አሸባሪው የትህነግ ቡድን አገር የማፍረስ እቅዱን ለማሳካት በርካታ እኩይ ተግባራትን እየፈፀመ እንደሚገኝ በደሴ ግንባር የተማረከው የሽብር ቡድኑ ሜይዴይ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ጉዕሽ ገብረ ተናገረ። የሽብር ቡድኑ በርካታ ህፃናትና ሽማግሌዎችን ያለ ትጥቅ በማሰለፍም ለአላስፈላጊ መስዋዕትነት እየዳረጋቸው እንደሚገኝም ምርኮኛው ተናግሯል። አሸባሪው ትህነግ አገር የማፍረስ እቅድ ነድፎ መንቀሳቀስ ከጀመረ ድፍን አንድ አመት ተቆጥሯል። ቡድኑ በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም በሰሜን እዝ ላይ ያሰበው እቅድ እንዳሰበው አልሆን ሲለው የትግራይን ህዝብ በሀሰት ፕሮፓጋንዳ በማሰባሰብ ለዳግም የክህደት ተግባር በተለያዩ ግንባሮች ጦርነት ከፍቶ ይገኛል። የሽብር ቡድኑ ሰሞኑን እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው የሰው ሃይል በማሰለፍ በደሴ ግንባር ውግያ ቢከፍትም በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ … [Read more...] about በደሴ የወንበዴው ክፍለ ጦር አዛዥ ጉዕሽ ገብሩ በቁጥጥር ሥር ውሏል