• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው

January 14, 2021 01:37 pm by Editor 1 Comment

“ስብሃትን “አቦይ” አልላቸውም … እንዲህ ዓይነት አባት አልመኝም” ጄኔራል ባጫ

የጁንታው ፈጣሪና መሪ ስብሃት ነጋ በመከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስልና ፎቶ ሲስቁ ታይተዋል። በርካቶችም ስብሃት ምን አሉ በሚል ሲነጋገሩ ነበር።

ሌፍተናንት ጄኔራል ባጫ ደበሌ እንደገለጹት ስብሃት ከተያዙ በኋላ አስተያየት ሰጥተዋል። ስብሃት በተያዙበት ሰዓት ለከፍተኛ የመከላከያ መኮንኖች፣ “እኛ እኮ ከሞትን ቆይተናል“ የሚል አስተያየት እንደሰጡ ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ስብሃት ከመያዛቸው አስቀድሞ “ቢያዙ ምን ይሉ ይሆን“ ብለው ጄነራሎቹ ይወያዩ እንደነበር የገለጹት ሌፍተናንት ጄነራል ባጫ “ግለሰቡ ቢያዙ ሕገ መንግሥቱ ጥሩ ነው ፤ ሕገ መንግሥቱ እንደዚህ ነው… ብለው ነው የሚያወሩት” የሚል ግምት በጄኔራሎቹ ሀሳብ እንደነበር ተናግረዋል።

ስብሃት ከተያዙ በኋላም እንደተገመተው፣ አንደኛው ጄኔራል ሲያናግሯቸው “ሕገ መንግሥቱ ጥሩ ነው፤ ተወያዩበት“ እያሉ ሲያወሩ እንደነበር የምዕራብ ዕዝ አዛዥ እንደገለጹላቸው ሌፍተናንት ጄነራል ባጫ ገልጸዋል።

ሌ/ጄኔራል ባጫ ተጫዋች ያሉት የምዕራብ ዕዝ አዛዥ መሰለ ስብሃትን “ስለ ሕገ መንግሥቱ ተወውና አንተ እስኪ ምን ይሰማሃል “ብሎ እንደጠየቋቸው ተናግረዋል። ስብሃት ሲመልሱ “እኔ የሚሰማኝ እኛ ከሞትን እኮ ቆይተናል” የሚል ነው።

“መቼ ነው የሞታችሁት?” የሚል ጥያቄ እንደተነሳላቸው ያስታወቁት ሌ/ጄነራል ባጫ “እኛ የሞትነውማ ኢህአዴግ የሚባለው የጠፋ ጊዜ ነው፤ አሁን የምታደርጉት ምን እንደሆነ ልንገርህ? አሁን እያደረጋችሁ ያላችሁት የቀብር ሥነ ሥነስርዓታችን እየፈጸማችሁ ነው“ ሲሉ ስብሃት ነጋ መመለሳቸውን አንስተዋል።

የጄኔራል ባጫ ንግግር ከዚህ በታች ይገኛል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Politics, Slider Tagged With: meles zenawi, operation dismantle tplf, sibhat, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    January 15, 2021 03:58 pm at 3:58 pm

    መቸውንም ቢሆን ወያኔ ማለት የተንኮል ማሰሮ ማለት ነው። የሚገርመው ግን የሰሜን እዝ ነው። ተደመሰሱ፤ ተያዙ፤ ሞቱ፤ ገደል ገቡ ይሉናል። እሺ ይሁን ገደል ይግቡ ብለን ስንጠብቅ ለሞት አንድ ቀን የቀረውን የወያኔ ቁንጮና የክፋት ውቅያኖስ ስብሃት ነጋን በቃሬዛ ወደ አዲስ አበባ ማምጣት ምን የሚሉት ነገር ነው? የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አያሌ ግፎችን የፈጸመ የወያኔን ትዕዛዝ ፈጻሚ ግፍን በግፍ ላይ የተላበሰ የቁም በድን ነው። አሁን ወያኔ ድል አድርጎ ወታደራዊ መሪዎችን ማርኮና ይዞ ቢሆን ኑሮ በድናቸው በመቀሌ አስፓልት እንደሚጎተት ጭራሽ አያጠራጥርም። ጉድ ያደረጋቸው ከግብጽና ከሱዳን ጋር የገቡት የጦርነት ቀን መማታቱ ነው። ለዛ ነው ሱዳን በመሬት አሳባ ወያኔ የሰሜንን እዝ ባጠቃ በሳምንቱ መሬት ቀምቼ ያዝኩ በማለት የደነፋቸው። በግብጽ፤ በአስመራ፤ በደቡብ ሱዳን የመከረው ጄ/አብዱልፋታህ አልቡርሃን ልቡ የደነደነ፤ እጅ በደም የታጠበ የውጭ ሃሎች መጠቀሚያ ሰው ነው። አሁን ማን ይሙት ሱዳን በጎረቤት ሃገር ላይ ጦርነት የምትከፍትበት ጊዜ ነው? ሱዳን የሚበላ የጠፋበት፤ ኑሮና የዲሞክራሲ ጥማት ያስመረረው ወጣት በሰልፍና በተቃውሞ ምድሪቱን የሚያናውጥበት ያልተረጋጋ መንግስት የቆመላት በግብጽ እንደ ጀልባ የምትገፋ ሃገር ናት። ግን የወያኔም ሆነ የሱዳን ጦርነት መክፈት ለግብጽ የህዳሴ ግድቡን ለማጥቃት እንዲያመቻት የተሰላ ሂሳብ ነው። አቅጣጫ ማስቀየሪያ ስልት። ከዚያ ቀደም ብሎ የተደረገው የጦር ልምምድም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው። በቤኒሻንጉልና ጉምዝ፤ በመተከልና በወለጋ አማራን ብቻ ለይቶ የማጥቃቱም ብልሃት የተነደፈው ከእነዚህ ሃይሎች ነው።
    አሁን በቅርቡ ከገዳሪፍ የደረሰኝ ጥቆማ እንደሚያስረዳው ከየስፍራው አምልጠው ወደ ሱዳን የገቡት የወያኔ ስመ ጄኔራሎችና ባለሌላ ማእረጎች አብረው ከሱዳን ጦር ጎን እንደተሰለፉ የአይን እማኝ ነግሮኛል። በአማካሪነት ደግሞ የግብጽ ሰዎች በቅርብና በሩቅ እንዳሉበት ተደርሶበታል። በዚህም የተነሳ ለኢትዮጵያ እየሰለላችሁ ነው በማለት ብዙ ሃበሾችን ሰብስበው አስረዋል። በትግራይ ተቆርጦ ቀረ የተባለው ጦር ከየስርቻው እየተጠራራ በመሰባሰብ ውጊያ ከፍቶ ችግር እንደፈጠረ ሰምተናል። ወደ 200 ሺህ ሰራዊት አለን ይሉን የነበሩት የክልሉ መሪ ደብረጽዪንና የክፋቱ ኮሮጆዎች ሁለቱ ጌታቸው ደርሰንባቸዋል፤ ተከበዋል፤ ሽማግሌ ልከናል ወዘተ የሚለው ዋጋ የለሽ ወሬ ያሰለቻል። ባለ በሌለ ሃይል ሳይውል ሳያድር ካልተደመሰሱ በስተቀር በራሱ ጥላ ለሚደነብረው ታፍኖ የኖረ ህዝብ እፎይታ አይሰጥም። ይባል አልነበረ ስብሃት ነጋ አፋፍ ላይ ደርሷል? እሱ እንኳን አፋፍ ሊወጣ ተደግፎም መራመድ እንደተሳነው የታመነው ተይዞ ከታየ በህዋላ ነው።
    የአለም የፓለቲካ ንፋስ ቅጡ ጠፍቶታል። ትላንት አለምን ስለ ዲሞክራሲ እናስተምራለን ይሉን የነበሩት አሜሪካኖች በታሪካቸው ታይቶ በማይታወቅ ሃገር በቀል ሽብር ታምሰዋል፤ ገናም ይታመሳሉ። እብዶች ስልጣን ሲጨብጡ የሚሉን ለሃገር ለወገን ነው ይሉና እርስ በእርስ ያጫርሳሉ። የአሜሪካም እድል ፈንታ ገና አለየለትም። ተምረናል፤ አውቀናል፤ ለሃገራችን ቁመናል የሚሉ የህዝብ ተወካዪች በፓርቲ ከለላ ከውሸት ጋር ሲቆሙ ማየት አሜሪካ ሂትለርን ልትመርጥ የቀራት አንድ እርምጃ ብቻ ነው። ሌላው ሁሉ ተንጋሎ መትፋት ነው። ጉረኛውና በውሸት ብቻ ያለምንም መረጃ አራት አመት ሙሉ አለምንና አሜሪካን እያመሰ ያለው ዶናልድ ትራምፕ በዪክሬን ሰበብ መጀመሪያ ላይ ከስልጣን ወርዶ ቢሆን ኑሮ ዛሬ ይህ ሁሉ ችግር ባልተፈጠረ ነበር። ግን የፓለቲካና የቡድን ጽዋ የጨለጡት እውነትን በውሸት ለውጠው ስለታደጉት ዛሬ ለተፈጠረው የከፋ ችግር መንገድ ጠራጊ ሆኗል። ያለምንም መረጃ ስፓንሽ ሳህራ (ሳህራዊ) ለሞሮኮ፤ በሱዳን፤ በባህረ ሰላጤው ሃገራት ሰላምን አመጣሁ እስራኤልና የአረብ ሃገሮች ሰላም ፈጠሩ የሚባለው ሁሉ ለጊዜ ፍጆታ እንጂ በአንድ ጀምበር የሚፈርስ የእንቧይ ካብ ነው። ለፓለቲካ ፍጆታ የተነፋ ጥሩንባ! ቱርክ ሃይሏን አንሰራርታ ከአውሮፓ እስከ አፍሪቃ እኔን ስሙኝ ስትል፤ ቻይና በኢኮኖሚ ጥቅማ ጥቅም አሳባ አፍሪቃን በእጇ አስገብታለች። ወደ 55 ሃገሮች ያሉበት የአፍሪቃ አህጉር እንደ ቀድሞው አሁንም የቀጥታና የእጅ አዙር ሃይሎች የሚቀራመቱት ምድር ሆኗል።
    አቶ ስብሃት እንዳለው “ከሞትን ቆይተናል” ነውና ዛሬ በሃጉሩ ውስጥ ለመኖር ባለመቻላቸው በየመንገድ፤ በየባህሩ ጉዞ ከሞት ተርፈው፤ በየሰው ቤት በግድና በውድ የባርነት ኑሮ የሚኖሩ እህትና ወንድሞቻችን እልፍ ናቸው። እኛም ለዘመናት ስንጠላለፍ ካለንበር ኑሮ እልፍ ሳንል በየክልላችን ባንዲራ እናውለበልባለን። ሲያሳዝን። ሰው በሰው የጭቃ ቤት ቀንቶ እሳት የሚለኩስበት፤ ከክልሌ ውጣ ብሎ አንገት ከሚቆርጥበት ምድር ላይ ቆመን ሽምግልና፤ ልመና፤ ፍትህ ወዘተ ስንል እገረማለሁ። ባጭሩ ሥራ በልብ ነበር። አሁን ግን ሁሉ ነገር በቴሌቪዝን መስኮት ላይ ሆኖ መለፍለፍ ነው። ምን አለበት ሁሉም ነገር ሲጠናቀቅ ቢወራ? ደግሞስ ተደመሰሱ ስትሉን ከእናንተ ጎን የሞተ የለም ማለት ነውን? የማይታመን ነገር? በጦርነት መካከል ቀዳሚ ሟች እውነት ስለሆነች ሁሉንም ነገር ፈትሾና አመሳክሮ ካልሆነ በስተቀር የተሰማውንና የታየውን ሁሉ ሳያልሙ መሰልቀጥ ማወራረጃ ፍለጋ ይሰዳል። አሁን ስዪም መስፍን ሞቷል ተብሏል፡ ቆሞ ሲሄድ ቢታይ የሚቀጥለውን ወሬ የሚታመን ያደርገዋል። ያው እሱ በህይወት እያለ “ባድመ ለእኛ ተፈረደ” እንዳለው አይነት አማች ዜና። እኔ እማዝነው ለተሰላፊዎች፤ ከበሮ እየመቱ ለሚዘፍኑ፤ ትላንትም ዛሬም በሰው ሞት እልል ለሚሉ። ማብቂያው መቼ ነው? ለምንስ እንገዳደላለን? አሁን እውነት ሱዳን በኢትዮጵያ ላይ ጦርነቱ እንዲቀናት የሚጽፉና የሚናገሩ ሰዎች ጤነኞች ናቸው? ለዛ ነው የጥቁር ህዝብ መከራ ይበልጡ የሚመነጨው ከራሳችን ነው የምለው። አይ ሃገር እንዲህ ነው ሲገሉ፤ ሲገዳደሉ፤ በሰው እንባ ክራር እየመቱ ሲጨፍሩ መኖር። ዘርፎና አዘርፎ መኖር። ያለፈው ክፉ ነው እያሉ የዛሬውን የባሰ ሲኦል ማድረግ። እንዲህ ናት ለውጥ… ድንቄም። በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule