ጠቅላይ ኤታ ማጆር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ከባላገሩ ቲቪ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል። ስለ ትልውድና አስተዳደጋቸው፣ ቀድሞው ሠራዊት በህወሓት/ትህነግ “ጨፍጫፊ” ስለመባሉ፣ በህወሓት ላይ የተወሰደው ዘመቻና ውጤቱ፣ ስለተያዙት የትህነግ ሹሞች፣ ወዘተ ሰፋ ያለ መግለጫ ሰጥተዋል። ዘመቻው በድል የተጠናቀቀው በሁለት ሳምንት መሆኑን የጠቆሙት ጄኔራሉ የወንበዴዎቹ ለቀማ ብቻ ተጨማሪ ጊዜ የወሰደ መሆኑን ጠቁመዋል። “እኛ የመግደል ሱስ የለብንም” ያሉት ኤታማጆር ሹሙ አብዛኛዎቹ የትህነግ አመራሮች እጃቸውን እንደሰጡ የቀሩትም እንዲሰጡ አሁንም ጥያቄ እናቀርባለን። ካልሆነ ግን የገቡበት ገብተን አንድም ሰው ሳናስቀር ለሕግ እናቀርባቸዋለን - በተለም አመራሩን ብለዋል። ትህነግ አደርገዋለሁ ስለሚለው ቀጣይ የሽምቅ ውጊያ ሲናገሩ፤ “ይሄ ሽምቅ እናደርጋለን ምናምን የሚሉት ጠቅላላ … [Read more...] about “የገቡበት ገብተን አንድ ሰው አናስቀርም – በተለይ አመራሩን” ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ
Middle Column
የትግራይ ገበሬና የከተማ ነዋሪ በሠራዊታችን ላይ አንድ ጥይት አልተኮሰም – ሪር አድሚራል ክንዱ
በቅርቡም በትግራይ ክልል በተካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ላይ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የሚዲያ ባለሙያዎች ወደስፍራው በመላክ ትክክኛ መረጃ ወደህዝቡ እንዲደረስ ማድረጉ ይታወቃል። የሚዲያ ባለሙያዎቹ በስፍራው ተገኝተው የሠሯቸውን ዘገባዎችና ያስቀሯቸውን ምስሎች የሚዘክር የፎቶ አውደ ርዕይም ከጥር 22 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከፍቶ ለህዝብ በማሳየት ላይ ይገኛል። “ዘመቻ ለፍትህ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን ይህንን የፎቶ አውደ ርዕይ የኢፌዴሪ የባህር ሃይል ዋና አዛዥና ሬር አድሚራል ክንዱ ገዙ፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አወሉ አብዲ እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ታደሰ በጋራ የከፈቱ ሲሆን፣ በዕለቱ የባህር ሃይል ዋና አዛዥ ሬር አድሚራል ክንዱ ገዙ ያሰሙትን መልዕክት አዲስ ዘመን እንደሚከተለው አጠናቅሮ … [Read more...] about የትግራይ ገበሬና የከተማ ነዋሪ በሠራዊታችን ላይ አንድ ጥይት አልተኮሰም – ሪር አድሚራል ክንዱ
ኢንተርፖል፤ የህወሃት ሳምሪዎች የማይካድራ ጭፍጭፋ ከቦኮሃራም የከፋ ነው
በማይካድራ ሳምሪ በተሰኙ የተደራጁ ወጣቶች የተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ ቦኮሀራም ናይጄሪያ ላይ በተመሳሳይ ወር ከፈፀመው ወንጀል የበለጠ እንደሆነ ኢንተርፖል አስታወቀ። ዓለም አቀፉ የፖሊስ ትብብር ተቋም ኢንተርፖል በፈረንጆቹ የዘመን አቆጣጠር በወርሃ ህዳር 2020 ዓ.ም በመላው ዓለም የተፈፀሙ 10 አስከፊ የሽብር ጥቃት አስመልክቶ ሪፖርቱን አውጥቷል። እንደዚህ ሪፖርት ከሆነ በህወሃት ቡድን አደራጅነት ማይካድራ ላይ የተፈፀመው የጅምላ ግድያ ቦኮሃራምና ሌሎች የሽብር ቡድኖች በተለዩ ሀገራት ከፈፀሟቸው አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች በመብለጥ በርካታ ንፁሃን ሰዎች ህይወታቸውን ያጡበት ኢሰብዓዊ ድርጊት ነው፡፡ የህወሃት ቡድን አስታጥቆ እንዳሰማራቸው በተገለጸው ሳምሪ የተሰኙ የወጣቶች የጥቃት ቡድን በማይካድራ በፈፀሙት ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ 600 ንፁሃን ዜጎች … [Read more...] about ኢንተርፖል፤ የህወሃት ሳምሪዎች የማይካድራ ጭፍጭፋ ከቦኮሃራም የከፋ ነው
ጄኔራሎች “ተገድለዋል” በሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሌ/ጄ አበባው ታደሰን ጨምሮ ጄኔራል መኮንኖችንና ከፍተኛ የጦር አዛዦች በትግራይ ልዩ ሃይል ተገድለዋል የሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ። ግለሰቡ በተጨማሪም ሎችንም የሀሰት መረጃዎች "የትግራይ ልዩ ሃይል ድል" በሚል ርዕስ ፍሪደም ቲቪ በተባለ የዩቲዩብ አድራሻ በተለያ ጊዜ ያልተጨበጠ መረጃ ያሰራጭ እንደነበረ ተገልጿል። ይህ ሃጎስ ሰልጠነ ፍስሃዬ የተባለው ግለሰብ ከአዲስ አበባ በመነሳት ኬንያ ከዛም ወደ ዩጋንዳ ካምፓላ ለመውጣት ሲሞክር ሃዋሳ ላይ በደቡብ ዕዝ የሰራዊት አባላት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። ስራውን እንዲሰራ የቀጠረው እንግሊዝ አገር የሚኖረው ዳዊት አብርሃ ዘረዝጊ የተባለ ሰው መሆኑንና ለአገልግሎቱም 6 መቶ የአሜሪካን ዶላር ይከፍለው እንደነበር ግለሰቡ … [Read more...] about ጄኔራሎች “ተገድለዋል” በሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰሞኑን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን ያላግባብ ተጠ ቅመው አገልግሎት መሥሪያ ቤቱን በተመለከተ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለማደናገር ሲሞክሩ የነበሩ አንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ከህገወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ ተቋሙ አሳስቧል፡፡ ከዚህ በኋላ የሀሰት መረጃዎችንና አሉባልታዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾች በማሰራጨት የሀገርን ብሄራዊ ጥቅምና ህልውና ለመጉዳት እንዲሁም የህዝብን ሰላምና ደህንነት ስጋት ላይ ለመጣል የሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ማስረጃዎችን በማጠናቀር በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እንደሚያደርግ ከወዲሁ ያሳውቃል። ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በሀገር ላይ … [Read more...] about የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ
“…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ
ጁንታው ትግራይን ለ፴ ዓመታት ያስተዳደረው በሴፍቲ ኔት ነው በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ እንዳልሆነ ተደርጎ የሚናፈሰው ወሬም ከእውነት የራቀ ነው አሉ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉ ነጋ። የፌዴራል መንግሥት በክልሉ የተጠናከረ ሰብአዊ ድጋፍ እያደረገ ነው ሲሉ ተናግረዋል። “ድጋፉ እየቀረበ አይደለም” በሚል ሃሰተኛ መረጃ የሚያናፍሱ አካላት የፖለቲካ ትርፍ በመፈለግ የሚፈጽሙት ድርጊት ነው ሲሉም ገልፀዋል። በክልሉ የመብራት፣ የውሃ እና የባንክ አገልግሎቶች በበርካታ አካባቢዎች መጀመራቸውን አንስተው፤ አገልግሎት ባልተጀመረባቸው አንዳንድ አካባቢዎች ደመወዝ ላልተከፈላቸው የመንግስት ሰራተኞች እንዲከፈላቸው እየተሰራ ነው ብለዋል። ሥራ አስፈጻሚው ዶክተር ሙሉ ነጋ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ የትግራይ … [Read more...] about “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ
ህወሓት ተሠረዘ!!!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህግ ከተቋቋመባቸው ዋና ዋና ተግባራት አንዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድጋፍ፥ ቁጥጥር እና ክትትል ነው። በመሆኑም በምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት ፓርቲዎች የተለያዩ መስፈርቶችን ማሟላታቸውን ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህም መሰረት ቀደም ብሎ መስፈርት አሟልተው ምዝገባቸው የተጠናቀቀ እና በሂደት ላይ ያሉ ፓርቲዎች ዝርዝርን ማሳወቁ ይታወሳል። ቦርዱ ከዚህ ቀደም ውሳኔ ያልሰጠባቸው እንዲሁም የተጠየቁትን ማብራሪያዎች ያቀረቡ ፓርቲዎችን አስመልክቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል። 1. ቦርዱ ህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ሕወሃት) የአመጻ ተግባር ላይ ተሰማርቷል ወይ የሚለውን ሁኔታ ለማጣራት በፓርቲው የተሰጡ መግለጫዎችን እና በይፋ የሚታወቁ ጥሬ ሃቆችን በማቅረብ ፓርቲው ኃይልን መሠረት ያደረገ የአመጻ ተግባር … [Read more...] about ህወሓት ተሠረዘ!!!
ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው
“ስብሃትን “አቦይ” አልላቸውም … እንዲህ ዓይነት አባት አልመኝም” ጄኔራል ባጫ የጁንታው ፈጣሪና መሪ ስብሃት ነጋ በመከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስልና ፎቶ ሲስቁ ታይተዋል። በርካቶችም ስብሃት ምን አሉ በሚል ሲነጋገሩ ነበር። ሌፍተናንት ጄኔራል ባጫ ደበሌ እንደገለጹት ስብሃት ከተያዙ በኋላ አስተያየት ሰጥተዋል። ስብሃት በተያዙበት ሰዓት ለከፍተኛ የመከላከያ መኮንኖች፣ “እኛ እኮ ከሞትን ቆይተናል“ የሚል አስተያየት እንደሰጡ ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ስብሃት ከመያዛቸው አስቀድሞ “ቢያዙ ምን ይሉ ይሆን“ ብለው ጄነራሎቹ ይወያዩ እንደነበር የገለጹት ሌፍተናንት ጄነራል ባጫ “ግለሰቡ ቢያዙ ሕገ መንግሥቱ ጥሩ ነው ፤ ሕገ መንግሥቱ እንደዚህ ነው… ብለው ነው የሚያወሩት” የሚል ግምት በጄኔራሎቹ ሀሳብ … [Read more...] about ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው
ለትምህርት እንዲሆነን
ታላቁ መጽሐፍ የተጻፈበትን ምክንያት ሐዋርያው ጳውሎስ ሲናገር “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር” ተጻፈ ይላል። በአገራችን የፖለቲካ ታሪክ እጅግ ዘግናኝ ጊዜያት አሳልፈናል። በሥልጣን የተቀመጠ የሚወርድ እስከማይመስለውና ሰብዓዊነቱን እስኪዘነጋ ድረስ ሕዝብን ሲበድል ይኖራል። የሕይወቱ መጽሐፍ ሲጠናቀቅ ይሰናበታል። ስንብቱ ግን በአሰቃቂና አሳፋሪ ሁኔታ ሲሆን መመልከቱ በየዘመናቱ የመሰከርነው ሐቅ ነው። ንጉሡ በደርግ ሲተኩ፤ ደርግ “ለለውጥ ባጎፈረው” ህወሓት ሲተካ፤ አሁን ደግሞ አይደረስብንም፣ አንበገርም፣ እንደ ደርግ አንሆንም፣ ዓቅምም፣ ገንዘብም፣ ሁሉም ነገር አለን ሲል የነበረው በረኸኛው የወንበዴ ጥርቅም ከየጉድጓዱና ሰርጡ እንደ አውሬ … [Read more...] about ለትምህርት እንዲሆነን
“ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ
አባይ ወልዱ እና አብረሀም ተከስተን ጨምሮ ዋነኛ የጁንታው አመራሮች የነበሩ በቁጥጥር ስር ውለው ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። አዲስ አበባ ከገቡትና አገርን ለመበታተን አቅደው በመከላከያ ሠራዊት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ካደረጉ አሸባሪዎችና ዋነኛ የጁንታው አመራሮች መካከል፤ አባይ ወልዱ የቀድሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የነበረ አብርሃም ተከስተ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የነበረ ረዳኢ በርሄ የክልሉ ኦዲተር ሃላፊ የነበረ ሙለታ ይርጋ የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊ የነበረ ዕቁባይ በርሄ የሃይማኖት ጉዳይ ክትትል ሃላፊ የነበረ ጌታቸው ተፈሪ የክልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤትና የሠላምና ደህንነት ሃላፊ የነበረ ኪሮስ ሃጎስ የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ የነበረች ንጋቱ አንገሶም አምደማርያም ተሰማ እነዚህ የጁንታው ከፍተኛ … [Read more...] about “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