• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ትህነግ ኤርትራውያንን ለመጨፍጨፍ ማቀዱን ትሮንቮል አረጋገጠ

November 12, 2021 01:01 pm by Editor 1 Comment

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር – ትህነግ ስም ሳይጠራ “ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ትሠራላችሁ” በሚል የጠቀሳቸው ክፍሎች ኤርትራዊያንን እንደሆነ ጥርጥር እንደሌለው ተመለከተ። ዛቻው በኢትዮጵያ ያሉ የኤርትራ ተወላጆች ላይ እንደሆነም ተጠቁሟል።

ትህነግ በመግለጫው በመከላከያ፣ በደኅንነትና ጸጥታ ተቋማት “ተሰግስጋችሁ” ሲል የፈረጃቸው ማስጠንቀቂያው እንዲደርሳቸው ደጋግሞ አመልክቷል። በዚሁ ስምና አገር ይፋ ባልተደረገበት የማስጠንቀቂያ መግለጫ የተጠቀሱት ተቋማት ውስጥ አሉ ያላቸው የውጭ ዜጎች “የአስካሁኑ በቃን” ብለው አገር ለቀው እንዲወጡ፣ አገራቸውም የተጠቀሱትን ወገኖች ከኢትዮጵያ እንዲያስወጡ ያሳሰባል።

ይህ ካልሆነ “የትግራይ መንግሥትና ሰራዊት በትግራይ ህዝብ ጆኖሳይድ በፈፀሙ ወንጅሎኞች ላይ በሚወሰደዉ ማንኛዉም አፀፋዊ እርምጃ ተጠያቂ እንደማይሆን የዓለም አቀፍ ማህበረሰብና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከወዲሁ እንድትገነዘቡት የትግራይ መንግስት ያሳዉቃል” ሲል መግለጫው አሳስቧል። እርምጃው ምን እንደሆነ፣ እንዴት እንደሚከናወን፣ በተናጠል የሚወሰድ ይሁን አይሁን የተባለ ነገር የለም።

መግለጫው በግልጽ ኤርትራን እንደ አገር፣ ዜጓቿን እንደ “ተባባሪ ወንጀለኛ” ባያነሳም ሼትል ትሮንቮል የሚባለው የኖርዌይ ተወላጅ መግለጫውን ተከትሎ ኤርትራውያን ኤጀንቶች የትግራይ ተወላጆችን በመለየት፣ በቦሌ ኢሚግሬሽን በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን አመልክቷል። ትህነግም በመግለጫው በመከላከያ፣ በደህንነትና በጸጥታ ተቋማት ሲል ከገለጸው ጋር ተመሳሳይ ሆኗል።

ለትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር የስም ለውጥ ሲያደርግ በማማከርና “የትግራይ መከላከያ ሃይል /TDF/ እንዲባል ስም ያወጣላቸው ሼትል፣ በምርጫ ቦርድ ህጋዊ አይደለም የተባለውን ምርጫ በፕሮፌሰርነት ስም ገብቶ በብቸኛነት የታዘበ መሆኑ አይዘነጋም። ድርጊቱ ሲጋለጥ የኢትዮጵያ መንግሥት ካገር እንዳባረረው ይታወቃል። ከዚህ ሌላ ግለሰቡ በጾታዊ ጥቃት የቀረበበት ውንጀላ እንደነበር ይታወሳል።

ይህንኑ ትሮንቮል ያወጣውን መረጃ ተከትሎ የአትላንቲክ ካውንስል ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ብሮንዊን ብሩቶን የአጸፋ ምላሽ ሰጥተዋል። በመልዕክታቸውም ትኖንቮል ከሌሎች የሚጠይቀውን አካዳሚያዊ ገለልተኝነት ራሱ የማይተገብረው ነው በማለት “ፕሮፌሰር”ነቱን ጥያቄ ውስጥ አስቀምጠውታል።

የዛሬ ሦስት ዓመት አካባቢ በአትላንቲክ ካውንስል የአፍሪካ ማዕከል ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ብሮንዊን ብሩቶን“ህወሓት፤ የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ጠላት!” (Ethiopia and Eritrea Have a Common Enemy) በሚል ርዕስ ግሩም ትንታኔ በመስጠት ተሟጋች መጣጥፍ አቅርበዋል።

በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የትህነግን ፕሮፓጋንዳ በተደራጀ መልኩ ከሚንቀሳቅሱት የተገዙ ሰዎች መካከል ግንባር ቀደም የሆነው ሼትል ትሮንቮል፣ ራሱን “የትግራይ መንግስት” እያለ የሚጠራው ግን በትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር/ትህነግ ስም የተመዘገበው ወራሪ ኃይል ስም ሳይጠቅስ ያወጣውን መግለጫ ይፋ በማድረጉ በርካቶች “እናመሰግናለን” ብለውታል።

በብዛት በኤርትራ ስደተኞች ስም ወደ ውጭ አገር የተጋዙት ለትህነግ አመራሮችና መዋቀር ቅርብ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች “ኤርትራዊያንና ተጋሩ ናቸው አንድ ነን” የሚል አዲስ ስልት እንዲያራምዱ በውስጥ መመሪያ እንደተሰጣቸው ይታወሳል። “የኤርትራ ሙስሊሞች እንጂ ክርስቲያኖች በትግራይ ወንጀል አልፈጸሙም። ክርስቲያኖች ወዳጆቻችን ናቸው። የሚፈለገው ዋጋ ተከፍሎም ቢሆን እነሱን ማቅረብ አለበን” በሚል አዲስ ስልት በመነደፉ ኤርትራዊያን ላይ ተቃውሞ ማሰራጨት እንደቆመ አይዘነጋም። ይህን ያስታወሱ ኤርትራዊያን እንዳሉት “የትህነግ አካሄድ ግልጽ ነው” ሲሉ ዛቻውን በዝምታ እንደማያዩት ለጎልጉል አስታውቀዋል።

ቁጣ ያስነሳውና ሰፊ መነጋገሪያ የሆነው “የእንጨፈጭፋችኋለን” የትህነግ ማስፈራሪያ ከተለያዩ ሚዲያ ዘገባዎች ላይ እንዲነሳ ቢደረግም “ጉዳዩ ለኤርትራ ተወላጆች የማንቂያ ደወል ነው። እንደ ቀድሞው ዛሬ የሚዘረፍና የሚጠቃ አካል የለም” ብለዋል። ለኤርትራ መንግስት ቅርብ የሆኑ እንዳሉት “እንቅልፍ የለም” ሲሉ መንግሥታቸው ትህነግ ለሚፈጽመው ማናቸውም ጥቃት እጥፍ ምላሽ የሚሰጥ ዝግጅት አጠናቋል። በስደት ካምፕ በርካታ የኤርትራ ልጆችን እንደገደለና እንዳጠቃቸው ሙሉ መረጃ እንዳለ አመልክተው እርምጃው የሁሉም ግፍ ድምር ሊሆን እንደሚችል አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያና ኤርትራ በጸጥታና በመከላከያ አብረው ለመስራት ስምምነት እንዳላቸው የሚጠቁሙ “ኤርትራና ኢትዮጵያ መካከል ስላለው ግንኙነት የትግራይ ተገንጣይ ቡድን ጣልቃ የመግባት ህጋዊ መሰረት የለውም። ጉዳዩን አስመልክቶ እንደ አንድ ክልል ባለው ውክልና በድምጽ ከመቃወም ውጪ ሌላ ጉዳይ ውስጥ መግባት የግንባር የጦርነቱ ዜና የተለወጠ ለመሆኑ ማሳያ ከመሆን አያልፍም” ብለዋል።

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ – ራሱን “መንግስት” በማለት በርካታ የአማርኛ ቃላት ግድፈት ያለበት መግለጫ ከዚህ በታች ያለው ነው። የስነልቦና ምሁራን ይህንን ዓይነቱን አጻጻፍ ብዙ ነገር አመላካች መሆኑን ሲጠቅሱ በተለይ ግን አንድን ነገር ጠበቆ ተቃራኒው በመሆኑ የፈጠረው ራስን የሚያስት ንዴት፣ ሽንፈት የተቀላቀለበት ዕልህን የሚያሳይ በደመነፍስ የተጻፈ፣ የውስጥን ድብቅ ማንነት በድንገትና ባልተጠበቀ ክስረት ምክንያት ሳይታሰብ እንዲወጣ ያደረገ ተፅዕኖ ያስከተለው የፅሁፍ ውጤት ነው በማለት ይናገራሉ።   


በትግራይ ህዝብ ጆኖሳይድ በፈፀሙ ወንጅሎኞች በሚወሰደዉ ማንኛዉም አፀፋዊ እርምጃ ተጠያቂ እንደማይሆን የትግራይ መንግስት አስታወቀ

ከትግራይ መንግስት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ባለዉ ጆኖሳይድ እየተሳተፋችሁ ያላችሁ የዉጭ ሃገር ዜጎች እጃችሁን እንድታነሱ የትግራይ መንግስት ያስጠነቅቃል!!

በተስፋፊዉ ሓይሎች ሳንባ የሚተነፍሰው አረመኒያዊ እኩይ ተግባራት የፈፀመዉና እየፈፀመ የሚገኘዉ የፋሽስት አብይ አሕመድ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ በይፋ አዋጅ ተግባራዊ እያደረገዉ ያለዉ ጭካኔ የተሞላበት የጆኖሳይድ የጅምላ ጭፍጨፋ ሶስት ዓመት ተኩል አስቆጥሯል። የፋሽስት አብይ አሕመድ ቡድን ባለፉት ሶስት ዓመት ተኩል የኢትዮጵያን ሁሉም መውጪያና መግብያ በሮች በርግዶ በርካታ የሃገሪቱን ተቋማት በማንአለበኝነት ለባዕድ ሓይሎች አሳልፎ ሰጥቷዋል።

የባዕድ ሓይሎች እንዳሻቸዉ ከሚያሽከረክራቸዉና በዘረፋ ራቁታቸዉ ካስቀራቸዉ ተቋማት መካከል በዋነኛነት የመከላከያ፣ የድህንነትና የፀጥታ ተቋማት ወዘተ— ተጠቃሾች ናቸዉ። በመሆኑ በፋሽስት አብይ አሕመድ ቡድን የጥፋት ጥሪ ተደርጎላቸዉ በመከላከያ፣ ደህንነትና ፀጥታ ተቋማት ተሰግስገዉ ተቋማቱን እንዳሻቸዉ በመዘወር ላይ የሚገኙ ቅጥረኛ አመራሮች፣ አማካሪዎች፣ ፈፃሚ የዉጭ ዜጎችና ሓይሎች በትግራይ ህዝብ የተፈፀመዉና እየተፈፀመ ባለዉ ጆኖሳይድ በቀጥታ የተሳተፈ፣ ተባባሪና ተዋናዮች በመሆናቸዉ በዓለም አቀፍ ፍርድቤት በወንጅል ሊጠየቁ ይገባል።

ስለሆነም በመከላከያ፣ ደህንነትና ፀጥታ ተቋማት እንዲሁም ሌሎች በአመራር፣ አማካሪነትና በፈፃሚነት በቀጥታ በአገር ለአላዊነት ጠልቃ የገባችሁ የዉጭ ዜጎችና ሓይሎች በዚህ ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረዉ በትግራይ ህዝብ ላይ የታወጀዉ ወታደራዊ ወረራና የተፈፀመዉ ጆኖሳይድ በወንጅል ላይ ወንጀል እየፈፀማችሁ የሚጠብቃችሁ ፍርድ የከፋ ከምታደርጉ እስከአሁን የፈፀማችሁት “ይብቃን” ብላችሁ ከዛሬ ጀምሮ እጃችሁ በመሰብሰብ ከእኩይ ተግባራቹ እንድትቆጠቡና አገር ለቃቹህ እንድትወጡ የትግራይ መንግስት በጥብቅ ያሳስባል።

በመጨረሻ ፋሽስት ቡዱን የትግራይ ህዝብ ለማጥፋት በፈፀመዉ ጆኖሳይድ ዜጎቻችሁ ያሰማራችሁ አገራት ከድርጊታቸዉ እንዲታቀቡና ዜጎቻችሁን ወደ አገራቸዉ እንዲመለሱ ጥሪ እንድታስተላልፉ የትግራይ መንግስት በጥብቅ ያስታውቃል። ይህን ሳይሆን ሲቀር ግን የትግራይ መንግስትና ሰራዊት በትግራይ ህዝብ ጆኖሳይድ በፈፀሙ ወንጅሎኞች ላይ በሚወሰደዉ ማንኛዉም አፀፋዊ እርምጃ ተጠያቂ እንደማይሆን የዓለም አቀፍ ማህበረሰብና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከወዲሁ እንድትገነዘቡት የትግራይ መንግስት ያሳዉቃል።

የትግራይ መንግስት ህዳር 1/2014 ዓ/ም


ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Left Column, News, Politics Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    November 14, 2021 11:07 am at 11:07 am

    አታድርስ ነው። ነጩ ለራሱ ሲቆርስ አያሳንስም። Kjetil Tronvoll ሙያው “A professor of Peace and Conflict Studies” ነው ተብለናል። በዚህ ዙሪያ ላይ ብልሃተኝነቱም ኢትዮጵያን፤ ኤርትራንና ዛንዚባርን ያካልላል። እኮ በለ እንዴት ነው የነጭ ሰው ስለ አፍሪቃ ሰላም የሚገባው? እሳት እየለኮሱና እያስለኮሱ የሰላም ምሁር መባሉ ለሚቀመጡበት ወንበር ሙቀት ካልሆነ ከዚህ ግባ የሚባል አንድም ነገር አይፈርጅም። እነዚህ ልክ እንደ Paul B. Henze ራሳቸውን በተለያየ የትምህርት ተቋማትና የእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ስር አስጠልለው የሚሰልሉት ለቀጠራቸው ነው። ይህ ወስላታ ምሁር ነኝ ባይ የለጠፈውን ቲውት ላነበበና ወያኔ በየጊዜው የሚወሸክተውን ቱልቱላ ላነበበ ሃሳባቸው ከአንድ ወንዝ መቀዳቱን ያሳያል። ድንቄም የሰላም ፕሮፌሰር። ያ ቀርቶ ሌላ ዘፈን መቶ። ማን ሊያምናችሁ። በአንድ እጅ ዳቦ በሌላ እጅ ክብሬት እየሰጣችሁ ነው ዓለምን ድሃና የመከራ ቋት ያረጋችሁት።
    አሁን እንሆ የኤርትራ የስለላ መረብ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ እየሰራ ነው ይለናል። ይሁና። ምን ችግር አለው? እንደ ወያኔ በወረራ አልመጡ። ግን ይህ ሁሉ ጡርንባ የወያኔን ጭኽት ለማድመቅ እንጂ እውነትን የተመረኮዘ አይደለም። ወያኔዎች አይደሉ እንዴ አሁን እኔ ኤርትራዊ ነኝ እንጂ ትግራዋይ አይደለሁም እያሉ ሰው የሚያማቱት። ወደ ናፈቁት ሃገር ሂዶ መኖር ነው። ከላይ በተለጠፈልን ጽሁፍ ላይ የትግራይ መንግስትና ሰራዊት ጂኖሳይድ ፈጻሚዎችን እንደሚያጠፋ ይዝታል። አይ ዓለም። ማን ነው አሁን በአማራና በአፋር ክልል ሰውና እንስሳ የሚገድለው? የሰላሙ ፕሮፌሴር ፕሮፌሰር ከመሆኑ በፊት በእንግሊዝ ሃገር ሲማር ያልተማረው ነገር የሰው ልጅን የክፋት ስነልቦና ነው። ለዚህም ነው አሁን ያለውን እይታ ሸውራራ ያደረገው። ልክ እንደ አሜሪካኖች የወሬ አውታር ውሸትን አጣፍጦ ማቅረብ። ሌላው በአሜሪካ ተጠዋሪ እነርሱ ሁሌ እርዳታ ሰጪ አድርጎ ወሬ መንዛት። በምላሹ እነርሱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ከየሃገራቱ የሚመዘብሩትን ምዝበራ አለመዘገብ። ይህ ነው ዲሞክራሲ ለራስ ኑሮ ለራስ መሞት። የሌላው ሰቆቃና እንባ የነጭ ካለሆነ በስተቀር የማይታሰብበት። ትህነግ ኤርትራዊያንን የሚጨፈጭፍበት ጉልበት የለውም። የኤርትራ ጦር መቀሌ በሳምንት ውስጥ መግባት ይችላል። ግን ያ አይደረግም። የሚገርመው ከአሁን በህዋላ ለትግራይ ድንበር ብሎ የሚሞት ኢትዮጵያዊ አይኖርም። ኢትዮጵያዊ አይደለንም ብለውናልና። አልፎ ተርፎም ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦል ድረስ ይጓዛሉ። እስቲ እባካችሁ እዚያ እናግኛችሁ ሂድልን። አረመኔ። የአረመኔ መንጋ። ከሰው ባህሪ የወጣ በራሱ ዘርና ቋንቋ የሰከረ ዓለም አቀፋዊ ወይም አህጉራዊ እይታ የሌለው የእብዶች ስብስብ። ፈጣሪ ያጥፋችሁ። ምንኛ በዘራቸው እንደ ሰከሩ ለማወቅ ከፈለጋችሁ የዓለም የጤና ድርጅት ሃላፊው የትግራይ ህዝብ ተራበ እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ ተቸገረ ብሎ አያውቅም። ደም አፍሳሽና መሰሪ ሰው የአለም የጤና ድርጅት ሃላፊ ያደረገው ራሱ ተአማኒነት የሌለው የሌቦችና የአታላዪች ጥርቅም መሆኑ የዚህ ሰው ዳግም ምርጫ ያሳያል። ነጩ አለም አፍራሽ ሃይልን ይወዳል። መስፈርቱ ለእነርሱ መታዘዝ ብቻ ነው። የዚህ የስም የሰላምና የግጭት ፕሮፌሰርም ጡርንባ በወያኔ ክፍያ የጎለበተ ነው። በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule