በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ለሚከሰቱ ግጭቶችና የሰላም እጦት ችግሮች ሙስና ዋነኛው መንስኤ መሆኑን ትራንስፓረንሲ ኢትዮጵያ አስታወቀ። ባለፈው ዓመት በተካሄደው ጥናት መሰረት ኢትዮጵያ በሙስና ከዓለም 87ኛ ደረጃ ላይ እንደነበረች ተጠቁሟል። የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ካሳሁን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ሙስና በኢትዮጵያ እየተከሰቱ ላሉ ግጭቶችና የሰላም እጦቶች ዋነኛ መንስኤ ነው። ኢትዮጵያ የተለያዩ የጸረ ሙስና ስምምነቶችን ብታደርግም፤ የጸረ ሙስና ትግሉን የሚያጠናክሩ ተቋማት አለመኖራቸው ውጤታማ ስራ እንዳይሰራ ምክንያት ሆኗል ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ። በኢትዮጵያ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችና የሰላም እጦቶች በአንድም ሆነ በሌላ ከሙስና ጋር የተያያዙ እንደሆኑ የተናገሩት አቶ ሳሙኤል፤ ሙስናና ብልሹ … [Read more...] about የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ
Middle Column
ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ
ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል የተባሉ የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት የኮንስትራክሽን እና ሎጂስቲክስ ም/ዳይሬክተር የሆኑት ተስፋዬ ደሜን ጨምሮ በአራት የአገልግሎቱ ሰራተኞች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ። በኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ስም 29 ሺሕ 200 ኩንታል ሲሚንቶ ከኹለት ፋብሪካዎች ገዝተው ለግለሰቦች በመሸጥ ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ለግል ጥቅማቸው ባዋሉ የአገልግሎቱ የኮንስትራክሽን እና ሎጂስቲክስ ም/ዳይሬክተርን ጨምሮ በአራት ሰራተኞች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል፡፡ የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው፤ ተከሳሾች በብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ውስጥ 1ኛ ተስፋዬ ደሜ … [Read more...] about ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ
የኢትዮጵያ ወርቅ የት ገባ?
ኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ወራት የወርቅ ምርት “በከፍተኛ መጠን” መቀነሱን የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ተናገሩ። የባንኩ ገዢ በሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ምክንያት ጥብቅ የፊስካል እና የገንዘብ ፖሊስ መከተል አለመቻሉን ገልጸዋል። ዶ/ር ይናገር ይህን ያሉት የብሔራዊ ባንክን የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ እና የሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት፤ ለፓርላማ የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ ሐሙስ ህዳር 29 ባቀረቡበት ወቅት ነው። የባንኩ ገዢ በዚሁ ሪፖርታቸው፤ በሩብ ዓመቱ የነበረውን የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ ዳስሰዋል። የሩብ ዓመቱ የወጪ ንግድ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር “መጠነኛ ጭማሪ” ማሳየቱን ያነሱት ዶ/ር ይናገር፤ ገቢው “በተወሰኑ ዘርፎች ላይ” የተገኘ መሆኑን ጠቁመዋል። ሀገሪቱ ላገኘችው ገቢ “ከፍተኛውን ድርሻ” የያዙት አበባ እና ቡና መሆናቸውን … [Read more...] about የኢትዮጵያ ወርቅ የት ገባ?
በፊርማው ስምምነት መሠረት የትህነግ ታጣቂዎች ከ፱ ግምባሮች ለቀቁ
በሰላም ስምምነቱ መሰረት የትግራይ ታጣቂዎች በስራቸው ከነበሩ የውግያ ግምባሮች ለቀው መውጣት እንደጀመሩ ተገልጿል። ታጣቂዎቹ ከደቡብ፣ ማይ ቅነጣል፣ ዛላምበሳ፣ ነበለት፣ ጨርጨር፣ ኩኩፍቶ፣ ሕጉምብርዳ፣ በሪተኽላይ እና አበርገለ ለቆ ግንባሮች ነው መውጣት እንደጀመሩ ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን የተሰማው። ከጥቂት ቀናት በፊት (የትግራይ ኃይሎች አዛዥ) ታደሰ ወረደ በሰጡት መግለጫ በናይሮቢው ስምምነት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ለኃይሎቻቸው ኦረንቴሽን (orientation) ሲሰጥ እንደነበር እና ይኸው ኦረንቴሽን እንዳለቀ ኃይላቸው ካለበት ቦታ Disengage አድርጎ / ተላቆ የውጊያ ግንባሮች የማፍረስ እና ሰራዊቱ ወደ ተቀመጠለት ቦታ እንደሚጓጓዝ መግለፃቸው አይዘነጋም። አዛዥ ኃላፊው ታደሰ ፤ "የሎጅስቲክስ አቅማችን ወይም የማጓጓዝ አቅማችን እስከፈቀደ ድረስ በአንድ ጊዜም … [Read more...] about በፊርማው ስምምነት መሠረት የትህነግ ታጣቂዎች ከ፱ ግምባሮች ለቀቁ
ይቅርታ ያደረገን ሕዝብ ማታለል አይገባም
ተሃድሶ ጥሩና መጥፎ ጎኖች አሉት። በተለይ ሥርነቀል አቢዮት በተለመደባት አገራችን ተሃድሶ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች አሉት። ያንን መዘርዘር ግን አሁን አስፈላጊ አይደለም። የዚህ ርዕሰ አንቀጽ ዓላማ በተሃድሶ ምክንያት እየደረሰ ያለውና መረን የለቀቀ ተግባር እርምጃ እንዲወሰድበት ለመጠቆም ነው። ትህነግ ያላሰበውን ሥልጣን ተቆጣጦሮ አዲስ አበባ ሲገባና ካድሬዎቹ የዲዛይነር ልብስ መልበስ ሲጀምሩ የተበላሸው ጭንቅላታቸው ያው በበረሃው እሳቤ ነበር የቀጠለው። ከዓመታት በኋላ የድርጅቱን መበስበስ እንደማያውቅ ሆኖ ያስደነቀው ሊቀጳጳስ መለስ ዜናዊ “እስከ እንጥላችን ገምተናል” ነበር ያለው። የዘራውን እንደሚያጭድ አለማሰቡ ዕውቀት ጸዴ በረኸኛ መሆኑን በራሱ አስመስክሮበታል። ያገኙትን ሁሉ መዝረፍ ሙያቸው አድርገው የተካኑት ትህነጋውያንና ኢህአዴጋውያን ሊቀ ደናቁርት ካድሬዎች በለውጥ ስም ልክ … [Read more...] about ይቅርታ ያደረገን ሕዝብ ማታለል አይገባም
መፍትሔ የሚሹ የኢትዮጵያ የጎን ውጋቶች
ኢትዮጵያ ባለፉት አራት በላይ በሆኑ ዓመታት ከባድ ጫናዎችን ተሸክማ ቆይታለች። ይልቁንም የሰሜኑ ጦርነት በውስጥም በውጭም ገፊና ሳቢ ምክንያቶችን ፈጥሮ ሲያናውጣት ቆይቷል። ይኸው ጦርነት ኹለት ዓመት ሊደፍን የዋዜማው እለት የተደረሰው የሰላም ስምምነት በጉዳዩ ላይ የብዙዎች ተስፋ እንዲያንሰራራ አድርጓል። ኢትዮጵያን ችግሮቿ ሁሉ የተቀረፉ ያህል ብዙዎች ተሰምቷቸዋል። ሆኖም አሁንም ኢትዮጵያ የጎን ውጋት የሆኗት ችግሮች አሉ። የወሰንና አስተዳደር ጥያቄዎች፣ የታጣቂ ኃይሎች እንቅስቃሴ፣ የምጣኔ ሀብት መዳከም፣ ማንነትን መሠረት ያደረጉ የተለያዩ ጥቃቶች አሁንም ይስተዋላሉ። እናም ኢትዮጵያ ችግሮቿን ቁልቁል ደርድራ አንድ በአንድ በማስተካከል፣ እንደ ሰሜኑ ጦርነት ሁሉ በኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል እና ጋምቤላ እንዲሁም በሌሎች ክልሎችም ሌሎቹንም ችግሮች እንድትቀርፍ ይጠበቅባታል። በሰብአዊ … [Read more...] about መፍትሔ የሚሹ የኢትዮጵያ የጎን ውጋቶች
በፓርላማው ውሎ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሾች
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች‼️ የምክር ቤት አባላቱ ፦- የስምምነቱ ሂደት እንደምታውና ፋይዳው ምንድነው ?- በጦርነቱ የተጐዱ አካባቢዎችን ፍትሃዊ በሆነ መልኩ የመልሶ ለመገንባት ምን ዝግጅት ተደርጓል ?- አንዳንዶቹ ስምምነቱ ከTPLF እንጂ ከTDF ጋር አይደለም ? ... ወዘተ የሚሉ የተለያዩ ሃሳቦችን እየሠነዘሩ ይገኛሉ ፤ የእነኚህ አካላት ፍላጎት ምንድን ነው ? ውሳኔዎችንስ ተግባራዊ ለማድረግ እነቅፋት አይሆንም ወይ?- የምክክር ኮሚሽን የእስካሁኑ አፈፃፀም ያለበት ደረጃ እንዲሁም በውይይት ሂደቱ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ምቹ ሁኔታዎችና ስጋቶች ምንድን ናቸው?- ውይይቱ ተሳክቶ መላው የሀገራችን ሕዝቦች ወደ ሚናፍቁት ልማት ፊታቸውን እንዲያዞሩ ከባለድርሻ አካላት ማለትም ከምሁራ፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ ወጣቶችና ከመላው … [Read more...] about በፓርላማው ውሎ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሾች
“ወልቃይቴ፤ ወልቃይቴ ነው፤ ይታወቃል” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
በዛሬው የፓርላማ ውሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ስለ ወልቃይት የተናገሩት፤ “ወልቃይትን በሚመለከት የሚነገሩ ሽረባዎች፣ ሴራዎች፣ conspiracies ብዙ እሰማለሁ። የኢትዮጵያ መንግስት በእነዚህ ሽረባዎች ውስጥ እጁ የለበትም። የወልቃይት ህዝብ እንዲገነዘብ የምንፈልገው፤ የሚወራው፣ የሚናፈሰው አሉባልታ ውስጥ የኢትዮጵያ መንግስት እጁ የለበትም።” “እኛ ደቡብ አፍሪካ የሄድንው ወልቃይት ወደ አማራ ይሁን ወደ ትግራይ ይሁን የሚለውን ለመወሰን አይደለም። የፕሪቶሪያው ‘ሰሚትም’ ይኸን ለመወሰን ስልጣን የለውም። ምን አገባው እና ነው የኢትዮጵያን መሬት እዚያ ሂድ እዚህ ሂድ የሚለው? እኛ እዚያ የሄድንው እንዴት ሰላም አምጥተን በንግግር ችግሮቻችንን እንፍታ ለማለት ነው። ለምን ወልቃይት ተስቦ እዚያ ውስጥ እንደሚገባ አላውቅም።” “ወልቃይት ብቻ አይደለም፤ ሰሜን ሸዋ ላይ ኦሮሚያ … [Read more...] about “ወልቃይቴ፤ ወልቃይቴ ነው፤ ይታወቃል” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
“(ላለፉት 4 ዓመታት) ሪፖርት ባለማቅረባችን ክቡር አፈ ጉባዔውን በግል እወቅሳቸዋለሁ” ወ/ሮ መዓዛ
የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚ አካል የፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ማክበር ካልቻለ ሥርዓት ተሰብሯል ማለት እንደሆነ፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ተናገሩ። ላለፉት አራት ዓመታት ሪፖርት ሊያቀርቡ ባለመቻላቸው አፈጉባዔውን ወቅሰዋል። ፕሬዚዳንቷ ይህን የተናገሩት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ፣ ከፍተኛና ጠቅላይ፣ እንዲሁም የሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን፣ የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድና የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ ክንውን ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በገመገመበት ወቅት ነው። ምክር ቤቱ ባካሄደው የአንድ ቀን የፍርድ ቤቶች ግምገማ ከምክር ቤት አባላትና ከሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች፣ ፍርድ ቤት ከወሰነላቸው በኋላ ውሳኔ የማይከበርላቸውን አካላት በተመለከተ በርካታ ጥያቄዎች ቀርበዋል። የሕግ … [Read more...] about “(ላለፉት 4 ዓመታት) ሪፖርት ባለማቅረባችን ክቡር አፈ ጉባዔውን በግል እወቅሳቸዋለሁ” ወ/ሮ መዓዛ
ትጥቅ ማስፈታቱ ተግባራዊ መሆን ጀመረ፣ ክልሉም ስምምነቱን በይፋ ተቀበለ
አሜሪካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን እደግፋለሁ አለች ረቡዕ ይፋ በሆነው የፕሪቶርያ ስምምነት መሰረት የትጥቅ ማስፈታቱ ሥራ መጀመሩ ታወቀ። በቅርቡ የሽግግር አስተዳደር የሚቋቋምለት የትግራይ ክልል ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤትም ስምምነቱን መቀበሉን በይፋ አረጋግጦ መግለጫ አሰራጨ። “… ይህ ስምምነት በተፈረመ በሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ የሁለቱ ወገኖች ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተገናኝተው ይነጋገራሉ” በሚለው ግልጽና በፊርማ የጸደቀ ውል መሰረት የኢፌድሪ ጠቅላይ ኢታማዦር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላና የትህነግ ማዕከላዊ ኮማንድ ፖስት አዛዥ የሚባሉት ታደሰ ወረደ በዛሬው ዕለት ተገናኝተው መናገራቸውን ኢ.ኤም.ኤስ. የተሰኘው የእነ ሲሳይ አጌና ሚዲያ ቀድሞ ቢገልጽም የኢትዮ 12 የአዲስ አበባ ዘጋቢ የዜናውን ትክክለኛነት ማረጋገጡን ገልጿል። የትህነግ ጦር ሌላ አዛዥ የሆኑት ባለሃብቱ ጻድቃንና … [Read more...] about ትጥቅ ማስፈታቱ ተግባራዊ መሆን ጀመረ፣ ክልሉም ስምምነቱን በይፋ ተቀበለ