• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የስደተኛ መታወቂያ የያዙ የትህነግ ተዋጊዎች ተይዘዋል፤ ተመድ እያጣራ ነው ብሏል

September 5, 2021 03:22 pm by Editor Leave a Comment

“የስደተኞች መታወቂያን ይዘው ተገኝተዋል” የተባሉ ታጣቂዎችን ጉዳይ እያጣራ እንደሆነ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ከፍተኛ የስደተኞች ጉዳይ ኤጀንሲ ገለጸ።

ኤጀንሲው “በሱዳን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የነበሩና የተመድ ስደተኞች ኤጀንሲ መታወቂያ የያዙ ታጣቂዎች ተገኙ” የሚሉ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወሩና በተለያዩ የሚድያ አውታሮች ሲዘገቡ መመልከቱን ስለ ጉዳዩ ለጠየቀው አል ዐይን አማርኛ በላከው የኢ-ሜይል መልዕክት አስታውቋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር ሰሞኑን በሱዳን አቅጣጫ መጥተው “ሽንፋ የተባለ ቦታን ለመያዝ የተንቀሳቀሱ የቅማንትና ህወሃት ታጣቂዎች መደምሰሳቸው”ን የሚያሳውቅ ጽሁፍ በትዊተር ገጻቸው ማጋራታቸው የሚታወስ ነው።

ዓለም አቀፍ ብዙሃን መገናኛዎች ‘ህወሓት ሰብዓዊ እርዳታን እየዘረፈ ነው’ መባሉን “ከዓለም አቀፍ ተቋማት ሲሰሙ ብቻ መዘገባቸው ለምን ተብሎ መጠየቅ አለበት” ሲል ከትናንት በስቲያ አርብ ያስታወቀው የፌዴራል መንግስትም እየተገኙ ያሉት መታወቂያን መሰል ማስረጃዎች ስደተኛ መስለው ወደ ሱዳን መጠለያ ጣቢያዎች የገቡት የማይካድራ ጭፍጨፋ ፈጻሚ የሳምሪ ቡድን አባላት ተመልሰው ሳይመጡ እንዳልቀረ አመላካች ነው ሲል መግለጹ ይታወሳል።

ይህን ተከተሎም የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ የስደተኞች ጉዳይ ኤጀንሲ /ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር/ የኢትዮጵያ ማስተባበሪያ ቢሮ ምላሽ ሰጥቷል።

ምላሹን የሰጡት የቢሮው ቃል አቀባይ ኔቨን ክሬቨንኮቪች ታጣቂዎቹ ይዘውት ተገኘ ከተባለው “የተመድ የስደተኛ መታወቂያ”ጋር በተያያዘ የወጣውን መረጃ ኤጀንሲው እያጣራ መሆኑን ለአል-ዐይን በላኩት የኢ-ሜይል መልዕክት ገልጸዋል።

ቃል አቀባዩ፤ ሰሞኑን “በሱዳን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የነበሩና የተመድ ስደተኞች ኤጀንሲ መታወቂያ የያዙ ታጣቂዎች ተመልሰው በግጭቱ ሲሳተፉ ተገኙ” የሚሉ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወሩና በተለያዩ የሚድያ አውታሮች ሲዘገቡ ተመልክተናል ብለዋል።

ተቋማቸው ጉዳዩን እያጣራ እንደሆነም ነው የገለጹት።

ስደተኞቹን የተመለከቱ አዳዲስ መረጃዎች ሲገኙ፣ ከመጠለያ ጣቢያዎች ሲወጡም ሆነ መታወቂያ ካርዳቸው ሲጠፋ የመረጃ ቋታችን የምናዘምንበት በመደበኛ የአሰራር ስርዓት አለን ብለዋል ስደተኞቹ ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ሲወስኑ ስደተኛነታቸውን እንደሚያጡ በመጠቆም።

ኤጀንሲው “በቅርቡወደ ኢትዮጵያ በስደተኞች የተደረገ እንቅስቃሴ” አለመመልከቱንም ገልጸዋል ቃል አቀባዩ።

“በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ሆነን የስደት ተመላሾችን የምናረጋግጥበት ሁኔታም የለም”ም ብለዋል ኔቨን ክሬቨንኮቪች።

ኤጀንሲው “የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች የሲቪል ባህርይን ጠብቀው እንዲቆዩ እና ይህንን ለማረጋገጥ የሚያስችል ድጋፍ ለሱዳን መንግስት ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት” ደጋግሞ መግለጹንም ተናግረዋል።

የተመድ ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍሊፖ ግራንዴ በቅርቡ ወደ ሱዳን አቅንተው መጠለያ ጣቢያዎቹን ጎብኝተው ነበር።

ግራንዴ በዚሁ ጉብኝታቸው ይህንኑ መግለጻቸውንም ነው ያስታወቁት።

ክሬቨንኮቪች “በስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ወታደራዊ ሥልጠናዎች ይሰጣሉ” የሚለው “መሠረተ ቢስ” ነውም ብለዋል።

ያልተረጋገጡ የግል መረጃዎችን የስደተኞች ናቸው በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ማጋራቱ እንዲቆምም አሳስበዋል።

ይህ በግለሰቦቹ፣ በቤተሰባቸውና በሱዳን በሚገኙ ስደተኞች ላይ ለበቀል እንደሚያነሳሳም ነው ቃል አቀባዩ የገለጹት። (አል-አይን)

ከዚሁ ጋር በተዛመደ የማኅበረሰብ አንቂ የሆነው ጌታቸው ሽፈራው መረጃው እንደተገኘ ይህንን መልዕክት በፌስቡኩ ለጥፎ ነበር፤

የኢትዮጵያ መንግሥት ሆይ!

ይሄውልህ የዓለም አቀፉን ማሕበረሰብ ቅሌት ማሳየት የምትችልበት መረጃ!

ከስር የተያያዘው መረጃ ሱዳንና UNCHCR  በዓለም አቀፍ ሕግ የሚያስጠይቅ ነው። ሀጎስ ሃይላይ በርሀ የተባለ ግለሰብ ሱዳን ውስጥ የUNHCR የስደተኛ የምዝገባ መታወቂያን ተቀብሏል። ስደተኛ ካምፕ ውስጥ ቀለብና መጠለያ እያገኘ ወጣ ብሎ ደግሞ እየሰለጠነ ከርሞ ኢትዮጵያን  ለመውጋት የመጣው ኃይል ዛሬ በቋራ መስመር ሲመታ መረጃዎቹ ተይዘዋል። ሀጎስ ምሳሌ ነው። እነ ጌታቸው ረዳ ሱዳን ውስጥ 30 ሺህ ጦር አለን ያሉት በሙሉ ስደተኛውን አሰልጥነው ነው።

በ1951 የጀኔቫ የስደተኞች ስምምነት መሰረት ስደተኛውን የተቀበለው ሀገርም ሆነ፣ ስደተኛውን የያዘው ተቋም ጥብቅ ግዴታዎች አሉባቸው። ሱዳን ስደተኛውን እንዳስጠለለች ሀገር የተቀበለችው ስደተኛ ጦርነት የሚያህል ተመድ በመርሁ የሚቃወመው ነገር እንዳይገባ የማድረግ ግዴታ አለባት። የሆነው ግን ስደተኞች ጣቢያ አካባቢ ማሰልጠኛ ተከፍቶ ስደተኛው አንዴ መጠለያ፣ ሌላ ጊዜ ማሰልጠኛ ጣቢያ እየተመላለሰ ኢትዮጵያን እንዲወጋ ተደርጓል። ያውም የሱዳንና የግብፅ መንግስት የመሳርያና ሌሎች እገዛዎችን አድርገውለት። የኢትዮጵያ መንግስት ይሄን መረጃ በማጠናከር  ለተመድና ለአባላቱ፣ ለኢትዮጵያ ወዳጅና ጠላቶች ማቅረብ አለበት።

ሱዳን ስደተኛ አስጠልላለሁ ብላ ከግብፅ ጋር ሆና አሰልጥና እየላከች መሆኑን ማሳወቅ አለበት። በተመድ ስር ያለው UNHCR በስሩ ያሉ ስደተኞችን ለጦርነት ተመልምለው፣ ሰልጥነው ሀገር ሲወጉ ዝም ብሎ እያየ እንደሆነ ለዓለም ማሳወቅ አለበት። የውጭ ጉዳይ በመግለጫው በደንብ ማካተት አለበት፣ ለኤምባሲዎች መረጃውን አጠናቅሮ ማድረስ አለበት። አምባሳደሮች ለያሉበት ሀገር መንግስትና ሚዲያ፣ በተመድ የኢትዮጵያ ተወካይ ደግሞ ለሚገባቸው አካላት ማድረስ አለበት። በዓለም አቀፍ ሕግ የሚኬድባቸው አካሄዶች በሙሉ ሊናቁ አይገባም።

ይህን ሁሉ የሚያደርገው በዓለም አቀፍ መድረክ ፍትሕ ስለሚገኝበት አይደለም። ነገር ግን አስር ጊዜ በኢትዮጵያ ጉዳይ ስብሰባ የሚጠራው ተደመድ ራሱ መጠለያ የሰጣቸው ስደተኞች ወታደር ሆነው ሀገር እየወጉ  መሆኑን ማሳወቅ ይገባል። ስደተኛ ካምፕ ውስጥ ሆነው ሱዳንና UNHCR እያንዳንዷን እንቅስቃሴ ሊቆጣጠሯቸው የሚገባቸው ስደተኞች ከባድ መሳርያ፣ የቡድንና የግል መሳርያ ይዘው ሀገር ሲወጉ፣ ንፁሃንን ሲጨፈጭፉ፣ ሲዘርፉ፣ ሲደፍሩ ነው የተደረሰባቸው።

እነ ሳማንታ ፓወር ሄደው በጎበኙት የሱዳን ካምፕ ያለው ስደተኛ ወታደር ሆኖ እየወጋን እንደሆነ ማሳወቅ ይገባል። በተመድ ስብሰባ አስር ጊዜ ስለስደተኛ አያያዝ እያነሱ የሚያወግዙን ልካቸውን ማወቅ አለባቸው። ቢያንስ ይሄ መረጃ ሌላ ጊዜ  ትህነግን ለመደገፍ ብለው፣ መርህን አጣመው አፍ  እንዳይከፍቱ መያዥያ ይሆናል።  ሄደው ሲጎበኙ ስደተኛው ሁሉ እየሰለጠነ እንደሆነ መረጃ አጥተው አይደለም። ስለሆነም የዓለም አቀፍ ተቋማት ነውርን ማሳወቅ የሚያስችሉትን መንገዶች ሁሉ ማየት ያስፈልጋል። ጦርነት ውስጥም ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው ማሳየት ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ መንግስት ይህን መረጃ ሊጠቀምበት ይገባል!

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule