አንዳንዶች ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ በቆዩበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት የመጨረሻ ዘመንና የመጨረሻው ሳምንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ሰኔ 28 ቀን 2013. ዓ.ም. በነበራቸው ጥያቄና መልስ፣ በአገሪቱ ታሪክ ከፍተኛ የተባለውን 561 ቢሊዮን ብር የ2014 ዓመታዊ በጀት እንዲሆን የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ የመጨረሻ የውሳኔ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡ በዕለቱ ከፍተኛ የአገሪቱ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች፣ የግሉ ዘርፍ ተወካዮችና ሌሎችም አካላት በተገኙበት በዚሁ የፓርላማው ስድስተኛ ዓመት አራተኛ ልዩ ስብሰባ በወቅታዊ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ያመዘኑ በርከት ያሉ ጥያቄዎች ከ15 የምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀርበውላቸው ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምክር ቤቱን … [Read more...] about “ለዶሮ በሽታ በሬ ማረድ ትክክል አይደለም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ
tplf
የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!?
ከመግቢያው በፊት ይህንን ዘገባ በቴድሮስ አድሃኖም ላይ የሠራነው ከዓመት በፊት April 12, 2020 ነው። ትህነጉ ቴድሮስ አገራችንን ወክሎ የዓለም ጤና ጥበቃ ሃላፊ መሆን እንደሌለበት ገና ለምርጫ ሲወዳደር ጀምሮ አጥብቀን ተቃውመናል። አሁን ወቅቱ የደረሰ ይመስላል። ጥያቄው እየቀረበ ነው። ቴድሮስ አሸባሪውን ህወሃት እስካሁን እየደገፈ ያለ በመሆኑ ብቻ ከሥልጣኑ መወገድ ብቻ ሳይሆን ለፍርድም መቅረብ ያለበት ነው። ዘገባውን በድጋሚ አትመነዋል። እንደ መግቢያ ሰሞኑንን ከኮቪድ - 19 ጋር ተያይዞ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሓኖም አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱ ይታወሳል። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ካወደመው፣ የዘር ፖለቲካን ከሚያራምደው ፍጹም ጽንፈኛና ዘረኛ፣ እንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ ኢትዮጵያውያንን በዘራቸው፣ በፖለቲካ እምነታቸው ካኮላሸ፣ ከጨፈጨፈ፣ ቶርቸር … [Read more...] about የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!?
“ለትግራይ እንደ ጫማ ሶል ሆነን ነው ስናገለግል የነበረው … ለእኛ ይህ አይገባም ነበር” – ብ/ጀነራል ናስር አባ ዲጋ
የክፋት አለቃው ህወሀት መራሹ ወንበዴ ቡድን በክፋት ሰይፉ ጉዳት ካደረሰባቸው የሰራዊት ክፍሎች መካከል ብ/ጀነራል ናስር አባዲጋ የሚመሩት የ8ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ይገኝበታል። ሜካናይዝድ ክፍለ ጦሩ የደረሰበትን የክፋት ጥቃት ተቋቁሞ ሃይሉንና ትጥቁን በመያዝ እየተዋጋ ወደ ጎረቤት ሃገር ኤርትራ ከተሻገረ በኋላ እንደገና ሃይሉንና ትጥቁን አቀናጅቶ እየተዋጋ የገባ ክፍለ ጦር ነው። እስከ ሽራሮ እየተዋጋ መጥቶም፣ ከሰሜን ምዕራብ ግንባር ዳንሻ ጀምሮ እየተዋጋ ከመጣው ምዕራብ ዕዝ ጋር በመቀናጀት እስከ መቀሌ ከዛም ጁንታው ተበጣጥሶ በረሃ እስከገባበት ጊዜ ድረስ በውጤት እርቀቱ ሆኖ ከባድ ምት በማሳረፍ የነበረው ሚና በቃላት ከሚገለፀው በላይ ነው። መቀሌን እንደተቆጣጠርን የሜካናይዝድ አዛዡን ብ/ጀነራል ናስር አባዲጋን አግኝቼ ስለ ጥቃቱ አናግሪያቸው ነበር። እሳቸውም … [Read more...] about “ለትግራይ እንደ ጫማ ሶል ሆነን ነው ስናገለግል የነበረው … ለእኛ ይህ አይገባም ነበር” – ብ/ጀነራል ናስር አባ ዲጋ
