“ስብሃትን “አቦይ” አልላቸውም … እንዲህ ዓይነት አባት አልመኝም” ጄኔራል ባጫ የጁንታው ፈጣሪና መሪ ስብሃት ነጋ በመከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስልና ፎቶ ሲስቁ ታይተዋል። በርካቶችም ስብሃት ምን አሉ በሚል ሲነጋገሩ ነበር። ሌፍተናንት ጄኔራል ባጫ ደበሌ እንደገለጹት ስብሃት ከተያዙ በኋላ አስተያየት ሰጥተዋል። ስብሃት በተያዙበት ሰዓት ለከፍተኛ የመከላከያ መኮንኖች፣ “እኛ እኮ ከሞትን ቆይተናል“ የሚል አስተያየት እንደሰጡ ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ስብሃት ከመያዛቸው አስቀድሞ “ቢያዙ ምን ይሉ ይሆን“ ብለው ጄነራሎቹ ይወያዩ እንደነበር የገለጹት ሌፍተናንት ጄነራል ባጫ “ግለሰቡ ቢያዙ ሕገ መንግሥቱ ጥሩ ነው ፤ ሕገ መንግሥቱ እንደዚህ ነው… ብለው ነው የሚያወሩት” የሚል ግምት በጄኔራሎቹ ሀሳብ … [Read more...] about ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው
tplf
“ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ
ስዩም፣ አባይና አስመላሽ ተደመሰሱ፤ ደብረጽዮን 24 ሰዓት ተሰጥቶታል መከላከያ ሠራዊት ስዩም መስፍንን ጨምሮ ሌሎች የህወሓት አመራሮች መደምሰሳቸውን አሳወቀ። ደብረጽዮን በ24 ሰዓት ውስጥ እጁን ካልሰጠ እንደሚደመሰስ ተነግሮታል። የመከላከያ ሠራዊት ሀይል ሥምሪት መምሪያ ሀላፊ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው፣ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ዛሬም እንደ ትናንቱ አስደናቂ ጀግንነታቸውን በአንፀባራቂ ድል ታጅበው በድል መወጣት መቀጠላቸውን ለኢዜአ ገልፀዋል። አሁንም የተቀሩትን የጁንታ አመራሮች የገቡበት ገብተው የማደን ተግባራቸውን አጠናክረው ቀጥለዋልም ብለዋል። የህወሐት ቡድን ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ በስልጣን ላይ እያለ ኢትዮዽያዊ፣ ከስልጣን ሲወርድና የማይመች ሁኔታ ሲፈጠር ደግሞ አገርን የመበታተንና የማተራመስ ስትራቴጂ ነድፎ … [Read more...] about “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ
ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ
ከትህነግ ጎን ተሰልፈው የነበሩ 120 የአፋር ነፃ አውጪ ታጣቂዎች ሀገርን እንዲያፈርሱ በጥፋት ሀይሉ የታቀደላቸውን ጥፋት ተግባራዊ ሳያደርጉ ወደ አፋር ክልል በሰላም እንዲገቡ መደረጉን የሀገር መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል። ለውጡን ተከትሎ ከኤርትራ በርሀ ወደ ሀገር የገቡት “የኡጉጉሙ” ታጣቂዎች ለአንድ ዓመት ያህል በትህነግ ስልጠና ተሰጥቷቸው ለጥፋት ቢዘጋጁም በመከላከያ እና በአፋር ክልል መንግስት የጋራ ጥረት እንዲመለሱ ተደርገው የሰላም ውይይት መጀመራቸው ነው የተገለፀው። ታጣቂዎቹ ሲገቡ የተቀበላቸው፣ ያኔ ለመሰደዳቸው ምክንያት የነበረው ትህነግ እድሉን በመጠቀም ለሌላ ጥፋት እንዳሰማራቸው ከሀገር መከላያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያሳያል። የኡጉጉሙ 120 ታጣቂዎች ለአንድ ዓመት ያህል በትህነግ ስልጠና ተሰጥቷቸው ለጥፋት ቢዘጋጁም፤ በመከላከያ እና በአፋር ክልል … [Read more...] about ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ
ለትምህርት እንዲሆነን
ታላቁ መጽሐፍ የተጻፈበትን ምክንያት ሐዋርያው ጳውሎስ ሲናገር “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር” ተጻፈ ይላል። በአገራችን የፖለቲካ ታሪክ እጅግ ዘግናኝ ጊዜያት አሳልፈናል። በሥልጣን የተቀመጠ የሚወርድ እስከማይመስለውና ሰብዓዊነቱን እስኪዘነጋ ድረስ ሕዝብን ሲበድል ይኖራል። የሕይወቱ መጽሐፍ ሲጠናቀቅ ይሰናበታል። ስንብቱ ግን በአሰቃቂና አሳፋሪ ሁኔታ ሲሆን መመልከቱ በየዘመናቱ የመሰከርነው ሐቅ ነው። ንጉሡ በደርግ ሲተኩ፤ ደርግ “ለለውጥ ባጎፈረው” ህወሓት ሲተካ፤ አሁን ደግሞ አይደረስብንም፣ አንበገርም፣ እንደ ደርግ አንሆንም፣ ዓቅምም፣ ገንዘብም፣ ሁሉም ነገር አለን ሲል የነበረው በረኸኛው የወንበዴ ጥርቅም ከየጉድጓዱና ሰርጡ እንደ አውሬ … [Read more...] about ለትምህርት እንዲሆነን
“ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ
አባይ ወልዱ እና አብረሀም ተከስተን ጨምሮ ዋነኛ የጁንታው አመራሮች የነበሩ በቁጥጥር ስር ውለው ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። አዲስ አበባ ከገቡትና አገርን ለመበታተን አቅደው በመከላከያ ሠራዊት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ካደረጉ አሸባሪዎችና ዋነኛ የጁንታው አመራሮች መካከል፤ አባይ ወልዱ የቀድሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የነበረ አብርሃም ተከስተ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የነበረ ረዳኢ በርሄ የክልሉ ኦዲተር ሃላፊ የነበረ ሙለታ ይርጋ የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊ የነበረ ዕቁባይ በርሄ የሃይማኖት ጉዳይ ክትትል ሃላፊ የነበረ ጌታቸው ተፈሪ የክልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤትና የሠላምና ደህንነት ሃላፊ የነበረ ኪሮስ ሃጎስ የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ የነበረች ንጋቱ አንገሶም አምደማርያም ተሰማ እነዚህ የጁንታው ከፍተኛ … [Read more...] about “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ
የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ
የመከላከያ ሀይል ሰምሪት መምሪያ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው እንዳረጋገጡት 9 የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን 4 የቡድኑ አባላት ደግሞ እርምጃም ተወስዶባቸዋል። የሰሜን ዕዝን በ45 ደቂቃ ውስጥ መብረቃዊ ጥቃት በመፈጸም ከጥቅም ውጭ አድርገነዋል ብሎ የገለፀውን የጁንታው አፈቀላጤ ጨምሮ 4 ከፍተኛ የጁንታው ቡድን አመራሮች ከነአጃቢዎቻቸውና ጠባቂዎቻቸው ተደምስሰዋል። የመከላከያ ሠራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሃላፊ ብርጋዴል ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ እንደገለፁት ሴኩቱሬ ጌታቸውና ዘርአይ አስገዶምን ጨምሮ በርካቶች ሲደመሰሱ ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ እና ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔና ሌሎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። በዚህም መሰረት፣ ዳንኤል አሰፋ (የጌታቸው አሰፋ ወንድም) 1. የጁንታው ቃል አቀባይ ሴኩቱሬ ጌታቸው፣ 2. ዘርአይ አስገዶም … [Read more...] about የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ
ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመቀሌ ከከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር ተወያዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሕግ ማስከበር ሂደቱን ከመሩ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር መቀሌ ላይ ተወያይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአካባቢው ለሕዝቡ እየተደረገ ያለው ሠብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። መቀሌ ላይ በተካሄደው ውይይት ጄኔራል አበባው ታደሰና ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተሳትፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን በውይይቱ ላይ ተናግረዋል። በጁንታው ላይ የተገኘው ድል የሚያኩራራ ሳይሆን 'የምንማርበትና የኢትዮጵያን ቀጣይነት የምናረጋግጥበት ነው' ማለታቸውን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራይን ክልል መልሶ ለማቋቋም መንግስት … [Read more...] about ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው”
