• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የስኳር ፋብሪካዎች ተሽጠው ዕዳቸውን እንዲከፍሉ ተወሰነ

April 14, 2021 08:53 am by Editor Leave a Comment

በመንግሥት ባለቤትነት ሥር ከሚገኙት 13 ስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ አሥሩ ለግል ባለሀብቶች ተሸጠው፣ ከሽያጩ የሚገኘው ገቢ በከፍተኛ የዕዳ አጣብቂኝ ውስጥ ናቸው ተብለው ለተለዩ ሰባት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ዕዳ ክፍያ ጥቅም ላይ እንዲውል ተወሰነ።

ሪፖርተር ያገኘው መንግሥታዊ መረጃ እንደሚያመለክተው ሰባቱ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ካለባቸው አጠቃላይ ዕዳ ውስጥ፣ አመዛኙ እንደ አዲስ ወደ የሚቋቋመው ኮርፖሬሽን እንዲዘዋወር ተወስኗል። 

አዲስ የሚቋቋመው ተቋም “የዕዳና ሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን” የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፣ ኮርፖሬሽኑን ለማቋቋምም የሚያስችል ደንብ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በሚኒስትሮች ምክር ቤት መፅደቁ ይታወቃል። 

ኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ የዕዳ ጫና ውስጥ ወድቀዋል ተብለው ከተለዩት ሰባት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አጠቃላይ ዕዳ ውስጥ፣ ኮርፖሬሽኑ አመዛኙን በመውረስ ዕዳቸውን የመክፈል፣ እንዲሁም ድርጅቶቹን ከዕዳ አስተዳደር ወጥተው ትርጉም ያለው ኢኮኖሚያዊ ተልዕኮ እንዲወጡ የማስቻል አስተዳደራዊ ሚናም ተጥሎበታል። 

በመንግሥት የተለዩት ሰባቱ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ ኢትዮ ኢንጅነሪግ ግሩፕ (የቀድሞው ሜቴክ)፣ ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን፣ የኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽንና ስኳር ኮርፖሬሽን ናቸው።

እነዚህ ድርጅቶች ከአገር ውስጥ አበዳሪዎች በዋናነት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ከውጭ አበዳሪዎች ተበድረው ያልመለሱት አጠቃላይ ዕዳ 780 ቢሊዮን ብር ወይም 19.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ፣ ገንዘብ ሚኒስቴር ሰሞኑን ይፋ ያደረገው መረጃ ያመለክታል።

አዲስ የሚቋቋመው ኮርፖሬሽን ሰባቱ ድርጅቶች ካለባቸው 780 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 570 ቢሊዮን ብሩን ወርሶ የመክፈልና የማስተዳደር ኃላፊነት ተጥሎበታል።

ኮርፖሬሾኑ የሚቋቋመው ራሱን በቻለ የንግድ ተቋም አደረጃጀት እንደሚሆን፣ ኃላፊነቱን ለመረከብ የሚያስፈልገው የመጀመርያ ካፒታልም ከመንግሥት በጀት ውጪ እንደሚሆን መረጃው ያመለክታል። 

በመሆኑም አሥር የመንግሥት ስኳር ፋብሪካዎችን በመሸጥ የሚገኘው ገቢ ኮርፖሬሽኑ ለሚያስፈልገው የመጀመርያ ካፒታል ፈሰስ እንዲደረግ የተወሰነ ሲሆን፣ ከስኳር ፋብሪካዎቹ ሽያጭ ከሚገኘው ገቢ በተጨማሪ በቅርቡ ለውጭ ኩባንያዎች ከሚሰጠው የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ ክፍያ፣ እንዲሁም ከኢትዮ ቴሌኮም ከፊል ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ትልቅ ድርሻ ወደ ኮርፖሬሽኑ ፈሰስ እንዲደረግ መወሰኑ ታውቋል።

መንግሥት በመጀመርያ ይዞት የነበረው ዕቅድ 13 ስኳር ፋብሪካዎችን ለመሸጥ የነበረ ሲሆን፣ ይህንንም ወደ ተግባር ለመቀየር የሁሉም ፋብሪካዎች አጠቃላይ ሀብትና ንብረት በገለልተኛ የኦዲት ኩባንያ እንዲገመት አድርጓል።

ይህንን የሀብትና ንብረት ግመታ እንዲያከናውንም ቡከር ቴት የተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ ተቀጥሮ የግመታ ሥራውን ከዓመት በፊት አጠናቆ፣ ሪፖርቱንም ለመንግሥት እንዳቀረበ የተገኘው የሰነድ መረጃ ያመለክታል።

ኩባንያው ባካሄደው የግመታ ሥራ የ13 ስኳር ፋብሪካዎችን አጠቃላይ ሀብትና ንብረት ከዓመት በፊት በነበረ ዋጋ መሠረት 88 ቢሊዮን ብር ገምቷል። 

ይሁን አንጂ በተመሳሳይ ወቅት የነበረው የስኳር ፋብሪካዎቹ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ዕዳ ወለድን ሳይጨምር ብቻውን 81.6 ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን፣ በዚህ ተመሳሳይ ወቅት የፋብሪካዎቹ አጠቃላይ የውጭ ዕዳ መጠን ወለድን ሳይጨምር 2.1 ቢሊዮን ዶላር ነበር። 

በመሆኑም የ13 ስኳር ፋብሪካዎች አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ዕዳ ወለድን ሳይጨምር፣ በአሁኑ ወቅት ባለው የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥሌት 165.6 ቢሊዮን ብር ይሆናል። ይሁን እንጂ ይህ ግመታ ከተከናወነ በኋላ መንግሥት ተጨማሪ ወጪዎች በስኳር ፋብሪካዎች ላይ በማፍሰሱ የምርት ማሻሻያ ሥራዎችን፣ እንዲሁም የተመረጡ ፋብሪካዎችን የግንባታ ደረጃ የማሻሻል ጥረቶችን ያደረገ በመሆኑ፣ በቀደመው የሀብት መጠን ላይ ለውጥ እንደሚያመጣ መረዳት ይቻላል።

መንግሥት ከ13 ፋብሪካዎች ውስጥ አሥር ፋብሪካዎች እንዲሸጡና የሚገኘው ገቢም የዕዳ ክፍያን ለማስተዳደር ወደ የሚቋቋመው ኮርፖሬሽን ሙሉ በሙሉ ፈሰስ እንዲደረግ በመወሰኑ፣ አሥሩ ፋብሪካዎች በተገመቱበት የሀብት መጠን ብቻ ቢሸጡ፣ ኮርፖሬሽኑ ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ መቋቋሚያ ካፒታሉን ከስኳር ፋብሪካዎች ሽያጭ ሊያገኝ ይችላል። 

ከስኳር ፋብሪካዎቹ ሽያጭ በተጨማሪ ከቴሌኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ ገቢ ከፍተኛ ድርሻ ለኮርፖሬሽኑ ፈሰስ የሚደረግ ሲሆን፣ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ዘርፉን ለውጭ ገበያ ለመክፈት በተወሰነው መሠረት፣ ለሁለት የውጭ ኩባንያዎች የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ ለመሰጥት የተጀመረው የጨረታ ሒደት ተጠናቆ፣ በመጪዎች ጥቂት ሳምንታት አሸናፊዎቹ ኩባንያዎች ይፋ እንደሚደረጉ ይጠበቃል።

ጨረታውን የሚያሸንፉት ሁለት ኩባንያዎች እያንዳንዳቸው ለ15 ዓመታት የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ የሚያገኙ ሲሆን፣ ከሁለቱ ኩባንያዎች የፈቃድ ክፍያ በትንሹ በአማካይ መንግሥት ሁለት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ ሊያገኝ እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች ይገምታሉ። 

ለሁለት የውጭ ኩባንያዎች የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ ለመስጠት በመካሄድ ላይ ካለው የጨረታ ሒደት ጎን ለጎን፣ መንግሥት በኢትዮ ቴሌኮም ላይ ያለውን 45 በመቶ ድርሻ ለመሸጥ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ይታወቃል። 

የኢትዮ ቴሌኮም ከፊል ሽያጭን አስመልክቶ እስካሁን ከተደረጉት ዝግጅቶች መካከል የተቋሙ አጠቃላይ ሀብትና ንብረት ግመታ፣ በውጭ የኦዲት ኩባንያ ተሠልቶ መጠናቀቁና ለመንግሥት መቅረቡ ይገኝበታል። 

የኢትዮ ቴሌኮም ከፊል ሽያጭ እስኪጠናቀቅ ድረስ የተካሄደው የሀብትና ንብረት ግመታ ውጤት በሚስጥር መጠበቅ ያለበት በመሆኑ ይፋ አልተደረገም፡፡ ነገር ግን የኢትዮ ቴሌኮም ሀብት በመንግሥት ከተገመተው 42 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከጥቂት ወራት በፊት የኢትዮ ቴሌኮምን የተከፈለ ማቋቋሚያ ካፒታል ከ40 ቢሊዮን ብር ወደ 400 ቢሊዮን ብር ማሳደጉ ይታወሳል። (ሪፖርተር)

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: abay tsehaye, sugar factory, tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule