የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ “የመለስ ዜናዊ የአመራር አካዳሚ” “የአፍሪካ የአመራር ልህቀት ማዕከል” (‘African Leadership Excellence Academy’) በሚል መቀየሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስታውቀዋል።
አካዳሚው ከስም ለውጥ ጋር የ21 ኛው ክፍለዘመን የአመራር ጥያቄዎችን ለማሟላት የሚያስችል ዐቅም ያላቸውን ልሂቃን የሚያፈራ እና የዕድገት ተኮር አስተሳሰብን የሚያንፀባርቅ የትምህርት ተቋም እንዲሆን ያለመ ነው ብለዋል። ሌሎችም ከአሸባሪው ህወሃት ጋር የተቆራኙ ስሞችና መጠሪያዎች እንዲሁ እንዲቀየሩ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል።
ከዚህ በፊት አካዳሚውን እንዲመሩ የተሾሙት ዮሐንስ ቧያለው የአካዳሚው ስም በመጸየፍ አልመራም ማለታቸው ይታወሳል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Ereso Negi says
መልካም አድጋችኋል። ስሙ ግብሩን የሚያመለክት መሆኑ ጥሩ ነዉ ።
አለም says
እንኳንስ አፍሪካ ኢትዮጵያን አስተካክሎ አልመራ፤ ዘራፊ ሁላ። የባህር ዳር አውሮፕላን ማረፊያም ከግንቦት አህያነቱ ተገላግሏል። ጂጂጋ በጀሌ ያስተከለው ሃውልቱ ይነቀል። የፓትርያርክ ጳውሎስም ሃውልት ይነቀል።