“የማይካድራ ጭፍጨፋ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰብዓዊ፣ ስነልቦናዊ ቀውስና ጥልቅ ሀዘን ያስከተለ ነው” – ዶ/ር ዳንኤል
በህወሓት ጁንታ ቡድን ላይ ህግ የማስከበር ዘመቻ መጀመርን ተከትሎ በማይካድራ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመው እልቂት በነዋሪዎች እና በተመልካች ላይ አስከፊ የስነ ልቦና ቀወስ ሊያስከትል እንደሚችል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር (ኢሰመኮ) ዶ/ር ዳንኤል በቀለ አስታወቀዋል። ዶክተር ዳንኤል የማይካድራ ጭፍጨፋ አስመልክቶ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፣ በማይካድራ የተፈጸሙ ግፍ በቁጥር ከሚገለጸው ሪፖርት ባሻገር በነዋሪዎች ላይ ሰብዓዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ እንዲሁም ጥልቅ ሀዘን አስከትሏል። በማይካድራ አማራ እና በወልቃይት ተወላጆች ላይ ያነጣጠረውን ጥቃት ተከትሎ ቤተሰቦች መበታተናቸውንና ሕፃናት ለስነልቦና ቀውስ መዳረጋቸውን የተናገሩት ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል፤ የጭፍጨፋው ሰለባ ቤተሰቦች ህይወታቸውን እንደቀድሞ ለማስቀጠል አዳጋች እንደሚሆንባቸው … [Read more...] about “የማይካድራ ጭፍጨፋ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰብዓዊ፣ ስነልቦናዊ ቀውስና ጥልቅ ሀዘን ያስከተለ ነው” – ዶ/ር ዳንኤል
አምስት ቢሊየን (የሱዳን) ፓውንድ በሱዳን ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረ የወንበዴው አባል ተያዘ
የሱዳን ወታደሮች በሱዳን ግዛት ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረ ኢትዮጵያዊ የሚሊሻ መሪ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታወቁ። የሚሊሻ መሪ ነው የተባለው ግለሰብ በሱዳን ክልል ውስጥ ከህወሓት ወገን ሆኖ ሲዋጋ የነበረ መሆኑንም ሱዳን ትሪቢዩን ታማኝ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። ማንነቱ ያልተጠቀሰው ግለሰብ ከቤተሰቦቹ እና በርካታ ቁጥር ካላቸው ወታደሮችና አጃቢዎች ጋር በገዳሪፍ ግዛት አልፋሻቃ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉም ነው የተገለጸው። በወቅቱም አምስት ቢሊየን ፓውንድ (የሱዳን ይሁን የእንግሊዝ ያልተጠቀሰ)፣ መጠኑ ያልተገለጸ ወርቅ፣ የእንጨት ስራ ውጤቶች እና ሁለት ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ጋር መያዙም ተገልጿል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about አምስት ቢሊየን (የሱዳን) ፓውንድ በሱዳን ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረ የወንበዴው አባል ተያዘ
በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም በዝግጅት ላይ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም በዝግጅት ላይ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ። የከተማው ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር አየልኝ ታክሎ፤ የከተማው ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ጋር ባደረጉት ክትትል ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል። ግለሰቡ ለሽብር ተግባር ለመጠቀም ካዘጋጃቸው 35 ተቀጣጣይ ቁሳቁስ፣ 216 ማሰልጠኛ ማንዋል፣ ሶስት የተለያዩ ባንኮች ደብተር፣ 20 ገንዘብ ገቢና ወጪ ደረሰኝ እና ከአንድ ላፕቶፕ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉንም ተናግረዋል። በግለሰቡና በግብረ አበሮቹ ላይ የሚደረገው ምርመራ እንደቀጠለ መሆኑን የገለፁት ኮማንደር አየልኝ ስለጉዳዩ ዝርዝር መረጃ እንደሚሰጥም ጠቅሰዋል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም በዝግጅት ላይ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ










