አሸባሪው የትህነግ ቡድን አገር የማፍረስ እቅዱን ለማሳካት በርካታ እኩይ ተግባራትን እየፈፀመ እንደሚገኝ በደሴ ግንባር የተማረከው የሽብር ቡድኑ ሜይዴይ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ጉዕሽ ገብረ ተናገረ።
የሽብር ቡድኑ በርካታ ህፃናትና ሽማግሌዎችን ያለ ትጥቅ በማሰለፍም ለአላስፈላጊ መስዋዕትነት እየዳረጋቸው እንደሚገኝም ምርኮኛው ተናግሯል።
አሸባሪው ትህነግ አገር የማፍረስ እቅድ ነድፎ መንቀሳቀስ ከጀመረ ድፍን አንድ አመት ተቆጥሯል።
ቡድኑ በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም በሰሜን እዝ ላይ ያሰበው እቅድ እንዳሰበው አልሆን ሲለው የትግራይን ህዝብ በሀሰት ፕሮፓጋንዳ በማሰባሰብ ለዳግም የክህደት ተግባር በተለያዩ ግንባሮች ጦርነት ከፍቶ ይገኛል።
የሽብር ቡድኑ ሰሞኑን እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው የሰው ሃይል በማሰለፍ በደሴ ግንባር ውግያ ቢከፍትም በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ሊደርስበት ችሏል።
በዚህ ግንባር የመከላከያ ሰራዊት ባደረገው ዘመቻም በርካታ የጠላት ሃይልን የደመሰሰ ሲሆን በርካቶችንም ማርኳል።
ከተማረኩት ውስጥም የሜይዴይ ክፍለ ጦር አዛዥ የሆነው የ64 አመቱ ኮሎኔል ጉዕሽ ገብሩ ይገኝበታል።
ጀግኖች፥ የጀግኖች ልጅ ልጆች፥ ልባሞች፣ የቁርጥ ቀን ልጆች፣ ፋኖዎች የአሸባሪው ጁንታ ኮለኔል ጉዕሽ ገብሩ ማርከው በጨዋ ደንብ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አስረክበዋል።
እንደ ምርኮኛው ገለፃ የሽብር ቡድኑ ያሰማራው ሃይል ዲሲፕሊን የሌለው በመሆኑ በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች በርካታ የግድያና ዘረፋ ተግባራትን አከናውኗል። (EBC)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply