በቦሌ ክፍለ ከተማ 2 ሚሊዮን 3 ሺህ 407 የሀሰተኛ ብር ኖት ሲያዘጋጁ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። ለአቤቱታ ወደ ፖሊስ በመጡ ሰዎች ጥቆማ ሰጪነት ነው ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ያስታወቀው። የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀልን ትራፊክ አደጋ ምርመራ ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ያሬድ ታረቀኝ መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም ሁለት ተጠርጣሪዎች በአጠቃላይ 2 ሚሊዮን 3 ሺህ 407 ሀሰተኛ የብር ኖት፤ የአሜሪካ ዶላር እና የተለያዩ ሐገራትን ገንዘቦችን በመኖሪያ ቤታቸው ሲያዘጋጁ መያዛቸውን ገልጸዋል። ከሚጠቀሙበት የተለያዩ ቁሳቁሶች ጋርም እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ አስረድተዋል። ተጠርጣሪዎቹ የኮትዲዩቫር ተወላጆች … [Read more...] about ከ2.3 ሚሊዮን ብር በላይ የሀሰተኛ ብር ኖት ሲያዘጋጁ የነበሩ ተያዙ
Archives for October 2020
በቦሌ ኤርፖርት 3.4 ሚሊዮን ብር የሚገመት ወርቅ በቁጥጥር ሥር ዋለ
አንድ ነጥብ አራት ኪሎ ግራም መጠን ያለው ወርቅ አዲስ አበባ ከሚገኘው የካሜሮን ኤምባሲ ወደ ካሜሮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተላከ መልዕክት በማስመሰል ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር በቁጥጥር ስር ዋለ። በአዲስ አበባ ኤርፖርት ወደ ካሜሮን ለመጓዝ ዝግጅት ሲያደርግ የነበረ መንገደኛ የዲፕሎማቲክ መልዕክት በማስመሰል ለማሳለፍ ሲሞክር በማሽን በታገዘ ፍተሻ ሊያዝ ችሏል። የተያዘው ወርቅ በወቅታዊ የብሔራዊ ባንክ የመግዣ ዋጋ ሶስት ሚሊዮን አራት መቶ ሺህ (3,400,000) ብር ግምታዊ ዋጋ ወጥቶለታል። የገቢዎች ሚኒስቴር የሀገርን ሀብት ከምዝበራ የታደጉ የጉምሩክ ሰራተኞች እና የፀጥታ አካላት ምስጋናውን አቅርቧል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በቦሌ ኤርፖርት 3.4 ሚሊዮን ብር የሚገመት ወርቅ በቁጥጥር ሥር ዋለ
የመተከል ዞን ሕዝብ ሊደራጅና ሊታጠቅ ይገባዋል – አቶ ደመቀ መኮንን
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በዛሬው (ሰኞ) ዕለት የተፈፀመውን አሳዛኝ ድርጊት መነሻ በማድረግ በመተከል ዞን ከሚመራው ኮማንድ ፖስት አመራር አካላት ጋር በዞኑ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ መክረዋል። ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች ቤተሰቦች እና ወዳጆች መፅናናትን ተመኝተዋል። በዞን የተለየዩ አካባቢዎች ያለውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት ኮማንድ ፖስት ተደራጅቶ የራሱን ዕቅድ አዘጋጅቶ ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ቢሆንም፤ አሁንም የዜጎች ህይወት በአሳዛኝ ሁኔታ መጥፋት መቀጠሉ ሪፖርት ቀርቧል። በዚህ አካባቢም ሆነ በሌሎች ሠላምና ፀጥታን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመፍጠር የሴረኞችን ገመድ መበጣጠስ፣ ጠንካራ የህግ የበላይነት ማስከበር ህብረተሰቡ ራሱን የመከላከል አቅም እንዲኖረው ማድረግ ወሳኝ ተግባር መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል። ምክትል ጠቅላይ … [Read more...] about የመተከል ዞን ሕዝብ ሊደራጅና ሊታጠቅ ይገባዋል – አቶ ደመቀ መኮንን
በአፋር ህገወጥ የጦር መሳሪያ በመደበቅ የተጠረጠሩ ግለሰቦች ተያዙ
በአፋር ክልል የጭፍራ ወረዳ ፖሊስ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ደብቀው አግኝቻቸዋለሁ ያላቸውን ሁለት ተጠርጠሪዎች መያዙን አስታወቀ። የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር አብደላ ሁመድ ለኢዜአ እንደገለጹት ግለሰቦቹ የተያዙት ትላንት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ነው። በጭፍራ ከተማ ድንገት በተካሄደ የቤት ለቤት ፍተሻ ግለሰቦቹ ከደበቋቸው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ጋር መያዘቸውን ተናግረዋል ። በግለሰቦቹ መኖሪያ ቤቶች ተደብቀው ከተያዙ የጦር መሳሪያዎች መካከል አራት ክላሽንኮቨ ጠብመንጃና አራት ሽጉጦች እንደሚገኙበት ተናግረዋል። (ኢዜአ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በአፋር ህገወጥ የጦር መሳሪያ በመደበቅ የተጠረጠሩ ግለሰቦች ተያዙ
በአዲስ አበባ አስተዳደር በኃላፊነት የሚሠሩ የትህነግ አባላት ፓርቲያቸውን ከዱ
በአዲስ አበባ ከተማ በከተማው አስተዳደር በተለያየ የሃላፊነት ስፍራዎች የሚያገለግሉ የህወሓት አመራር የነበሩ አሁን ግን ብልፅግናን ለመቀላቀል የወሰኑ አባላት በህወሓት የተደረገላቸውን ጥሪ እንደማይቀበሉ አስታወቁ። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በህወሓት አባልነት ታቅፈው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እና ብልፅግና ከተመሰረተ ወዲህም በተለያየ የከተማው አስተዳደር የአመራርነት ቦታዎች ላይ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት አመራሮቹ በቅርቡ ህወሓት ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለረጅም ጊዜያት በህወሓት ውስጥ መቆየታቸውንና በተለያዩ የድርጅቱ የአመራር እርከን ሲያገለግሉም እንደነበር ገልፀዋል። ህወሓት በአሁኑ ሰዓት ህዝባዊነቱን ያጣ፤ ከዚያም አልፎ ሃገር ለማተራመስ በግልፅ እየሰራ ያለ ድርጅት በመሆኑ ከድርጅቱ ጋር መቀጠል እንደማይገባቸው እንዳመኑና በኢትዮጵያ እየመጣ … [Read more...] about በአዲስ አበባ አስተዳደር በኃላፊነት የሚሠሩ የትህነግ አባላት ፓርቲያቸውን ከዱ
ኢዜማ በአዲስ አበባ አስተዳደር ላይ ክስ መሠረተ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሰሰ። ፓርቲው ክሱን የመሰረተው የከተማው አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት በሰጠው ትዕዛዝ፤ የፓናል ውይይት እንዳያደርግ መከልከሉን በመቃወም ነው። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ፍትሐ ብሔር ችሎት ባለፈው አርብ መስከረም 30፤ 2013 የተከፈተው የክስ መዝገብ፤ በፓርቲው ላይ የደረሰው “የሁከት ተግባር እንዲታገድ” የሚጠይቅ ነው። ኢዜማ ይህን ክስ ለማቅረብ የተገደደው ሕገ መንግስታዊ የሆነው “የመሰብሰብ መብት” በተከሳሽ መስሪያ ቤት በተሰጠ ትዕዛዝ በመገደቡ መሆኑን ገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ለክስ ያበቃውን ትዕዛዝ ለፓርቲው የጻፈው ባለፈው ሳምንት ሰኞ መስከረም 25፤ 2013 ነበር። … [Read more...] about ኢዜማ በአዲስ አበባ አስተዳደር ላይ ክስ መሠረተ
አዲስ አበባ ብዙ ዋጋ የተከፈለባት ከተማ
1. መግቢያ፣ አዲስ አበባ ብዙ ዋጋ ተከፍሎባታል ሲባል ነገር ለማጣፈጥ የተነገረ ወሬ ሳይሆን በተጨባጭ የሆነና የተደረገ መሆኑን እኔ በህይወቴ ያየሁትን እንዲት ገተመኝ እንደ ምሳሌ ልጥቀስ። ስሜ ደረጀ ተፈራ ይባላል ተወልጄ ያደኩት አዲስ አበባ ፊትበር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። ሰፈራችን ለታላቁ ቤተመንግስት (ምኒልክ ቤ/መ) ቅርብ በመሆኑ የደርግ ቅልብ ወታደሮችም ሆኑ የወያኔ አጋዚ ጦር የአካባቢውን ጸጥታ ለማስከበር ብቻ ሳይሆን ኮረዶችንም ለማሽኮርመም እኛ ሰፈር አይጠፉም ነበር። በደርግም ሆነ በወያኔ አገዛዝ ዘመን አንድ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር ከቤተ መንግስት፣ የደርግ ቅልቦችና የወያኔ አጋዚ ጦር፣ ከውጭ ጉዳይ ሚ/ር አና ከፓሊስ ገራዥ ደግሞ ፌዴራል ፖሊሶች ክላሻቸውን እያንቀጫቀጩ መጀመሪያ የሚመጡት እኛ ሰፈር ነበር። በዚህ ላይ ኮ/ል መንግሥቱ … [Read more...] about አዲስ አበባ ብዙ ዋጋ የተከፈለባት ከተማ
ዳኛውማ “ደርግ” ነው
የመጽሐፉ ርዕስ፡ “ዳኛው ማነው?” የብርሃነ መስቀል እና የታደለች ህይወት በኢሕአፓ የትግል ታሪክ 2012 ዓ.ም. እና የብርሃነመስቀል የእሥርቤት ቃል ምርመራ ሰኔ1971 ዓ.ም. ሙሉውን የመጽሐፍ ግምገማ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣበ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው። … [Read more...] about ዳኛውማ “ደርግ” ነው
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ወቅታዊ መግለጫ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ መስከረም 15/2013 ዓ.ም ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባው፣ በከተማዋ የተጀመረውን ትምህርት ተሞክሮ እና አገልግሎቶች በአካታች ልማት (inclusive development) መርህ መሰረት አዲስ አበባ ዙሪያ ልዩ ዞን ወይም የኦሮሞ ብልጽግና “የፊንፊኔ ልዩ ዞን” በሚል መጠሪያ ባካተታቸው አካባቢዎች በሚገኙ 346 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚማሩ አንድ መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ(152,000) ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ፣ የተማሪ ደንብ ልብስ፣ጫማ እና የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችል 669,210,780 (ስድስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሚልዮን ሁለት መቶ አስር ሽህ ሰባት መቶ ሰማንያ ብር) በጀት በመመደብ ለእርዳታ አገልግሎቱ እንዲውል በልዩ ሁኔታ ውሳኔ አሳልፏል። ፓርቲያችን ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ … [Read more...] about የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ወቅታዊ መግለጫ
“In Honor and Remembrance of the Life of Professor Mesfin Woldemariam” Obang
Good Morning to everyone here. First of all, I would like to give my deepest sympathy to the family of Professor Mesfin Woldemariam and the great numbers of Ethiopians who consider him a great friend of the Ethiopian people for many generations. I also thank those who have given me the opportunity to speak today about one of greatest men I have been privileged to meet and know. This giant of a man has played an important and strategic role in my life and that of many others. Most people … [Read more...] about “In Honor and Remembrance of the Life of Professor Mesfin Woldemariam” Obang