዩ የሚድያ አውታሮች ሲዘገቡ መመልከቱን ስለ ጉዳዩ ለጠየቀው አል ዐይን አማርኛ በላከው የኢ-ሜይል መልዕክት አስታውቋል። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር ሰሞኑን በሱዳን አቅጣጫ መጥተው “ሽንፋ የተባለ ቦታን ለመያዝ የተንቀሳቀሱ የቅማንትና ህወሃት ታጣቂዎች መደምሰሳቸው”ን የሚያሳውቅ ጽሁፍ በትዊተር ገጻቸው ማጋራታቸው የሚታወስ ነው። ዓለም አቀፍ ብዙሃን መገናኛዎች ‘ህወሓት ሰብዓዊ እርዳታን እየዘረፈ ነው’ መባሉን “ከዓለም … [Read more...] about የስደተኛ መታወቂያ የያዙ የትህነግ ተዋጊዎች ተይዘዋል፤ ተመድ እያጣራ ነው ብሏል
ባጠናቀቅነው ነሀሴ ወር በቁጥጥር ሥር የዋሉ ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች
መነሻውን ከጋምቤላ ያደረገ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-15074 አ/አ በሆነ ዶልፊን ህዝብ ማመላለሻ ሲዘዋወር የነበረ ህገወጥ መሳሪያ ከነተጠርጣሪዎቹ በዚህ ወር ተይዟል፤ የተያዘው መሳሪያ በቁጥር 12 ክላሽንኮቭ እና 5 ጥይት መያዣ ነው። የሰሌዳ ቁጥር A76390 በሆነ ቪትዝ መኪና 5 ክላሽንኮቭ ከ132 ጥይት ጋር ሲዘዋወር በድንገተኛ ፍተሻ ተይዟል (እንደ ጎንደር ከተማ ፖሊስ መረጃ) በሀመር ወረዳ በዚህ እያጠናቀቅን ባለነው ወር ውስጥ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 10 መሳሪያ፣ 14 ክላሽ ጥይት፣ 3 የክላሽ መጋዘን ተይዟል። በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው ውሃ ልማት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው አምባሳደር ፔንሲዮን ውስጥ 10 ባለሰደፍና 10 ታጣፊ ክላሽንኮቭ ጠብመንጃዎች እና 17 የክላሽንኮቭ ጥይት ካርታዎች ተይዘዋል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 2 … [Read more...] about ባጠናቀቅነው ነሀሴ ወር በቁጥጥር ሥር የዋሉ ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች
ሰሞኑን በተደረገው ጦርነት ከ10ሺህ በላይ የትህነግ ታጣቂዎች ተገድለዋል
የኢትዮጵያ መካለከያ ሠራዊት ቅዳሜ በሰጠው መግለጫ በከሃዲው ጄነራል ምግበይ ይመራል የሚመራው “አርሚ 1” የተባለ ኃይል ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን በይፋ አሳወቀ። መግለጫውን የሰጡት የመከላከያ ሚኒስቴር የሠራዊት ግንባታ ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀኔራል ባጫ ደበሌ ሲሆኑ የኢትዮጵያ ሰራዊትን ግዳጅ አፈጻጸምና ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል። ህወሓት ህፃናትን አሰልፎ በአማራ ክልል ወረራ መፈፀሙን ያነሱት ሌ/ጄነራል ባጫ የቡድኑ ፍላጎት ኢትዮጵያ የምትባልን ሀገር መበታተን ነው ብለዋል። ህወሓት ስልጠና ያልወሰዱ ህፃናትን ወደ ጦርነት በመማገድ ላይ ነው ሲሉም አክለዋል። የትግራይ ወጣቶችን ከተቻለ ሁለት ቀን አሰልጥኖ አንድ ጠመንጃ ለአምስት ሰጥቶ ወደግምባር ካስገቡ በኋላ መሪዎቹ ውጊያውን ስለሚያውቁ ተኩስ ሲበዛባቸው ወደኋላ የሚሸሹትን እንደሚገድል ነው … [Read more...] about ሰሞኑን በተደረገው ጦርነት ከ10ሺህ በላይ የትህነግ ታጣቂዎች ተገድለዋል










