በአዲስ አበባ ከተማ በከተማው አስተዳደር በተለያየ የሃላፊነት ስፍራዎች የሚያገለግሉ የህወሓት አመራር የነበሩ አሁን ግን ብልፅግናን ለመቀላቀል የወሰኑ አባላት በህወሓት የተደረገላቸውን ጥሪ እንደማይቀበሉ አስታወቁ።
እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በህወሓት አባልነት ታቅፈው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እና ብልፅግና ከተመሰረተ ወዲህም በተለያየ የከተማው አስተዳደር የአመራርነት ቦታዎች ላይ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት አመራሮቹ በቅርቡ ህወሓት ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለረጅም ጊዜያት በህወሓት ውስጥ መቆየታቸውንና በተለያዩ የድርጅቱ የአመራር እርከን ሲያገለግሉም እንደነበር ገልፀዋል።
ህወሓት በአሁኑ ሰዓት ህዝባዊነቱን ያጣ፤ ከዚያም አልፎ ሃገር ለማተራመስ በግልፅ እየሰራ ያለ ድርጅት በመሆኑ ከድርጅቱ ጋር መቀጠል እንደማይገባቸው እንዳመኑና በኢትዮጵያ እየመጣ ያለውን ለውጥ በማመን ከዚህ በኋላ ህዝብ እስከጠቀመ ድረስ በብልፅግና ዓላማዎች ታቅፈው ህዝብን ማገልገላቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
የብልፅግና አስተሳሰብ መቀየር ካልቻለው የህወሓት አሮጌ አስተሳሰብ ይልቅ የትግራይን ህዝብ ጥቅም ሊያስከብር እንደሚችልም አመራሮቹ መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። (EBC)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply