የቤተ-ክርስቲያን መስኮት ሰብረው ከሙዳየ ምፅዋት ገንዘብ ሰርቀው ሊሰወሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ። በጉራጌ ዞን በሶዶ ወረዳ ጊሚሴ ቀበሌ ቤተክርስቲያን ሰብረው ገንዘብ የዘረፉ ግለሰቦች በሁለት ወንድማማች እና በአከባቢው ህብረተሰብ ትብብር ለህግ አካል እንዲቀርቡ መደረጋቸውን ወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ። ትዛዙ ፍቅሬና አብርሀም ሞላ የተባሉት ተጠርጣሪዎቹ መድሀኒዓለም ቤተ-ክርስቲያን መስኮት ሰብረው ከሙዳየ ምፅዋት ውስጥ ገንዘብ ሰርቀው ሊሰወሩ ሲሉ በመቅቡል መሀመድ፣ በሀይሩ መሀመድ እና በአካባቢው ማህበረሰብ አማካኝነት እጅ ከፍንጅ ተይዘው ለህግ አካል እንዲቀርቡ መደረጉን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር አለማየሁ ደነቀ ተናግረዋል። ወንጀለኛ አብርሀም ሞላ ከዚህ በፊትም ነጌሳ ስላሴ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ የተቀመጠ ጤፍ በመዝረፍ ክስ ቢመሰረትበትም እድሜው አልደረሰም … [Read more...] about ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ
tplf terrorist
ከሽፏል!
የአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት HR6600/S3199 ሕግ ሆኖ እንዲፀድቅ የቀረበው የውሳኔ ኃሳብ እንዲቋረጥ ወሰነ። HR6600 እና S3199 ረቂቅ ሕጎች ሕግ ሆነው ከመውጣት እንዲዘገዩ የአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት ውሳኔ ላይ መደረሱን የኢትዮጵያ አሜሪካ ሲቪክ ካውንስል በትዊተር ገጹ አስታውቋል። ረቂቅ ህጉ እንዲቋረጥ ለጊዜው ከስምምነት የተደረሰበት ውሳኔ በቀጣይም ህግ ሆነው እንዳይፀድቁ ኢትዮጵያውያን እያደረጉት ያለው የዲፕሎማሲ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ካውንስሉ አሳስቧል። የኢትዮጵያ አሜሪካ ሲቪክ ካውንስል በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነትና ጫና በመቃወምና ዳያስፖራ ማህበረሰቡን ጭምር በማስተባበር ከፍተኛ የህዝብ ዲፕሎማሲ ስራ በመስራት ላይ ያለ መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገ ተቋም ነው። (AMN) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ከሽፏል!
ትህነግንና ሸኔን በአፍሪካ ደረጃ አሸባሪ አድርጎ ለማስፈረጅ እየተሠራ ነው
ድልድይ በማፍረስ፤ መሠረተ ልማቶችን በማውደም ከየቦታው በተለቃቀሙ ወንበዴዎች መሪነት ኢትዮጵያን በ“ነጻ አውጪ” ስም በግፍ ሲገዛ የነበረው ትህነግ በአፍሪካ በትክክለኛ መጠሪያ ስሙ ሊጠራ ዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰማ። ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። አባላቱና ደጋፊዎችም በዚሁ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው። ህወሓትና ተላላኪዎቹ በአሸባሪነት እንዲሰየሙ ተጠየቀ አሸባሪው ህወሓት በሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር በሕግ መታገድ፤ መሪዎቹም በኃላፊነት መጠየቅ አለባቸው አሸባሪው … [Read more...] about ትህነግንና ሸኔን በአፍሪካ ደረጃ አሸባሪ አድርጎ ለማስፈረጅ እየተሠራ ነው
ሸኔን ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እየተሰራ ነው
በፌደራል እና በክልል የፀጥታ ኃይሎች ጠንካራ እርምጃ ተወስዶበት ከተበታተነ በኋላ ንፁሃን ላይ ጥቃት እየፈፀመ ያለውን አሸባሪው ሸኔን ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እየተሰራ ነው ሲል የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። ጠንካራ የህዝብ አደረጃጀት በመፍጠር በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በተሰራው ኦፕሬሽን የሽብር ቡድኑ ከበፊት ቁመናው እና ይዞታው መዳከሙን የቢሮው ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ጠቅሰዋል። ጠንካራ እርምጃ ተወስዶበት የተበታተነው አሸባሪው ቡድን በተለያዩ ቦታዎች ንፁሃንን የማጥቃት የተለመደ የጥፋት ድርጊቱን እየፈፀመ ነው ብለዋል። ይህን የጥፋት ድርጊቱን ለማስቆም በፌደራል እና በክልል የፀጥታ ኃይሎች በተቀናጀ መልኩ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል ነው ያሉት። በመንግሥት መዋቅር ላይ ሆነው ከአሸባሪው ሸኔ ጋር በማበር በህዝብ እና … [Read more...] about ሸኔን ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እየተሰራ ነው
ውሃ ጥምን በኢትዮጵያዊ እስረኞች ስቃይ ‘የማርካት’ ፖለቲካዊ ቅዠት
ሪያድ ኢትዮጵያን በተለያዩ መስኮች በዘላቂነት እንደምትደግፍ የሳዑዲ ልማት ፈንድ መግለፁን ከወደ ሳዑዲ አረቢያ በዛሬው ዕለት ተሰምቷል። የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና የሳዑዲ ልማት ፈንድ ስራ አስፈፃሚ "ለሳዑዲ አረቢያና ኢትዮጵያ የጋራ ጥቅም የሚውሉ ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል። እንደ ዘገባዎቹ የሳውዲ የልማት ፈንድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሱልጣን ቢን አብዱራህማን አል-ሙርሺድ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴን ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን፤ ሳዑዲ አረቢያ በሳዑዲ ፈንድ በኩል በኢትዮጵያ ባከናወናቸው የልማት ተግባራትና እየተከናወኑ በሚገኙ ፕሮጀክቶች ላይ ከመወያየት ባለፈም ስለ ቀጣይ የትብብር ዘርፎች መክረዋል ነው የተባለው። የትብብር መስኮቹ በዝርዝር ያልተገለፁ ቢሆንም የትብብር መስኮቹ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የብልጽግና ዘርፎች ላይ … [Read more...] about ውሃ ጥምን በኢትዮጵያዊ እስረኞች ስቃይ ‘የማርካት’ ፖለቲካዊ ቅዠት
በሕዝብ ላይ የሚስማር ጥይት እስከማዝነብ የደረሰው የህወሓት የጭካኔ ጥግ!!
እብሪተኛው የህወሓት ኃይል የትኛውንም አማራጭ ተጠቅሞ ወደ ሥልጣን መመለስ ወይም ኢትዮጵያን መበታተን የሚል ቀቢፀ ተስፋ ይዞ ነበር ወደ ወረራ የገባው፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆነው በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከለከለውን በርካታ ሚስማር መሰል ፍንጣሪ (flechette) የተሰገሰገባቸውን በከባድ መሣሪያ ጭምር የሚተኮሱትን የሚስማር ጥይቶች በንፁሃን ላይ ማርከፍከፉ ነው፡፡ በምስሉ ላይ ወራሪው ኃይል በአፋር ጭፍራ ከተማ በንጹኃን ላይ የተጠቀማቸው የሚስማር ጥይቶች ይታያሉ፡፡ ወራሪው ኃይል ይህን መሣሪያ በአፋር እና በአማራ ክልሎች ተጠቅሟል፡፡ ነዋሪዎች እንደመሰከሩት ሚስማሮቹን ከበርካታ ጉዳት ከደረሰባቸው ንፁሃን ሰዎች ገላ ላይ ነቅለዋል፡፡ ሰቆቃውን ተመልክተዋል፡፡ ኢትዮጵያ እንደዚህ አይነት መሣሪያዎች ጥቅም ላይ ላለማዋል ዓለም አቀፍ ስምምነት ፈርማለች። (አዲስ … [Read more...] about በሕዝብ ላይ የሚስማር ጥይት እስከማዝነብ የደረሰው የህወሓት የጭካኔ ጥግ!!
ዘላቂ ወዳጅ የሌላት አሜሪካ ፊቷን በትህነግ ላይ እያዞረች ነው
ትህነግ ብዙ ወጪ ያደረገበት የሎቢ ሥራ ኪሣራ እየገጠመው ነው አሜሪካ ኢትዮጵያን ወደ አጎዋ ለመመለስ ፍንጭ አሳየች የኢትዮጵያ መንግሥት ከአሜሪካ የንግድ ልዑክ የተነሱበትን ቅሬታዎች በተመለከተ ተጨማሪ “አዎንታዊና ገንቢ” ዕርምጃዎችን የሚወስድ ከሆነ፣ ኢትዮጵያ ከተጠቃሚነት የተሰረዘችበትን የአሜሪካ መንግሥት ከቀረጥ ነፃ የንግድ ዕድል (አጎአ) በተመለከተ የንግግር ሒደት ውስጥ ለመግባት ፈቃደኛ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጋዜጠኞች ጋር በስልክ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣን፣ ኢትዮጵያ ከአውሮፓውያኑ ጥር ወር 2022 ጀምሮ ከአጎአ ተጠቃሚነት የታገደችው የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ከሰብዓዊ መብትና ሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የተቀመጡ መስፈርቶችን ባለማሟላቷ መሆኑን መናገራቸውን ኋይት ሀውስ … [Read more...] about ዘላቂ ወዳጅ የሌላት አሜሪካ ፊቷን በትህነግ ላይ እያዞረች ነው
የወንጀል ክስ ማንሳት እና ማስቀጠል የሚቻለዉ መቼ ነዉ?
የክስ ማንሳት የፍሬ ነገር ይዘትና ስነ ሥርዓት በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 122 ስር በአምስት ንዑስ አንቀጾች ተጠቃሎ ይገኛል፡፡ በይዘቱም፡- • ከከባድ የሰው ግድያ እና ከከባድ ውንብድና ወንጀሎች ውጭ ዐ/ሕግ ከፍርድ በፊት ክስ ማንሳት ይችላል፡፡ • ክስ የሚነሳው በዐ/ህጉ ጥያቄ ወይም በሌላ የመንግስት አካል ትዕዛዝ ሊሆን ይችላል፡፡ • ክሱ የሚነሳው በፍ/ቤት ፈቃድ ሲሆን ፍ/ቤቱ ለመከልከልም ሆነ በመፍቀድ ምክንያቱን ማስቀመጥ አለበት፡፡ • በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 113 መሰረት አዲስ ክስ ካልቀረበ ተከሳሹ ለግዜው ይለቀቃል፡፡ • የክሱ መነሳት ዐ/ሕግ ክስን ከማንቀሳቀስ አያግደውም፡፡ የሚል ሀሳብ ያለው ነው፡፡ የፍትሕና የሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲቲዩት ባዘጋጀው ረቂቅ የወንጀል ስነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 119 ስር ዐ/ሕግ ከፍርድ ቤት በማንኛውም ጊዜ ክስ … [Read more...] about የወንጀል ክስ ማንሳት እና ማስቀጠል የሚቻለዉ መቼ ነዉ?
አሸባሪው የትግሬ ቡድን ያደረሰው ውድመት በሳይንሳዊ መልኩ እየተጠና ነው
የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ እየተካሄደ የሚገኘውን ጥናት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ኀላፊ አንሙት በለጠ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ ክልል መጠነ ሠፊ የሰብዓዊ ጥሰት፣ የንብረት ዘረፋና ውድመት ፈጽሟል ብለዋል። በሽብር ቡድኑ ምክንያት የደረሰውን አጠቃላይ ውድመት ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ እየተጠና እንደሆነ አቶ አንሙት አስረድተዋል። በጥናቱ መሠረት ትክክለኛ ውድመቱ እንደሚገለጽ ነው የተናገሩት። ጥናቱ በጎደለው ልክ ለመሙላት አጋዥ እንደሚሆንም ጠቁመዋል። ከጥናቱ በኋላ የወደሙ መሰረተ ልማቶች ተመልሰው በሚገነቡበት ሁኔታ ላይም ስትራቴጂክ እቅድ እየተዘጋጀ እንደሆነ አመላክተዋል። አቶ አንሙት እንደተናገሩት የጥናቱ ዓላማ ቡድኑ ያደረሰውን ውድመት ትክክለኛ መረጃን መስጠትና በሰነድ ማስቀመጥ፣ የሽብር ቡድኑ ተጠያቂ … [Read more...] about አሸባሪው የትግሬ ቡድን ያደረሰው ውድመት በሳይንሳዊ መልኩ እየተጠና ነው
ሸዋሮቢት ከተማ በአሸባሪው ትህነግ ታጣቂዎች በቡድን የተደፈሩት እናት ራሳቸውን አጠፉ!
"መግደልም መድፈርም መብታችን ነው" – “ተገድደነው የዘመትነው” የሚሉት የትህነግ ታጣቂዎች ዕድሜያቸው 50ዎቹን ያለፈው የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዋ አዛውንት በአሸባሪው የህወሓት ታጣቂዎች በቡድን ከተደፈሩ በኋላ ራሳቸውን አጥፍተዋል። ፖሊስና የአካባቢው የዓይን እማኞች በሥፍራው ለሚገኙት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች እንደገለጹት፤ ዕድሜያቸው 50ዎቹን የተሻገረውና የሸዋሮቢት ከተማ ቀበሌ 02 ነዋሪ የነበሩት ወይዘሮ ሞሚና አህመድ (ስማቸው የተቀየረ) በአሸባሪው የህወሓት ታጣቂዎች በመደፈራቸው የልጄን ዓይን ከማይ ብለው ራሳቸውን አጥፍተዋል። ወ/ሮ ሞሚና የማገዶ እንጨት በመሸጥና እንጀራ በመጋገር የሚተዳደሩ ሲሆን፤ የ15 ዓመት ታዳጊ ልጅ እንዳላቸው የሸዋሮቢት ከተማ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ሀላፊ ኮማንደር አህመድ መሐመድ ለኢፕድ ገልጸዋል። ዛሬ ትህነግን … [Read more...] about ሸዋሮቢት ከተማ በአሸባሪው ትህነግ ታጣቂዎች በቡድን የተደፈሩት እናት ራሳቸውን አጠፉ!