የመለስ ዜናዊ አካዳሚ ለ21ኛው ክፍለዘመን የማይመጥን ስም በመሆኑ ተቀየረ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ "የመለስ ዜናዊ የአመራር አካዳሚ" "የአፍሪካ የአመራር ልህቀት ማዕከል" (‘African Leadership Excellence Academy’) በሚል መቀየሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስታውቀዋል። አካዳሚው ከስም ለውጥ ጋር የ21 ኛው ክፍለዘመን የአመራር ጥያቄዎችን ለማሟላት የሚያስችል ዐቅም ያላቸውን ልሂቃን የሚያፈራ እና የዕድገት ተኮር አስተሳሰብን የሚያንፀባርቅ የትምህርት ተቋም እንዲሆን ያለመ ነው ብለዋል። ሌሎችም ከአሸባሪው ህወሃት ጋር የተቆራኙ ስሞችና መጠሪያዎች እንዲሁ እንዲቀየሩ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል። ከዚህ በፊት አካዳሚውን እንዲመሩ የተሾሙት ዮሐንስ ቧያለው የአካዳሚው ስም በመጸየፍ አልመራም ማለታቸው ይታወሳል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about የመለስ ዜናዊ አካዳሚ ለ21ኛው ክፍለዘመን የማይመጥን ስም በመሆኑ ተቀየረ
“በተለምዶ ‘ሸኔ’ የሚባለው ራሱን ‘የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት’ ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው”
በርካቶች 'ሸኔ' እያለ እራሱን የሚጠራ ድርጅት በሌለበት እንዴት አሸባሪ ተብሎ ይሰየማል ሲሉ ይጠይቃሉ። ይህ ስያሜ አንዳች ነገር ለመሸፈን ተፈልጎ ነው በሚል ጥርጣሬያቸውን የሚገልፁ ምሁራንም አልጠፉም። ለመሆኑ 'ሸኔ' ማነው? በዚህ ጉዳይ ላይ በዛሬው ዕለት የተጠየቁት የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዮስ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል፦"በተለምዶ 'ሸኔ' የሚባለው እራሱን ደግሞ 'የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት' ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው። በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በሌሎችም ክልሎች እየተንቀሳቀሰ ጥቃት የሚያደርስ ድርጅት ነው። እራሱ ለእራሱ የሰጠውን ስያሜ ግን እኛ የምናፀድቅበት ምክንያት የለንም፤ ተገቢም አይሆንም ብለን እናምናለን። ይህ ቡድን ከዚህ በፊት እንደ 'ህወሓት' ተመዝግቦ፣ ህጋዊ እውቅና፣ ህጋዊ ሰውነት እና ሰርተፊኬት ኖሮት የሚያውቅ አይደለም፤ … [Read more...] about “በተለምዶ ‘ሸኔ’ የሚባለው ራሱን ‘የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት’ ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው”
የስኳር ፋብሪካዎች ተሽጠው ዕዳቸውን እንዲከፍሉ ተወሰነ
በመንግሥት ባለቤትነት ሥር ከሚገኙት 13 ስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ አሥሩ ለግል ባለሀብቶች ተሸጠው፣ ከሽያጩ የሚገኘው ገቢ በከፍተኛ የዕዳ አጣብቂኝ ውስጥ ናቸው ተብለው ለተለዩ ሰባት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ዕዳ ክፍያ ጥቅም ላይ እንዲውል ተወሰነ። ሪፖርተር ያገኘው መንግሥታዊ መረጃ እንደሚያመለክተው ሰባቱ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ካለባቸው አጠቃላይ ዕዳ ውስጥ፣ አመዛኙ እንደ አዲስ ወደ … [Read more...] about የስኳር ፋብሪካዎች ተሽጠው ዕዳቸውን እንዲከፍሉ ተወሰነ
እነ ስብሃት ነጋ ጥያቄያቸው ውድቅ ሆነ
እነ አቶ ስብሃት ነጋ ጉዳያችን በትግራይ ክልል ፍርድ ቤት ይታይልን ሲሉ አቤቱታ አቅርበው ነበር። ይህን አቤቱታ ያቀረቡት ዛሬ (ማክሰኞ) በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው። በችሎት የተገኙት የጠቅላይ አቃቤ ህግ ቡድን በበኩሉላቸው የፌዴራል መንግስትን ስልጣን ለመጣል በሚል የሽብር አዋጁን በመተላለፍ በመላው ሀገሪቱ የተፈጸመ ወንጀል መሆኑን በመጥቀስ ተጠርጣሪዎቹ መቀሌ ሆነው በሰጡት ትዕዛዝ ባህርዳር እና ጎንደርን በሮኬት ማስደብደባቸው አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል። በተጨማሪም ተከሳሾቹ ስልጣን ተከፋፍለው በተለያዩ ቦታዎች የተፈጸመ ወንጀል ነው ያለው አቃቤ ህግ ዶክተር አዲስ አለም ባሌማ የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ሆነው አዲስ አባባ ቁጭ ብለው ሲፈጽሙ የነበረው ወንጀል አንድ ቦታ አለመሆኑን ማመላከቻ ነው ብሏል በምላሹ። ይህ … [Read more...] about እነ ስብሃት ነጋ ጥያቄያቸው ውድቅ ሆነ
አሜሪካ በሴናተሯ አማካይነት “ለቅሶ” ደረሰች
የፕሬዚዳንት ባይደን የቅርብ ወዳጅ የሆኑት ሴናተር ክሪስቶፈር ኩንስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ለማነጋግር አዲስ አበባ መጥተው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን አነጋግረዋል። የኋይት ሐውስ የፕሬዚዳንቱ የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ የሆኑት ጄክ ሱለቫን ባወጡት አጭር መግለጫ እንዳሰፈሩት በትግራይ አለ በሚባለው የሰብዓዊ መብት ገረጣና ሰብዓዊ ቀውስ ባይደን ያላቸውን ትልቅ ጭንቀት ሴናተር ኩንስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንደሚያቀርቡ ነበር የጠቆሙት። በተጨማሪም ሁኔታው የአፍሪካ ቀንድን አለመረጋጋት ውስጥ ሊከተው የሚችል በመሆኑ ሴናተሩ ከአፍሪካ ኅብረት ጋር እንደሚመክሩበት አማካሪ በመግለጫቸው አመልክተው እንደነበር ይታወሳል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ በተገኙበት አቶ ደመቀ ተቀብለው አስፈላጊው ማብራሪያ እንደተሰጣቸው የውጭ ጉዳይ … [Read more...] about አሜሪካ በሴናተሯ አማካይነት “ለቅሶ” ደረሰች
ኤርሚያስ ለገሰ “የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም”
የቀድሞው ኢህአዴግ ካድሬዎች እና የህወሓት ጀነራሎች ሂሳብ አስተማሪው ኤርሚያስ ለገሰ ሆን ብሎ በቁጥር ሊጫወት ሞክሯል፡፡ አላማው ኢዜማ የክልል ምክር ቤት ወንበሮችን ሊያሸንፍ እንደማይችል አስመስሎ መሳል ነው፡፡ ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ ሆኖበት ነው፡፡ ኤርምያስ ሹመት አስቦ የለውጡ ደጋፊ የነበረ ጊዜ የተናገረው የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም፡፡ ምናልባት እንዲገባው ከዚህ በፊት ከነበረው የተቃዋሚዎች ዕጩዎች ቁጥር በ11% እድገት አሳይተናል እንበለው ይሆን?? ምንም እንኳን [ለእንደዚ አይነቱ አውቆ አበድ መፍትሄው] ንቆ መተው ቢሆንም ያቀረበውን የተንኮል መረጃ እንደ እውነት ሊወስዱ የሚችሉ ቅኖችን ከስህተት ለማዳን ዝርዝር መረጃውን ከዚህ በታች አቅርቤዋለሁ፡፡ ምርጫ የሚደረገው በዘጠኝ ክልሎች እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች … [Read more...] about ኤርሚያስ ለገሰ “የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም”
በማይካድራ የጅምላ መቃብር ተገኘ፤ በህወሓት የተገደሉት ቁጥር ከ1300 እንደሚበልጥ ተነገረ
የማይካድራ ከተማ ከንቲባን አቶ ቸሩ ሀጎስ የቀበሌ 01 ሊቀመንበር አብሪሁ ፋንታሁን እና የከተማዋን ነዋሪዎች ጠቅሶ ጌቲ ኢሜጅስ በምስል አስደግፎ ባሰራጨው መረጃ ላይ እንደተገለጸው፤ እአአ ማርች 5/2020 በአቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን የጅምላ ቃብ ውስጥ ከ1300 በላይ የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑ ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል። የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑት እነዚሁ ሟቾች ህወሓት ሳምሪ በሚል ባደራጃቸው ወጣቶች፣ ሚሊሻዎች እና በፖሊሶቹ አማካኝነት የተገደሉ መሆኑን ታዋቂው ዓለምአቀፍ ሚዲያ ጌቲ ኢሜጅስ በዘገባው ጠቅሷል። ሟቾቹ በአከባቢው ላሉ ባለሀብቶች በጉልበት ስራ ተቀጥረው የሚሰሩ ንጹሀን መሆናቸውን ያስታወሰው ዘገባው፤ ገዳዮቹ ቤት ለቤት እየሄዱ የአማራ ብሄር ተወላጆችን እየመረጡ ጭፍጨፋውን መፈጸማቸውን ገልጿል። አብዛኛዎቹ ሟቾች በስለታማ መሳሪያዎች ተጨፍጭፈው … [Read more...] about በማይካድራ የጅምላ መቃብር ተገኘ፤ በህወሓት የተገደሉት ቁጥር ከ1300 እንደሚበልጥ ተነገረ










