• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የሪፐብሊካን ጋርድ አባላት አስመረቀ

September 8, 2021 12:34 pm by Editor Leave a Comment

በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ስር የሚገኘው ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ከሪፐብሊካን ጋርድ የተመለመሉ በቪአይፒ እና በቁልፍ መሰረተ ልማት ጥበቃ የሰለጠኑ መኮንኖችን አስመርቋል።

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የሪፐብሊካን ጋርድ አባላት ትልቅ ሃላፊነትና እምነት የተጣለባቸው ሲሆን፤ የሀገርን ብሔራዊ ደህንነት በማረጋገጥ ረገድም ከፍተኛ ሚና ሲያበረክቱ እንደነበር ገልጸዋል።

በተለይ ከሀገራዊ ለውጡ ጋር ተያይዞ ያጋጠሙ ፈተናዎችን በከፍተኛ ወኔና ትዕግስት በመፍታት ያበረከቱት አስተዋጽኦ አስቸጋሪ ጊዜዎችን ለማለፍ እንዳስቻለ ያስታወሱት አቶ ተመስገን፤ በቀጣይ ተልዕኳቸውን በብቃትና ጥብቅ በሆነ የስራ ዲሲፒሊኒ ለመወጣት የሚስችላቸውን ስልጠና ከዩኒቪርሲቲ ኮሌጁ መቅሰማቸውን አመልክተዋል።

አቶ ተመስገን የሪፐብሊካን ጋርድ አባላቱ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥርላቸውን ስልጠና እንዲያገኙ ላስቻሉት ለዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ አካለት ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የሪፐብሊካን ጋርድ ምክትል አዛዥ ብ/ጀነራል አብድሮ ከድር፤ የሪፐብሊካን ጋርድ አባላት በርካታ ሀገራዊ ግዳጆችን እየተወጡ መሆኑን አመልክተዋል።

አሁንም አሸባሪው ህወሓት በተለያዩ አቅጣጫዎች የከፈተውን ጦርነት ለመመከት ከሌሎች ሃይሎች ጋር በመቀናጀት ከፍተኛ ጀብዱ እየፈጸሙ ነው ብለዋል።

“በብሔራዊ የመረጃና ደህንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የተሰጠው ስልጠና ሀገራችን ከእኛ የምትጠብቀውን ግዳጅ በላቀ ደረጃ ለመፈጸም እገዛ ያደርጋል” ያሉት ብ/ጀነራል አብድሮ፤ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ አመራሮች ስልጠናው ከውጥኑ ጀምሮ እስከ ፍጻሜው የተሳካ እንዲሆን ከፍተኛ እገዛ በማድረጋቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ከልጠናውም የሪፐብሊካን ጋርድ አባላቱ ለተሰጣቸው ስምሪት አጋዥ የሚሆን በጣም ጠቃሚ ግብዓት መገኘቱን መስክረዋል።

የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዚዳንት አቶ ወንድወሰን ካሳ በበኩላቸው፤ የሪፐብሊካን ጋርድ አባላት ከተሰጣቸው ሀገራዊ ተልዕኮ አንጻር ውጤታማ ስምሪት እንዲያደርጉ የሚያስችላቸው ስልጠና እንደተሰጣቸው አመልክተዋል።

የቪአይፒ እና የቁልፍ መሰረተ ልማት ጥበቃ የዘመናችን የብሔራዊ ደህንነት ስምሪት ወሳኝ አካል ናቸው ያሉት የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ፕሬዚዳንት፤ የሪፐብሊካን ጋርድ አባላቱ በዚህ ረገድ አቅማቸውንና ክህሎታቸውን የሚያሳድግ የንድፈሀሳብና የተግባር ስልጠና መውሰዳቸውን አመልክተዋል።

የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በ2013 በጀት ዓመት ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ጀማሪ ኦፊሰሮች ከሰጠው ተከታታይ ስልጠና በተጨማሪ፤ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ፣ ለገቢዎችና ጉምሩክ፣ ለክልሎች እንዲሁም ለተለያዩ ተቋማት ባለሙያዎችና አመራሮች በመረጃ፣ በደህንነትና በተያያዥ መስኮች በርካታ ስልጠናዎች ስጥቷል።

በቀጣይም ለአካባቢው እና ለጎረቤት ሀገራት አቻ የመረጃና ደህንነት ተቋማት በመረጃና ደህንነት ዘርፎች የተለያዩ ስልጠናዎችን ለመስጠት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ስምምነት መፈፀሙን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያደረሰው መረጃ ያመለክታል። (ኢ.ፕ.ድ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: News, Right Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule