• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ወያኔ የመርገም ውጤት ነው” አቶ ሽመልስ

November 8, 2021 10:50 am by Editor 1 Comment

  • ይህ ኃይል አስተሳሰቡም ተግባሩም ሠይጣናዊ ነው፤ የሠይጣን ቁራጭ ነው
  • ወያኔ ይዋሻል፤ የውሸት አባት ደግሞ ሠይጣን ነው
  • የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ድጋሚ ወያኔን የበላይነት ቢቀበል እግዚአብሔር አይቀበለውም
  • ኢትዮጵያዊ ውስጥ ወያኔን የሚወጋው ሰው እንኳን ባይኖር ንፋስ ይጥለዋል
  • ወያኔ ውሸት ላይ ስለቆመ ከእንግዲህ ኃይል ሆኖ አይቆምም

ሕዝቡ በየአካባቢው በውስጡ ተሰግስገው ያሉት የአሸባሪው ሕወሓት ተላላኪዎችንና የሸኔ ጉዳይ አስፈፃሚዎችን መታገልና ከውስጡ መንጥሮ ማውጣት እንዳለበት የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አሳሰቡ።

አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (OBN) ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፤ አሸባሪው ትሕነግ ለኢትዮጵያ ጠላት ሆኖ የተፈጠረ ኃይል ነው። ይህ የአገር ጠላት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት በመዝመትና አካባቢውን በንቃት መጠበቅ ይኖርበታል። በተለይ የአሸባሪው የሕወሓት ተላላኪዎችንና የሸኔ ጉዳይ አስፈፃሚዎችን መታገልና ከውስጡ መንጥሮ ማውጣት አለበት ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለአሸባሪዎቹ ሕወሓትና ሸኔ ቡድኖች የእግር እሳት በመሆን መውጫና መግቢያ እስኪጠፋቸው ማሳደድ አለበት ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ እነዚህ ሁለቱ አሸባሪዎች ለግል ጥቅማቸው እንጂ ለህዝብ አንድነትና ፍላጎት ደንታ እንደሌላቸው ገልጸዋል።

በትዕቢት ኢትዮጵያን ለመውረር የመጣውን አሸባሪ ኃይል ኢትዮጵያውያን ልንቀብረው እንደሚገባ ያሳሰቡት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፤ በአሸባሪው የሕወሓት ቡድን ሚስቱንና ርስቱን እንዲቀማ የሚፈልግ ሰው ባለመኖሩ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በተባበረ ክንድ ይህን ወራሪ ኃይል ሊያስወግደው እንደሚገባ ገልፀዋል።

ከሁሉም አካባቢ የኢትዮጵያ ህዝብ ክተት ብሎ ወደ ግንባር እየተመመ ይገኛል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤የትግራይ ህዝብን አስገድዶና በተለያየ ፕሮፖጋንዳ አታሎት የፈፀመውን ወረራና ዘረፋ ታሪክ ይቅር የማይለው ነው ብለዋል።

አሸባሪው ሕወሓትና ተላላኪዎቹ ከኢትዮጵያ የተለዩ ‘ከዛፍ የተቆረጡ ቅርንጫፎች’ ናቸው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ እነዚህ ኃይሎች ከህዝብ የተለዩና ተቀባይነት ስለሌላቸው ከዛፍ ላይ የተቆረጠ ቅርንጫፍ ህይወት ሊኖረው አይችልም ብለዋል።

የአሸባሪው ሕወሓትን የሐሰት መረጃ በማጋለጥና ቁብ ባለመስጠት አገርን ከጠላት መታደግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

አሸባሪው ሕወሓት ዋና ዓላማ ኢትዮጵያውያንን በዘር፣በሃይማኖት በመጋጨት እሱ ያለተቀናቃኝ መግዛት የሚፈልግ መሆኑን አመልክተው፤ ኢትዮጵያ ይህን እኩይ ዓላማውን ተረድቶ አክሽፎበታል፤ አሁንም ይህን ቡድን በማስወገድ ረገድ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንደሚኖርበት አስታውቀዋል።

የመከላከያ ሠራዊቱ ለሀገሩ፣ ለህዝቡ ደህንነት፣ ለባንዲራውና ለህገ መንግሥቱ መከበር ቀን ከሌት ህይወቱን እየሰዋና እየተዋደቀ እንደሚገኝ ጠቁመው፤መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሰራዊቱን በመቀላቀልና አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ በማድረግ በአጭር ጊዜ የሽብር ቡድኖችን ማስወገድ ይገባል ብለዋል።

አሸባሪው ሕወሓትና ተላላኪዎቹ ከተወገዱ በኋላም በኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖትና የባህል ነፃነት የሚደፍንት፣ እውነተኛ ወንድማማችነት የሚጎለብትበት፣ ኢትዮጵያዊ ማንነት ከፍ የሚልባት አገር እንደምትሆንም አረጋግጠዋል።

ሊነጋጋ ሲል ይጨልማል እንዲሉ አሁን በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ የጨለመ ቢመስለንም መንጋቱ አይቀርም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ነገር ግን ጨለማ ብርሃንን ሊቋቋም ስለማይችል በኢትዮጵያ የብርሃን ዘመን ተመልሶ የሚመጣበት ቀን ቅርብ ነው ብለዋል። (አዲስ ዘመን)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Interviews, Left Column, News Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    November 12, 2021 05:37 pm at 5:37 pm

    ወንድሜ ሽመልስ ልክ ብለሃል። ወያኔ ጭራቅ ነው። ሰው በላ። ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦል ድረስ የሚወርድ የእብድ ጥርቅም። ለዚህ ሃይል ዋናው ማርከሻው እንደ አንድ ህዝብ በየአቅጣጫው የወያኔን ወራሪ ሃይል መታት ሲቻል ነው። በሌላ አባባል ወያኔ ጉልበቱን ተማምኖ ሰራዊቱን እንዳረደው፤ አልፎ ተርፎም አማራንና አፋርን መጨፍጨፉ ምን ያህል የክፋት ቋት እንደሆነ ያሳያል። ስለሆነም ወያኔን በወታደራዊ ሃይል በመምታት ዳግም እንዳያንሰራራ ልነሳም ካለ ረጅም ጊዜ እንዲፈጅበት አድርጎ ካለበት ደረጃ ዝቅ ማድረግ ያስፈልጋል። ያ ካልሆነ እያስገደድም ሆነ በውሸት ፕሮፓጋንዳ የትግራይን ህዝብ እያሰለፉ ውጊያውን ሊያራዝመውና የሃገራችን መከራ ሊያብሰው ይችላል። ለዚህም የሃገሪቱ መከላከያ ሰራዊት፤ የክልል ሃሎች፤ ሚሊሻው፤ ፋኖውና ቄሮው ወያኔን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ከትግራይ መሬት ጭምር ወያኔን ማጥፋት ያስፈልጋል። ያኔ የትግራይ ህዝብ ራሱ በመረጠው መንገድ፤ መገንጠልም ሆነ አብሮ መኖርን መወሰን ይችላል። ወያኔ እያለ በምድራችን ሰላም አይኖርም። በተለያዬ ክልሎች የሚለኮሱት እሳቶች ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የወያኔ እጅ እንዳለበት ከእኛ በበለጠ አንተ ታውቃለህ። የዘንዶው (ወያኔ) ራስ ከተመታ ሌላው ሁሉ ተፍረክራኪ ነው። ከዚህ ላይ ነጮች ምክር ብለው በቀጥታም ሆነ በእጅ አዙሪ የሚልኳቸውን ነገሮች አትቀበሉ። እሺ ብሎ ማለፍና ሙያን በልብ መፈጸም ነው። ወያኔ በጀርመን ናዚ ከተፈጸመው በደል በላይ በሃገራችን ህዝብ ላይ ግፍ የሰራ ድርጅት ነው። የሚገርመኝ የተማረኩት ራሳቸው ያላቸው ኩራትና መኮፈስ የትዕቢታቸውን ልክ ያሳያል። በዘር ፓለቲካ የሰከሩ ክፉዎች ናቸው። ለዘመናት ጠላትህ አማራ ነው እየተባሉ የተጋቱት ያ የፈጠራ ትርክት ዛሬም አለቀቃቸውም። አማራና ኦሮሞን ለማጫረስ የአኖሌን ሃውልት ያቆመው ወያኔ የሰራዊቱን ሚስቶችና አባላትን ጡት ነው በሳንጃ የቆረጠው። ሲኖ ትራክ ነው በወታድሮች ላይ የነዳው? ይህ እንዴት ለሃገራችን ህዝብ ይዋጥለታል? አንድ ገጣሚ እንዳለው፡
    ብቻቸውን በልተው ሃገሬን በቁሟ
    27 ዓመት መልሰው መላልሰው
    ሂሳብ አለን አሁል ዛሬም ተመልሰው
    ይህ ነው የወያኔ ብልሃት። ለመኖር፤ ለመክበር እልፎችን ማስለቀስ፡ መግደልና መዝረፍ። ሌላው የመረረው ደግሞ እንዲህ አለ። በእርግጥም ስንኙ ወያኔን ይገልጠዋል።
    ድንበር ጠባቂ ሃይል አርዶ የሚበላ
    ሌላ ምን ጅብ አለ ከወያኔ ሌላ።
    ወያኔ ያለምንም ርህራሄ እንዳይነሳ ተደርጎ መደቆስ አለበት። በጎንደር፤ በአፋር፤ በወሎ የተፈጸመው ግፍ ይጮሃል። ምላሽ ይሻል። ከሰራዊቱ ጎን ተሰልፈው ለሃገር አንድነትና ለህዝቦች ነጻነት የሚፋለሙ ሃይሎችን ሁሉ መንግስት ሊጠቀምባቸው፤ ሊደግፋቸው፤ ሊያስታጥቃቸው ይገባል። ዝም ብሎ ሆ ሆ ማለቱ መልካም አይሆንም። ወያኔ እንዲጠፋ ሁሉም የየበኩልን ማድረግ እንዲችል መንግስት በተጠንቀቅ በመቆም ወያኔን ተፋላሚ ሃይሎችን ሁሉ አይዞአቹ በማለት የውጊያ መሳሪያና ጥይት ከተቻለም ራሽን ሊያቀርብላቸው ይገባል። የወያኔ ግባተ መሬት ቀርቧል። ዋ የትግራይ ህዝብ ልጆቻችን ሲሉት ምን ሊመልስ ይሆን? የጌታቸው ሬሳ በመቀሌ ሲጎተት ይታየኛል። ጠብቀን እንይ! በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule