• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ለትግራይ እንደ ጫማ ሶል ሆነን ነው ስናገለግል የነበረው … ለእኛ ይህ አይገባም ነበር” – ብ/ጀነራል ናስር አባ ዲጋ

June 23, 2021 11:41 am by Editor 2 Comments

የክፋት አለቃው ህወሀት መራሹ ወንበዴ ቡድን በክፋት ሰይፉ ጉዳት ካደረሰባቸው የሰራዊት ክፍሎች መካከል ብ/ጀነራል ናስር አባዲጋ የሚመሩት የ8ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ይገኝበታል።

ሜካናይዝድ ክፍለ ጦሩ የደረሰበትን የክፋት ጥቃት ተቋቁሞ ሃይሉንና ትጥቁን በመያዝ እየተዋጋ ወደ ጎረቤት ሃገር ኤርትራ ከተሻገረ በኋላ እንደገና ሃይሉንና ትጥቁን አቀናጅቶ እየተዋጋ የገባ ክፍለ ጦር ነው።

እስከ ሽራሮ እየተዋጋ መጥቶም፣ ከሰሜን ምዕራብ ግንባር ዳንሻ ጀምሮ እየተዋጋ ከመጣው ምዕራብ ዕዝ ጋር በመቀናጀት እስከ መቀሌ ከዛም ጁንታው ተበጣጥሶ በረሃ እስከገባበት ጊዜ ድረስ በውጤት እርቀቱ ሆኖ ከባድ ምት በማሳረፍ የነበረው ሚና በቃላት ከሚገለፀው በላይ ነው።

መቀሌን እንደተቆጣጠርን የሜካናይዝድ አዛዡን ብ/ጀነራል ናስር አባዲጋን አግኝቼ ስለ ጥቃቱ አናግሪያቸው ነበር። እሳቸውም የሚከተለውን ብለውኛል።

ሰራዊቱ የገባውን ቃል ኪዳን ለመፈፀም ምሽግ ላይ በነበረበት ከጀርባው ቃላት በማይገልፀው ጭካኔ በጥይት ተመቷል, በሳንጃ ታርዷል። በውድቅት ሌሊት በተኛበት እጅ ወደ ላይ እያሉ ከልጁ እና ከሚስቱ እየነጠሉ በክፋታቸው በልተውታል። ድርጊቱ የሰው ልጅ ሆኖ ሰው ላይ የሚፈፀም አይደለም። በውትድርና አገልግሎት ዘመኔ እንደዚህ አይነት ክህደትም ጭካኔም አይቼም ሰምቼም አላውቅም። ድርጊታቸው አረመኔያዊ ነው።

ለምሳሌ ታንክ ሾፌር በምንም አይነት ጭንቅላቱን አይመታም። ጠላት ከገባ ቦንብ ወርውሮ ታንክ ጋር ምድብተኛውን ያቃጥላል እንጂ። በነፍስ ወከፍ ጥይት ግን ጭንቅላት አይመታም። ይህን ያደረገ ውስጣችን የተደራጀ ጠላት ነው። የጠነከረብንም ውስጣችን የተደራጀው ጠላት ነው። በዚህም ብዙ ጎድተውናል። ነገሩ በጣም ዘግናኝ ነው።

ጥቃቱን የፈፀሙበት እለት መብራትና ኔትወርክ አጥፍተው ነበር። ሃሳባቸው በተኛንበት የቻሉትን ገድለው የቻሉትን ማርከው መሳሪያ መቀበል ነበር። ግን አልተሳካላቸውም። የመጣ መኪና ከ40 በላይ ነው። ለሰላሳ ሰዓታት ያክልም ያለማቋረጥ ተዋግተናል። ውጊያውን ማሸነፍ እንደማይችሉ ሲያውቁ ልዩ ሃይል ኮማንዶ ከቤተ መንግስት እናስመጣለን እያሉ ነበር። ይህም ጀግንነታችን አላስቆመውም።

መጨረሻ ላይ ሙሉ ሃይላችንን ይዘን ወደ ጎረቤት ሃገር ኤሪትራ ተሻገርን። እንደ ክፍለ ጦር እስታፍ ደግሞ 85 ፐርሰንቱ ትግሪኛ ተናጋሪዎች ነበሩ – በተለይ በሀላፊነት ቦታ። ውጊያው ከነዚህ ጋርም በመሆኑ ነው የከበደን። ነገሩን ይፋ ሳያወጡ ውስጥ ለውስጥ ብዙ ነገሮችን ሰርተዋል። መገናኛ አካባቢ ትልቅ እንቅፋት ፈጥረዋል።

ግምጃ ቤትም ከፍተው አስታጥቀዋል። ንብረት ጫን አትጫንም ከፍተኛ ችግር ፈጥረዋል። የተሽከርካሪ ነዳጅ ለመሙላት ብዙ አስተጓጉለውናል። መጨረሻም ዝገግጅታችን ጨርሰን ወደ ጓል ባድመ ተንቀሳቀስን። ወደዛ እየሄድን እንደሆነ እኔ እና ኮሚቴዬ ነበር የምናውቀው። ኮሚቴዬ ግን የምናደርገውን ሁሉ ለጁንታው አለቆች ያሳውቅ ነበር። በጉዟችንም ብዙ እንቅፋቶች ተፈጥረዋል።

እንቅፋቶችን እያስወገድን ጓል ባድመ እንደደረስንም ከሌሎች አሃዶች ጋር መልሶ መቋቋም አድርገን እንዋጋለን ብለን ተነሳን። ከማዕከል ከመጡ አመራሮቻችን ጋር ተገናኝተን ስለ ሁኔታው ተነጋገርን። በጥቃቱ ሰራዊቱ እጅግ ተቆጥቷል። ፈጥነን ገብተን ለምን አንደመስስም የሚል ከፍተኛ ተነሳሽነት ፈጥሯል።

ለሰዎቹ የመጨረሻ ቅጣት ሞት ቢባል እንኳ ሞት ያንሳል። አንድ ሺ ጊዜ ቢሞቱም ቅጣት አይሆንም። ቤተሰብ ነበርን። አንድ ነበርን። ብዙ ነገሮችን አብረን አሳልፈናል። እኔ ወደ ትግራይ ምድር የገባሁት ከኢትዮ-ኤሪትራ ውጊያ ጀምሮ ነው። ያ ማለት ወደ ሃያ ሶስት ዓመት ያክል ሆኖኛል ማለት ነው። በዚህ ዓመት ውስጥ የሰራነው ቀላል አይደለም። ትግራይ ለማች የምትባለው በኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት ነው። በወታደሩ ደሞዝ ጭምር ነው። በተለይ መከላከያን ይመለከታል።

ትግራይ በተፈጥሮ ሃብት ልማት ተሸላሚ ነበረች። ማንም የተከለው አይደለም። 80 ፐርሰንት ሰራዊቱ በጉልበቱና በገንዘቡ የተከላቸው ችግኞች ናቸው። ብዙ ትምህርት ቤቶችና መንገዶች ሰርተናል። ከጀርባ ሊወጉን እየተዘጋጁ እንኳ ት/ቤት ገንቡልን የሚል ጥያቄ አንስተዋል። ለዚህ ግንባታ ነው ሰራዊት ቀስቅሰን ብር እየሰበሰብን የነበረው። ሽሬ ላይ ለሚኖሩ አካል ጉዳተኞች የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እስከ አራተኛ ፎቅ ድረስ ገንብተናል። ለዚህ ግንባታ ኮሚቴው እኔ ነኝ የነበርኩት። ሰራዊቱም ገንዘቡን ለማዋጣት አይሰስትም ነበር።

ሰራዊታችን ከዓመት ዓመት ሙሉ ደመወዙን ወስዶ አያውቅም። ጥቃቱ የደረሰ ዕለት እንኳ በክልሉ በስፋት የተከሰተውን አንበጣ ለመከላከል ከህዝቡ ጋር ስራ ነው የዋልነው። በአጠቃላይ ለትግራይ እንደ ጫማ ሶል ሆነን ነው ስናገለግል የነበረው። አንድም ቀን እነሱን የሚጎዳ ነገር አስበንም አድርገንም አናውቅም።  

ለእኛ ይህ አይገባም ነበር። ሰራዊቱን ያስቆጣውም ያነሳሳውም ይህ ነው። ሁሉንም አውዶች በጀግንነት ነው ሲፈፅሞ የነበረው። ውጊያው በአጭር ጊዜ የተቋጨውም ለዚህ ነው። በተገኘው ድል ደግሞ ከምናገረው በላይ ደስተኛ ነኝ። የሜካናይዝድ ክፍለ ጦሩ አባላትም እንደዛው። አሸናፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ነውና!

ታገል አልማው
ፎቶግራፍ ሽመልስ እሸቱ (መከላከያ ፌስቡክ)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, News, Politics Tagged With: general nasir abadiga, operation dismantle tplf, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Bekele Gebre says

    June 24, 2021 12:49 am at 12:49 am

    TPLF is brutal and inhuman. For long Ethiopians debated that TPLF and Tigray people are not one & the same. But now situations are indicating that most are lining behind the terrorist TPLF and fighting the national defense force that brings nothing to the poor Tigrean excepting suffering while TPLF fighting for power and misappropriation of national wealth as seen while they were in power. Even if they request for referendum for session, they end up in unbelievable suffering of the poor and nothing more.

    Reply
  2. Tesfa says

    June 27, 2021 03:17 pm at 3:17 pm

    ቂል ብቻ ነው ወያኔን አምኖ የሚጠጋ። ከበረህ እስከ ከተማ ያለው ታሪካቸው በደም የተጨማለቀ ነው። ግፍ ለእነርሱ ምሳና ቁርስ ነው። በአንጃ ስም በየጊዜው በትግራይ በረሃ የተገደሉ የትግራይ ልጆች ደም ዛሬም ለፍትህ ይጮሃል። ሰሚ ግን የለም። ግን በመንጋ አስተሳሰብ ለሚንጋጋ የዘርና የጎሳ ፓለቲከኛ እውነትን ፍትሾ ከእውነት ጋር መሰልፍ አዳጋች ነው። ያው አንድ እንቁራሪት ሲንጫጫ ሌላው እንደሚንጫጫው ሁሉ አብሮ መንጎድ ነው። አሁን ከጌታቸው ረዳ ጋር አብራ ፎቶ ተነሳች የተባለችው የእርዳታ ሰራተኛ በእኔ ግምት ትጥቅና ስንቅ አቀባይ እንጂ እርዳታ ሰጪ አይደለችም። ይህ በፊትም ሲሰራበት የኖረ ነው። ወያኔ የኢትዮጵያን ስም በዓለም መድረክ ላይ አጠልሽቶ ራሱን በጉቦና በሌላም መንገድ እያጎላ ለዘመናት መለያየትን ሲያራምድ ቆይቷል። ለነጩ ዓለም የተሰበከለት እኛ አናሳዎች ስለሆን ለዘመናት በአማራ ተጨቁነናል እያሉ ነው። በትግራይ መሬት አሁን የሚንጋጉት ስመ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ይበልጦቹ የስለላ መሳሪያዎች ናቸው። ይህን ካለፈ ታሪክ ጋር ማመሳከር እውነትን ለመረዳት ይረዳል። ለትግራይ ህዝብ ተላከ፤ ተሰጠ፤ እየተባለ በየሚዲያው የሚናፋው የምግብና የልብስ አልፎም የገንዘብ እርዳታ ለህዝቡ እንዳለ አይደርስም። ካርቱም ገቢያ ላይ ያለውን እቃ፤ ገዳሪፍ ላይ ያለውን የእህልና የቁሳቁስ በግልጽ ሽያጭ ያየ ምን እንደምል ሊገባው ይችላል። እነዚህ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች በየምክንያቱ የእርዳታውን መጠን ካመነመኑት በህዋላ ተራፊው ደግሞ በሃገር ውስጥ ሌቦች ተመዝብሮና በወያኔ የጠለፋ ቡድን ተጠልፎ ትንሽዬ ነገር ብቻ ናት ለተረጂው ህዝብ የሚደርሰው። አሁን ጉልበቴን አጠናክሬ ይህን ሥፍራ ነጻ አወጣሁ፤ ያን ያዝኩ፤ ደመሰስኩ፤ ገደልኩ የሚሉት የወያኔ አፈ ቀላጤዎች በውጭና በሃገር ውስጥ አፍቃሪ ኢትዮጵያ የሆኑ ድህረ ገጾችን በማበላሽት፤ በመጥለፍ፤ በማሰናከል የተሳሳተ መረጃ ለዓለም ህዝብ በመበተን፤ ለትምህርት ተቋማትና ለሥራ ቦታዎች የፈጠራ ወሬ ያዘለ ደብዳቤ በመጻፍ፤ ሰዎችን ከመኖሪያ ቤታቸው ድረስ በመሄድ በማስፈራራት፤ በስልክ ወዪልህ እንገልሃለን/ልሻለን በማለት አጥብቀው እየሰሩ እንደሆነ ጎልቶ ይታያል። ሲልላቸው በደቦ ተሰባስበው አንድን ምስኪን ወይም አንዷን ምስኪን በመቀጥቀጥ የትግራይን ህዝብ መከራ እናስቆማለን ብለው የሚያስቡ ወራዶች በዓለም ዙሪያ ይራወጣሉ። የችግሩ ፈጣሪ እኛ፤ የችግሩም መፍትሄ በእጃችን ነው የሚሉት እነዚህ ጎዶች መብረቃዊው ጥቃታቸው በራሳቸው ላይ ቶርኔዶ ሲሆንባቸው ከእብደታቸው መማር እንዴት እንዳልቻሉ ይገርመኛል። በወያኔ አሳሩን የሚበላው የትግራይ ህዝብ አንዴ ሻቢያ መጣብህ፤ ሌላ ጊዜ ብልጽግና ሊያርድህ ነው ሲባል ሁሌ ውሸት እንደጋቱት ይኽው ለዚህ በቅተናል። እኔ የሻቢያም ሆነ የብልጽግና ጠበቃ አይደለሁም። ፓለቲከኛ ሆኖ በድርጅት ራሱን አስጠልሎ ሽንክ ያልሆነ ፍጡር በምድር አይገኝም። ግን ሰው ሰው መሆኑ ቀርቶ እንስሳ ሲሆን ማየት ምንኛ ያሳዝናል። የሰሜን እዝ ለትግራይ ህዝብ ያልሆነለት የለም። ብዙ አርገናል ይባላል። ያን ማን ከዳ? የትግራይ ህዝብ እኮ አፍ አውጥቶ ምንም ያረጋቹሁት የለም አላለም። እናውቅልሃለን የሚሉት የወያኔ ስብስቦች ባላወቀው ጦርነት ውስጥ ማግደው አሁን እንሆ ባይተዋር አድርገውታል። ሰው ከዘሩ ውጭ በተሰላ አስተሳሰብ ካልተራመደ አጥርቶ ማየት አይቻለውም። የአሁን የነጮች ጋጋታና ከልክ ያለፈ የሚዲያ ሽፋን ሌላ ላቅ ያለ ወሬ ሲገኝ የወያኔው ጉዳይ ማገዶ ይሆናል። እንዴት ጥቁር ህዝብ የነጭንና የዓረብን ተንኮል መረዳት ይሳነዋል? ዋናው የእነርሱ መሪ ቃል “እሾህን በእሾህ” ነው። እንድንገዳደል፤ ቤታችን እንድናቃጥል ሁሌ የእነርሱ ተመጽዋች እንድንሆን ይሻሉ። በፊትም ዛሬም ያደረጉትና የሚያደርጉት ይህኑ ነው።
    ጄ/ሉ ለትግራይ እንደ ጫማ ሶል ሆነን ነው ያገለገልነው ማለታቸው ያው ህዝብን የሚያገለግል ብሄራዊ ሃይል እንደዛ ነው ተግባሩ። ግን ወያኔ ያን ያህል ተደራጅቶ በሰራዊቱ አደጋ እስኪያደርስ ድረስ ምንም ጭምጭምታ አለማግኘቱ ምን ያህል የወያኔ አመራሮች ሰራዊቱን ኩበት ለቀማ ይልኩት እንደነበር ያሳያል። የሰራዊቱ የስለላ መረብ ፍሬ ቢስ እንደሆነም ነው የሚያመላክተው። ተተኪውን ጄ/ል ከመቀሌ አየር ማረፊያ ሲመልሷቸው እንዴት ሰው አይነቃም? ጡረታ የወጡት የወያኔ አመራሮች መቀሌን ሲያጨናንቋት የታሰበ ነገር እንዳለ እንዴት መገመት ይከብዳል። አንድ መኮነን ሲናገሩ “እኛ ከውስጥ እንወጋለን ብለን አስበን አናውቅም”። ታዲያ ማንን ነበር በመቀሌው ሰልፍ ላይ ኑና ግጠሙን እናሳያችሁሃለን እያሉ ወያኔ ሲፎክር የነበረው። ይገርማል። በእውነት የሰሜን እዝም ሆነ ሌላው የሰራዊት ክፍል ከዚህ ስህተት ተምሮ ጠንካራ የስለላ መረብ ይዘረጋ ይሆን? ይመስለኛል። ካለሆነ ተመልሶ መሸወድ ነው። ጊንጥ ኪሱ ከቶ አልነደፍም የሚል ሰው እብድ ነው። ወያኔ ሰው ገድሎ የሚያፋልግ ከጀርመኑ ናዚ ጋር የሚነጻጸር ከሰው ስብዕና የወጣ የቡድን ድርጅት ነው። አሁንም የትግራይን ልጆች የሚያስጨርሰው ከዚያው ከመቀሌ በፓሊስ፤ በሲቪል፤ በጊዜአዊ መንግስት ተቋም ውስጥ ተሰግስገው የሚገኙ ወያኔ አፍቃሪ ሃይሎች በሚያቀብሉት መረጃ ነው ሰው በየደረሰበት እንደ እርድ ከብት ተቆራርጦ የሚጣለው። ይህ ለትግራይ ህዝብ ማሰብ ከሆነ የቁም እብደት ነው። እውነቱ ግን ለራስ ስልጣን የሚያስብ ማንም መንግስት/ሃይል ቢሆን በደም መታጠብን እንደ ውሃ ነው የሚቆጥረው። ተልካሻና ትርፍ የለሽ ፓለቲካ ከዘመናት በህዋላ ዞሮ ተመልሶ ገድልና ጫካ ቤቴ ነው ብሎ በእርጅና ይታገላል። የሮም አወዳደቅ ይሉሃል እንዲህ ነው። በሌላው ሞት መሳቅ የራስ ቀን እስኪመጣ ድረስ!
    ወያኔ የተበተነ ድቄት፤ ተደመሰሰ፤ ሃገር ጥሎ ጠፋ፤ ታሰረ ተፈታ ገል መሌ መባሉ ሁሉ ወሬ ነው። ወያኔ ማለት የካብ እባብ ማለት ነው። አንድ ጋ ታይቶ ሌላ ጋ። ምንም የሚሞቱ አይደሉም። ክፋት መሪያቸው ነው። ነጩና አረቡ አለም ምግባቸው ነው። ዛሬም ወደፊትም ሲገድሉ፤ ሲያፈርሱ፤ ሲገዳደሉ ይኖራሉ። ለወያኔ መዘናጋት ሞትን መጋበዝ ነው። መምጫቸው አይታወቅም። ነጭ ይልኩብሃል። አረብ ይቀጥራሉ። አማራውን ይደልላሉ፤ ኦሮሞውንና ሌላው ተጨቆንክ ና እኛ ቀን እናወጣልሃለን እያሉ መላሾ ይሰጣሉ። ልብ ያለው ሁሉን ይመረምራል። እስቲ ይታያችሁ እንዴት ባለ ሂሳብ ነው ወደ ኤርፓርት የሚሄድ ኢንጂኒየር ተጠልፎ ስጋው ተቆራርጦ በመቀሌ የተገኘው። እንቅስቃሴውን የሚከታተሉ በየጊዜው ሪፓርት የሚያረጉ እዚያው ከጸጥታ አስከባሪዎች መካከል ወያኔዎች አሉ። ይከፈላቸዋል። የደም ሃብት ይሉሃል እሱ ነው። ፍትህ ለትግራይ ህዝብ። ሞት ለወያኔ! በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule