• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን

March 22, 2023 05:05 pm by Editor 1 Comment

የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በዛሬው የምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ወቅት ፤ “የሰላም ስምምነቱ ቀሪ ጉዳዮች ቢኖሩም ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” ሲሉ መናገራቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት በአብላጫ ድምፅ ተሰርዟል።

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ / ህወሓት / ከሽብርተኛ ድርጅትነት በተሰረዘበት የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ልዩ ስብሰባ ላይ 280 የፓርላማ አባላት ተገኝተው ነበር።

61 የፓርላማ አባላት ተቃውመው ድምፅ ሰጥተዋል

ከተገኙት የፓርላማ አባላት መካከል 61 የፓርላማ አባላት ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት መሰረዙን ተቃውመው ድምፅ ሰጥተዋል።

5 የፓርላማ አባላት ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል።

በዚህም በአብላጫ_ድምፅ ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት ይነሳ የሚለው የውሳኔ ሃሳብ ፀድቋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔውን ተከትሎ ባሰራጨው መረጃ ፤ “በህወሓትና በፌደራል መንግስት በኘሪቶሪያ የተደረገውን ሥምምነት ለማጽናት ህወሐትን ከሽብርተኝነት ስያሜ ማንሳት አማራጭ_የሌለው ጉዳይ መሆኑን የውሳኔ ሃሳቡ በቀረበበት ወቅት ተነስቷል” ብሏል።

ምክር ቤቱ ህወሓትን ከሽብርተኛ ድርጅት ዝርዝር ያነሳው የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተከትሎ ነው።

በስምምነቱ አንቀጽ 7/2 C መሰረት የፌዴራል መንግሥት በህወሓት ላይ የተጣለውን የሽብርተኝነት ስያሜ በምክር ቤቱ እንዲነሳ ሁኔታዎችን እንደሚያመቻች ይገልጻል። (tikvahethiopia)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, Politics Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    March 24, 2023 12:17 pm at 12:17 pm

    አይ የሃበሻ ፓለቲካ ያዘው ልቀቀው ነው፡፡ ለሞተ ይብላኝ፡፡ ችግሩ የወያኔ ከሽብርተኝነት መዝገብ ላይ መነሳቱ አይደለም፡፡ ወያኔ አሸባሪና ግፈኛ እንደሆነ የትግራይ ህዝብና የኢትዪጵያ ህዝብ ያውቃል፡፡ ግን ሽብርተኝነቱና የጌታቸው መሪ ሆኖ መሰለፍ የተከናወነው በአሜሪካ ግፊት መሆኑ ዛሬም ከሩቅና ከቅርብ የሚያዙን እንዳሉ ቁልጭ አርጎ ያሳያል፡፡ አቶ ሬዲዋን ሁሴን በፓርላማው ያሰሙት የጥንቆላ (ተንኳሽ) ንግግርም ከወያኔና ከአሜሪካ እንዲሁም ከጠ/ሚ አብይ የተኮረጀ ነው፡፡ ሲጀመር ለሰላም የቆመ ሰው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አንድን ቡድን ለይቶ አይዘልፍም፡፡ ይህ የሚያሳየው የቱን ያህል አማራን ወክያለሁ የሚለው ሃይል አሁንም ተለጣፊና ታዛዥ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ሶስት ጊዜ በወያኔ ዘረፋ፤ ግድያ የደረሰበት የአፋርና የአማራ ህዝብ ምን አይቶ ነው ትጥቅ ፍታ ገለ መሌ የሚባለው? ለኦሮሞ ብሄርተኞችና ጠባብ ቡድኖች ሰለባ እየሆነ ያለው ይህ ህዝብ ዛሬም ነገም የሚገፈተረው ለምን ይሆን? የእነ ማን ቤት ነው አዲስ አበባና ዙሪያዋ የፈረሰው? እነማን ናቸው በኦሮሞ አፋኝ ቡድኖች ተይዘው በስውር ስፍራ ተወስደው የሚቀጠቀጡት? ምን ስለተናገሩ ነው? ይህን ልብ የሚል አለ? እነማን ናቸው በወለጋ እየተለቀሙ የሚገደሉት? እንዴት ይህን ማየት የተሳነው የጊዜው ባለስልጣን አቶ ሬዲዋን በወደቀ ዛፍ ላይ ምሳር ያበዛል? ለገባው ይህ ሁሉ ጋጋታ ብዙሃንን ገፍትሮ ራስን ለማጎልበት የሚደረግ ሽቀባ እንደሆነ ልብ ሊባል ይገባል፡፡ እውነቱ ከቤተ መንግስት እስከ መቀሌ ተቀብሯል!
    አቶ ጌታቸው ረዳ በትግርኛ ቋንቋ ባስተላለፈው መግለጫ ዛሬም የኤርትራ ወታደሮች፤ የአማራ ተስፋፊዎች፤ በማለት ነገርን ማጠልሸቱ ለምን ይሆን? የኤርትራ ወታደር ትግራይ መሬት ካለ እንዲወጣ ማድረግ ያለበት ሃገር እመራለሁ የሚለው የጠ/ሚሩ መንግስት ነው፡፡ የአማራ ተስፋፊ መሬቶችን ይዞ እያለ የሚያላዝነው ወያኔ እነዚህ መሬቶች እሱ በራሱ በጉልበት ቆርሶ ከታላቋ ትግራይ ጋር የጨመራቸውን ከሆነ ጩኸቱ ከንቱና ሰላምን አደፍራሽ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የክልሉ ፓለቲካን አክ እንትፍ ላለ ኢትዮጵያዊ/ዊት የሃበሻ ምድር ሁሉ የሚኖርባት ናት፡፡ የሚያሳዝነው በዚህ የክልል ፓለቲካ አሁን ላይ ጢምቢራቸው የዞረው ኦሮሞዎቹ መሆናቸው ነው፡፡ የአፓርታይድ የመንደር ክልል ዛሬና ወደፊትም እሳት እየጫረና እያስጫረ የሚያጫርሰን እንጂ በአንዲት ሃገር ውስጥ ሰላምን የሚያመጣ የፓለቲካ ፓሊሲ አይደለም፡፡ በእኔ እምነት ወያኔን ከሽብርተኝነት መሰረዙ የሚያስገኘው በጎ ነገር እሳከለ ድረስ ችግር የለውም ባይ ነኝ፡፡ ግ ን በምላሹ መንግስት ያገኘው ምንድን ነው? በትግራይ የታሰሩ ወታደሮች፤ የሲቪል ሰራተኞች፤ ታፍነው የተወሰድ የአማራ ወጣቶችና የአፋር ተዋጊዎች፤ የተዘረፉ ሃብቶችና የቁም ከብቶች ወዘተ እንዴት ይረሳሉ? በአመዛኙ በስመ ትግሬ ተባባሪ ናቸው ተብለው በጠ/ሚሩ መንግስት በየስፍራው የተሰወሩትና የታሰሩት የትግራይ ልጆች እድል ፈንታስ ምንድን ነው? እኔ ከገጠመኝ አንድ ነገር ልናገር፡፡ ለሥራ ጉዳይ አዋሳ እሄድና እከሌ የታለ ብዬ እጠይቃለሁ? ውይ እሱ እኮ ከታሰረ ዘመን የለውም ትለኛለች ባለቤቱና የሁለት ልጆች እናት የሆነችው? ታዲያ እንዴት ትኖራላችሁ ስላት ልመና በለው በዚያ ነው በማለት ስትነግረኝ ይህ የትግራይ ተወላጅ የሆነውን ወታደራዊ መኮነን ሂጄ ለመጠየቅ እፈልጋለሁ ያለበት ቦታ ስላት እንኳን አንተን እኛን ድርሽ ሳያረጉን አሁን 3 ኣመት አለፈ በማለት እንባዋን ዘረገፈችው፡፡ ለቅሶዋን ተካፍዬ፤ ልጆችን ስሜ ያለኝ አካፍዬ ወደ መጣሁበት ተመለስኩ፡፡ ባጭሩ የሃበሻው ፓለቲካ ያኔም ዛሬም የእብደት ፓለቲካ ነው፡፡ ሰው ዘሩን መርጦ አይወለድም፡፡ አሁን የዛሬ 100 ኣመት አማራ ይህን ሰርቶ ያን አርጎ እያሉ የሚያስተራሩድንም የትርክት ፓለቲከኞች እንጂ እውነትን አያውቋትም፡፡ ባታውቀው ባይገባህ በተሳከረ የዘር ፓለቲካ ጨለማ ውስጥ ሆነህ እንጂ የምትገድለው የምታሰቃየው የራስህን ወንድምና እህት ነው፡፡ ቆሻሻ የዘር ፓለቲካን የሙጥኝ ብለው ህይወታቸው በዚሁ የጥላቻ ጥላሸት ተጋርዶ ፍጥረትና አለምን በውሉ ሳያውቋት ስንቶች አሸልበዋል፡፡ የትግራይ ሰላም መሆን የሁሉ ሰላም ነው፡፡ የአፋር አማራ እንዲሁም ኤርትራ ሰላም መሆን የጋራ ሰላማችን ነው ብሎ የማያስብ ጭንቅላት የአውሬ ጭንቅላት ያለው ብቻ ነው፡፡ ምድሪቱ የሁላችንም ናት፡፡ የክልል ፓለቲካውን አፍርሱት!
    ወያኔ 50 ኣመት ሙሉ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰውርና በይፋ እልፍ በደል ሰርቷል፡፡ በዚህ ራሱን ህዝባዊ እያለ በሚጠራው ድርጅት የላቀውን የመከራ ዶፍ የወረደበት ሰርቶ ለማደር በሚለፋው 99.9% የትግራይ ህዝብ ላይ ነው፡፡ ግፍ ማብቂያ አለው፡፡ የሃበሻውን የገመና ዘመን ምን እንደሚያጓትተው ሊገባኝ አይችልም፡፡ የማያባራ የመከራ ዶፍ! የዛሬ 50 ኣመት ያለቀሱ አይኖች ዛሬም ያነባሉ፡፡ ያኔ ከውጭ ስንዴና ሌላም ነገር ሲሰፈርለት የነበረው እስከ ልጅ ልጅ አሁንም ድርሻውን በቁና እየተቀበለ ነው፡፡ ለሃገር፤ ለወገን፤ ለጭቁኑ ህዝብ ቆመናል የሚሉ ሙታን ፓለቲከኞች እስከ መቼ ድረስ ነው በቋንቋና በክልል ፓለቲካቸው በህዝባችን ላይ የሚነግድበት? አይበቃም፡፡ አብሮ መኖር እንዴት የሰው ልጅ ተሳነው? የአማራ የትግሬ የኦሮሞ ገለ መሌ የሚለውን የመሬትና የክልል ንትርክ በመተው ሁሉም በፈለገው ሰርቶ የማደር መብቱ ለምን ይነፈጋል? ፓለቲከኞች የሚያቧቅሰንን አጀንዳ እየሰጡ እነርሱ በስልጣን ለመሰንበት በሚያድርጉት ሴራ አውቀንም ቢሆን ሳናውቅ ደጋፊ መሆናችን መቆም አለበት፡፡ መገዳደላችን ይብቃ!
    ባጭሩ ወያኔ ሶስት ጊዜ ጦርነት ከፍቶ እልፎችን ጨርሶና አስጨርሶ አሁን በአሜሪካ ግፊትና በጦር ሜዳ ላይ በደረሰበት ሽንፈት የተነሳ እጅ ወደ ላይ ማለቱ መልካም ነው፡፡ ግን ወያኔዎች እያሉ የትግራይ ህዝብም ሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም አያገኝም፡፡ ቃላቸው የማይታመን፤ አሰራራቸው የማፊያ፤ ዝርፊያቸው በቀንና ማታ የሆነ የጥቂት ሰዎች ስብስብ እንዴት የመላው ትግራይ ህዝብ አስለቃሽ እንደሆኑ ይቀጥላሉ? አታድርስ ነው፤ እግዚኦ መሃረነ ያሰኛል፡፡ የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ለአውሮፓ፤ ለአሜሪካ፤ ለአውስትራሊያ ጳጳሳት ሾማለች፡፡ ያልገባቸው ነገር ግን እነዚህ ቤ/ክ ተብየዎች የወያኔ ዋሻ የነበሩና ከፋፋይ ነገርን የሚያዛምቱ የምእመናኑ ቁጥር በአንዳንዶች ከአሥር የማይበልጡ መሆናቸውን ነው፡፡ በቅርቡ አንዲት እህቴ እንደነገረችኝ ልታመልክ ሂዳ ሰባኪው እዚያ ቤ/ክ እንዳትሄድ፤ ደግሞ እኛ ጋ አባል ሁናችሁ ተመዝገቡ ሲሉ እኔ ቤ/ክ ጥዬ ወጣሁ ብላኛለች፡፡ ግፋ ቢባል ለአንድ ትውልድ ሰዎች አማርኛም ትግርኛም፤ ግእዝም ተናጋሪ ሰዎች አምላኪ ሆነው ሊሰበሰቡ ይችላሉ፡፡ ከዚያ በህዋላ ግን ታሪክ ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ ጊዜ ሁሉንም ስፍራ ያስይዘዋል፡፡ ግን በአንድ በኩል ሰላም ሲባል በሌላ በኩል መስቀላቸውን ወደ ጠበንጃ ለውጠው ሃገር ከሚከፋፍሉ ስመ ጳጳሳትና ፓስተሮች ጉዳይ ሰው እንዲያውቅ በጥናት በተደገፈ መረጃ ከፋፋይና ወስላቶች መሆናቸውን ህዝባችን እንዲያውቅ ቢደረግ መልካም ነው፡፡ የተቦጫረቀው የሃበሻ ፓለቲካ እንኳን ሃይማኖት ገብቶበት አሁን ላይ ራሱ በቀንዳም ሰይጣኖች የሚመራ ነው፡፡ አይ ሃገር፡፡ እስቲ የወያኔን ከሽብርተኝነት መሰረዝና ትሩፋቱን ቆይተን እንይ! በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule