የማይካድራ ከተማ ከንቲባን አቶ ቸሩ ሀጎስ የቀበሌ 01 ሊቀመንበር አብሪሁ ፋንታሁን እና የከተማዋን ነዋሪዎች ጠቅሶ ጌቲ ኢሜጅስ በምስል አስደግፎ ባሰራጨው መረጃ ላይ እንደተገለጸው፤ እአአ ማርች 5/2020 በአቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን የጅምላ ቃብ ውስጥ ከ1300 በላይ የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑ ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል።
የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑት እነዚሁ ሟቾች ህወሓት ሳምሪ በሚል ባደራጃቸው ወጣቶች፣ ሚሊሻዎች እና በፖሊሶቹ አማካኝነት የተገደሉ መሆኑን ታዋቂው ዓለምአቀፍ ሚዲያ ጌቲ ኢሜጅስ በዘገባው ጠቅሷል።
ሟቾቹ በአከባቢው ላሉ ባለሀብቶች በጉልበት ስራ ተቀጥረው የሚሰሩ ንጹሀን መሆናቸውን ያስታወሰው ዘገባው፤ ገዳዮቹ ቤት ለቤት እየሄዱ የአማራ ብሄር ተወላጆችን እየመረጡ ጭፍጨፋውን መፈጸማቸውን ገልጿል።
አብዛኛዎቹ ሟቾች በስለታማ መሳሪያዎች ተጨፍጭፈው የተገደሉ ሲሆን፤ በዚህ ጭካኔ ከተሞላበት ጥቃት ነፍሳቸው የተረፈችው ደግሞ በጥይት እንደገደሏቸው ነው ዘገባው ያስታወቀው።
ሟቾቹ በወቅቱ በየመንገዱ ዳር፣ በውሃ መፈሳሻ ቦይዎች፣ በህወሓት አመራሮች በተቆፈሩ ጉድጓዶች እና በእርሻ ቦታዎች ላይ ተጥለው እንደተገኙም ገልጿል።
በማይካድራ አካባቢ አሁንም ድረስ የሟቾች አስከሬን በተለያዩ ቦታዎች እየተገኘ መሆኑን ዘገባው ጠቁሟል።(ኢ ፕ ድ)
ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply