ከአድዋ ወደ ራያ የዞረው የትግራይ አስተዳደር አዲስ መሪና ከመሪው ጀርባ የሚያጦዝ አዲስ ስብሃት ነጋን አግኝቷል። አዲሱ የስብሃት ነጋ ምትክ ንጉሥ ፈጣሪ (kingmaker) ጻድቃን ገብረ ትንሳኤ ሲሆን፣ የትግራይ ቲቪ ይፋ እንዳደረገው የትግራይ መሪ የሆነው ጌታቸው ረዳ ነው - ሁለቱም ከአማራ ከተወሰደው ራያ!! በይፋ በሚታዩ መረጃዎች ጌታቸው ረዳ በትግራይ ታጋይ ሳይሆን ትግራይን የመራ ብቸኛ ካድሬ ሆነው ይመዘገባል። ጌታቸው ረዳ ሌላ የሚያስመዘግበው ሪኮርድ ደግሞ በጥላቻና “እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” በሚል መርህ የተፈለፈሉ ሚዲያ፣ አክቲቪስቶች፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የብሔራቸው ተቆርቋሪ መስለው ሲንቀሳቀሱና ጥላቻን ሲያሰራጩ የነበሩ፣ በየክልሉ የክልልነት ጥያቄ በማስነሳት ግጭት እና አገር ብጥበጣ ውስጥ የገቡ፣ ሁሉ በጌታቸው አመራር ሥር ስለነበሩ ቆጣሪያቸው … [Read more...] about በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ
tplf
መፍትሔ የሚሹ የኢትዮጵያ የጎን ውጋቶች
ኢትዮጵያ ባለፉት አራት በላይ በሆኑ ዓመታት ከባድ ጫናዎችን ተሸክማ ቆይታለች። ይልቁንም የሰሜኑ ጦርነት በውስጥም በውጭም ገፊና ሳቢ ምክንያቶችን ፈጥሮ ሲያናውጣት ቆይቷል። ይኸው ጦርነት ኹለት ዓመት ሊደፍን የዋዜማው እለት የተደረሰው የሰላም ስምምነት በጉዳዩ ላይ የብዙዎች ተስፋ እንዲያንሰራራ አድርጓል። ኢትዮጵያን ችግሮቿ ሁሉ የተቀረፉ ያህል ብዙዎች ተሰምቷቸዋል። ሆኖም አሁንም ኢትዮጵያ የጎን ውጋት የሆኗት ችግሮች አሉ። የወሰንና አስተዳደር ጥያቄዎች፣ የታጣቂ ኃይሎች እንቅስቃሴ፣ የምጣኔ ሀብት መዳከም፣ ማንነትን መሠረት ያደረጉ የተለያዩ ጥቃቶች አሁንም ይስተዋላሉ። እናም ኢትዮጵያ ችግሮቿን ቁልቁል ደርድራ አንድ በአንድ በማስተካከል፣ እንደ ሰሜኑ ጦርነት ሁሉ በኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል እና ጋምቤላ እንዲሁም በሌሎች ክልሎችም ሌሎቹንም ችግሮች እንድትቀርፍ ይጠበቅባታል። በሰብአዊ … [Read more...] about መፍትሔ የሚሹ የኢትዮጵያ የጎን ውጋቶች
ትጥቅ ማስፈታቱ ተግባራዊ መሆን ጀመረ፣ ክልሉም ስምምነቱን በይፋ ተቀበለ
አሜሪካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን እደግፋለሁ አለች ረቡዕ ይፋ በሆነው የፕሪቶርያ ስምምነት መሰረት የትጥቅ ማስፈታቱ ሥራ መጀመሩ ታወቀ። በቅርቡ የሽግግር አስተዳደር የሚቋቋምለት የትግራይ ክልል ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤትም ስምምነቱን መቀበሉን በይፋ አረጋግጦ መግለጫ አሰራጨ። “… ይህ ስምምነት በተፈረመ በሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ የሁለቱ ወገኖች ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተገናኝተው ይነጋገራሉ” በሚለው ግልጽና በፊርማ የጸደቀ ውል መሰረት የኢፌድሪ ጠቅላይ ኢታማዦር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላና የትህነግ ማዕከላዊ ኮማንድ ፖስት አዛዥ የሚባሉት ታደሰ ወረደ በዛሬው ዕለት ተገናኝተው መናገራቸውን ኢ.ኤም.ኤስ. የተሰኘው የእነ ሲሳይ አጌና ሚዲያ ቀድሞ ቢገልጽም የኢትዮ 12 የአዲስ አበባ ዘጋቢ የዜናውን ትክክለኛነት ማረጋገጡን ገልጿል። የትህነግ ጦር ሌላ አዛዥ የሆኑት ባለሃብቱ ጻድቃንና … [Read more...] about ትጥቅ ማስፈታቱ ተግባራዊ መሆን ጀመረ፣ ክልሉም ስምምነቱን በይፋ ተቀበለ
ስምምነቱን በማይቀበሉ ወይም ዕንቅፋት በሚፈጥሩ ላይ አሜሪካ ዕርምጃ ትወስዳለች
በተጀመረ በአስረኛው ቀን ይፋ የሆነውን የሰላሙን ስምምነት ማክበር ለአሜሪካ ቀዳሚ አጀንዳ እንደሆነ በተለያዩ ኃላፊነት ላይ ያሉ ባለሥልጣኖች ቢናገሩም፣ ስምምነቱ ከመፈረሙ ከቀናት በፊት የስምምነቱን ውጤት በተመለከተ አሜሪካ አስቀድማ ውጤት አመላካች የሆነ ማስጠንቀቂያዋ ከወትሮው የከረረ ነበር። ይኸው ማስጠንቀቂያ ዛሬ የተገላቢጦሽ የሚሠራ መሆኑ ደግሞ ዜናውን ትኩስ አድርጎታል። ለትህነግ ያላትን ወገንተኝነት ያለ ኃፍረት በዓለምአቀፍ መድረኮች ስታስተጋባና አጀንዳ እየተከለች ኢትዮጵያ ላይ ጫናዋን ስታበረታ የነበረችው አሜሪካ፣ የሰላሙ ንግግር ከመጀመሩ ቀናት በፊት ውጤቱን አስመልክታ ያወጣቸውን መግለጫ ወይም አቋም ቁጣ ቀላቅለው ያስታወቁት በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ ነበሩ። ከትህነግ ጋር ቤተሰባዊ ግንኙነት እንዳላቸው በሥፋት በፎቶ … [Read more...] about ስምምነቱን በማይቀበሉ ወይም ዕንቅፋት በሚፈጥሩ ላይ አሜሪካ ዕርምጃ ትወስዳለች
ጥቅምት 24 “የክህደት ቀን” ተብሎ በግንቦት 20 መቃብር ላይ ይተከልልን!
በራሳቸው ሕዝብ ላይ ሲደርስ ሰማይ የሚደፋባቸውና ዓለም ሁሉ አብሯቸው እንዲያለቅስ የሚፈልጉት ምዕራባውያን በሌሎች ላይ ለሚደርሰው ሰቆቃ ቅንጣት ታህል ግድ አይላቸውም። አንድ ማሳያ እንጥቀስ፤ የዛሬ 80 ዓመት አካባቢ ጃፓን የአሜሪካንን ድንበር ጥሳ ከሐዋይ ደሴቶች አንደኛዋ ላይ የሚገኘውን ወታደራዊውን የፐርል ወደብ ገና በጠዋቱ በድንገት አጠቃች፤ በወደቡ ላይ የነበሩት 8 መርከቦች ጉዳት ደረሰባቸው፤ አራቱ ሰጠሙ፤ በአጠቃላይ ወደ 20 የሚደርሱ መርከቦችና ጀልባዎች ከጥቅም ውጪ ሆኑ፤ ከ300 በላይ የሚሆኑ አውሮፕላኖች፣ ጀቶችና ሔሊኮፕተሮች ከፍተኛ ጉዳት ደረሰባቸው፤ ከሁሉ በላይ ከ2,400 በላይ የሚሆኑ ባሕረኞች፣ ወታደሮችና ሰላማዊ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ፤ ከ1,000 በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆሰሉ። በቀጣዩ ቀን ዲሴምበር 8፣ 1941 የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ፍራንክሊን ሩዝቬልት … [Read more...] about ጥቅምት 24 “የክህደት ቀን” ተብሎ በግንቦት 20 መቃብር ላይ ይተከልልን!
ክብር ለጀግኖቻችን!
ትህነግ አሸንፎ ቢሆን ኖሮ … ድርድሩ የተደረገው ትህነግ ደብረብርሃንን፣ ባህርዳርን፣ ጎንደርን ይዞ ቢሆን ኖሮ ትጥቅ ይፍታ ይባል የነበረው ጥምር ጦሩ ነበር። ክብር ለጀግኖቻችን ይሁንና ድርድሩ የተደረገው ባለፈው አመት ምዕራባውያን ዲፕሎማቶቻቸውን ባስወጡበት ወቅት ቢሆን ኖሮ ጥምር ጦሩ ያለ እንቅፋት ወደ መቀሌ ይግባ ሳይሆን፣ ትህነግ ወደ አዲስ አበባ ይግባ ነበር የሚባለው። ክብር ለጀግኖቻችን ይሁንና፣ አምና ትህነግ እንደወረረን የባሰ ገፍቶ ቢሆን ኖሮ የጊዜያዊ አስተዳዳሪ መዳቢው ትህነግ ነበር። ያውም እንደህዝብ እንድንኖር ከፈቀደልን። ክብር ለጀግኖቻችን ይሁንና እንደ ጠላቶቻችን ቢሆን ኖሮ የትህነግ ጀኔራሎች ነበሩ ትጥቅ አስፈችዎች። ክብር ለጀግኖቻችንና ወልዲያና፣ ላሊበላን፣ ጋሸናና ደባርቅን ይዘው አልተደራደሩም። ክብር ለጀግኖቻችን ይሁንና አላማጣ … [Read more...] about ክብር ለጀግኖቻችን!
የትህነግ ታጣቂዎችና የጦር አመራሮች የጅምላ መቃብር ስፍራ የተገኘ
በመከላከያ ሰራዊት መስዋዕትነት ከህወሓት እየተላቀቁ በሚገኙት አካባቢዎች የአሸባሪው ህወሓት ድብቅ ገመና መጋለጡን ቀጥሏል። የሽብር ቡድኑ ቁንጮ አመራሮች አስገድደው በጦርነት ላሰለፏቸው ታጣቂዎች እንኳ ምንም አይነት ርህራሄ እንደሌላቸው በጨርጨር የተገኘው ጅምላ መቃብር ለዚህ ማሳያ ነው፡፡ ከጨርጨር ከተማ በስተምስራቅ በኩል በሺዎች የሚቆጠሩ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎችና የጦር አመራሮች የጅምላ መቃብር ስፍራ የተገኘ ሲሆን፥ ይህም የሽብር ቡድኑ ቁንጮ አመራሮች በትግራይ ህዝብ ደም በስልጣን ለመቆየት የማይፈነቅሉት ድንጋይ እንደሌለ ማሳያ ሆኗል፡፡ የጅምላ መቃብር ስፍራው መለያ ኮድ ያለውና በአንዳንዱ መቃብር ከ3 እስከ 5 አስከሬን በጋራ የተቀበረበት ሲሆን፥ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎቹን የቀበራቸው እንደ ኃላፊነታቸው እና ማዕረግ ደረጃቸው በመቃብራቸው ላይ ምልክቶችን በማድረግ … [Read more...] about የትህነግ ታጣቂዎችና የጦር አመራሮች የጅምላ መቃብር ስፍራ የተገኘ
ነገረ ወዲ ገብረ ትንሳኤ – ”አባዬ ምን በድለን ነው ህወሃት የምትቀጣን?”
ወደ ገደለው ስንሄድ፦ የራያው ልጅ ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ አራት ኪሎ የባዮሎጂ ተማሪ ነበረ። ከዛም ትግል ስታይሌ ነው አለና ደደቢት በረሃ ወረደ።[ውጊያ ተለማመደ]ወያኔ ከደርግ ጋራ ስትዋጋ ከጦር ፊታውራሪዎች አንዱ ሆነ፤ ፃድቃን ገብረትንሳኤ። ከገቡም በኋላ ለአስር አመታት ያህል፣ በሌተና ጀነራል ማዕረግ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የጦር ኤታማዦር ሹም (Chief of Staff) ነበረ።ፃድቃን ቀጥተኛ፣ ቅን እና ሆደ ቡቡ ነው ይሉታል የሚያውቁት።[አንዴ]የካህሳይ አብርሃን 'የአሲምባ ፍቅር' መፅሃፍን ካነበብክ፣ ያኔ ኢህአሠ አሲምባ እንደገባ በብሄር ፌድራሊዝም ጉዳይ ኢህአፓና ህወሃት ሲከራከሩ፣ ''የብሄር ፌዴራሊዝም የታክቲክ ጉዳይ ነው። ማታገያ ነው እንጂ End አይደለም'' ብሎ የሞገተ ነው። ''የትግራይ ገባር የመሬት ላራሹ ጥያቄው ስለተመለሰለት፣ አሁን መደብ ምናምን ከምንለው ጨቋኝ … [Read more...] about ነገረ ወዲ ገብረ ትንሳኤ – ”አባዬ ምን በድለን ነው ህወሃት የምትቀጣን?”
አንድ ጣሳ ማሽላ በ250 ብር በሚሸጥበት አላማጣ ተከማችቶ የነበረ ከ3 ሺሕ ኩንታል በላይ የእርዳታ እህል ተገኘ
በአላማጣ ከተማ አሸባሪው ህወሓት ለታጣቂዎቹ አከማችቶት የነበረው ከ3 ሺሕ ኩንታል በላይ የእርዳታ እህል ተገኝቷል። አሸባሪውና ወራሪው የወያኔ ቡድን ለራያ አላማጣ ህዝብ የሚመጣውን የእርዳታ እህል ለህዝቡ ሳያደርስ ለታጣቂዎቹ ቀለብ እንዲውል በየ መጋዝኖቹ እና ወፍጮ ቤቶች አከማችቶት መገኘቱን ነው መረጃው ያመለከተው። ተከማችቶ የተገኘው የእርዳታ እህልም ከ2 ሺሕ 500 ኩንታል በላይ የዩ ኤስ አይዲ የተፈጨ የስንዴ ዱቄት፣ ከ400 ኩንታል በላይ ከረጢት የታሸገ ስንዴ፣ ከ100 ኩንታል በላይ ብስኩቶች እና ኃይል ሰጪ ምግቦች መሆኑም ተገልጿል። የሽብር ቡድኑ ካለፈው 1 ዓመት ከ4 ወር በላይ በሆነ ጊዜ ውስጥ ለሰብዓዊ እርዳታ እንዲውል የሚገባ የትኛውንም አይነት ድጋፍ ከህዝቡ እየነጠቀ ለታጣቂዎቹ ሲያከማችና ሲቀልብ እንደነበር የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች ምስክርነታቸውን … [Read more...] about አንድ ጣሳ ማሽላ በ250 ብር በሚሸጥበት አላማጣ ተከማችቶ የነበረ ከ3 ሺሕ ኩንታል በላይ የእርዳታ እህል ተገኘ
በሕገ ወጥ የውጭ ሀገራት ገንዘብ ምንዛሪ በተሰማሩ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስና ከኦሮሚያ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በሕገ ወጥ የውጭ ሀገራት ገንዘብ ምንዛሪ በተሰማሩ ግለሰቦችና ድርጅቶቻቸው ላይ ጥናትን መሰረት ያደረገ እርምጃ መወሰዱን አስታውቋል፡፡ አገልግሎቱ ለሚዲያ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ባለፉት ሁለት ወራት በሕገ ወጥ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች ምንዛሪ ዙሪያ ሰፊና ጥልቀት ያለው ጥናት ሲካሄድ እንደነበር አመልክቷል፡፡ ችግሩ በጥናት ከተለየ በኋላም መረጃዎችንና ማስረጃዎችን መነሻ በማድረግ በተከናወነው ክትትል በሕገወጥ የውጭ ምንዛሪ ላይ ተሳታፊ የነበሩ 48 ግለሰቦችና ከፍተኛ መጠን ያላቸው የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች እንዲሁም ከድርጊቱ ጋር የተያያዙ የባንክ ደብተሮችና ልዩ ልዩ ሰነዶች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል ነው የተባለው፡፡ በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች … [Read more...] about በሕገ ወጥ የውጭ ሀገራት ገንዘብ ምንዛሪ በተሰማሩ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው