የፕሬዚዳንት ባይደን የቅርብ ወዳጅ የሆኑት ሴናተር ክሪስቶፈር ኩንስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ለማነጋግር አዲስ አበባ መጥተው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን አነጋግረዋል። የኋይት ሐውስ የፕሬዚዳንቱ የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ የሆኑት ጄክ ሱለቫን ባወጡት አጭር መግለጫ እንዳሰፈሩት በትግራይ አለ በሚባለው የሰብዓዊ መብት ገረጣና ሰብዓዊ ቀውስ ባይደን ያላቸውን ትልቅ ጭንቀት ሴናተር ኩንስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንደሚያቀርቡ ነበር የጠቆሙት። በተጨማሪም ሁኔታው የአፍሪካ ቀንድን አለመረጋጋት ውስጥ ሊከተው የሚችል በመሆኑ ሴናተሩ ከአፍሪካ ኅብረት ጋር እንደሚመክሩበት አማካሪ በመግለጫቸው አመልክተው እንደነበር ይታወሳል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ በተገኙበት አቶ ደመቀ ተቀብለው አስፈላጊው ማብራሪያ እንደተሰጣቸው የውጭ ጉዳይ … [Read more...] about አሜሪካ በሴናተሯ አማካይነት “ለቅሶ” ደረሰች