በነጭ ፕሮፖጋንዳ ሀገርን በማፍረስ ተግባር የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግስት አሳሰበ፡፡
በነጭ ፕሮፖጋንዳ ሀገርን በማፍረስ ተግባር የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አሳሰበ፡፡
በሀገር ጉዳይ ቀልድ የለም ያለው አገልግሎቱ ከዚህ ድርጊታቸው በማይቆጠቡት ላይ መንግስት የማያዳግም ርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል፡፡
መላው ህዝብ ኢትዮጵያን የማዳን የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የሚገኝ መሆኑን ተገንዝቦ የጀመረውን ሀገር የማዳን ንቅናቄ አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስቧል፡፡
“ዋስትናችን ህልውናችንን በአንድነት ማረጋገጥ መሆኑን በመረዳት” በአፍራሽ ኃይሎችና ግብረ አበሮቻቸው በኩል የሚነዙ መርዛማ ወሬዎች የሚመጡበትን መንገድ መዝጋት እንደሚገባም ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያውያንና የወዳጅ ሀገራት ሚዲያዎች ለህብረተሰቡ ትክክለኛውን መረጃ በተገቢው ጊዜ እንዲያቀርቡ ጠይቋል፡፡
“በጊዜያዊ ድሎች መወራጨት የጀመሩትን የጥፋት ኃይሎች የማይናወጡ ዘላለማዊ ድሎችን በማስመዝገብ መክተን ወርቃማ ታሪክ መፃፍ ያለብን አሁን ነውና ሁላችንም በአንድነት እንቁም” ብሏል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባወጣው መግለጫው፡፡
የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፡፡
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply