ቒጫ የጉራግኛ ቃል ሲሆን ጥሬ ትርጉሙም ደንብ፣ ስርዓት፣ ህግ ማለት ነው፡፡ የጉራጌ ህዝብ ባህላዊ ስርዓት ህግ ራሱን በራሱ መገልገል የጀመረው በስሙ እየተጠራ ባለበት ሀገር ከሰፈረበት ዘመን ጀምሮ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ይሁን እንጂ ህብረተሰቡ በየክፍሉ የሸንጎ ማእከላት በክፍለ ህዘብ ምድብ ባለበት ሁሉ የስሙ አሰያየሙ ይለያያል፡፡ መደበኛ ህግ ክፍሎች አሉት፡፡ የፍትሃብሄር፣ ወንጀለኛና የቤተሰብ (የጋብቻ) ስነስርዓት (ህግጋት) በውስጡ ይዟል፡፡ ይኽውም፡- የአንቂት ቒጫ - ይህ ደንብ በአጠቃላይ የጋብቻና የፍቺ ስነስርዓት የተደነገገበት ሲሆን የአተጫጨት፣ የቸግ ወይም የኒካ የሰርግ እና ፍቺ አፈጻጸም የሚዳኝበት ስርዓት (ደንብ) ነው፡፡የቅየ ቒጫ - ይህ ደንብ በሁለት ወሰንተኞች መካከል የድንበር መገፋፋት እንዳይኖር በሁለት ወገኞች ስምምነት በሚመረጡ ሽማግሌዎች አማካይነት … [Read more...] about የጆካ ዳኞች ባህላዊ የዳኝነት ሥነ-ሥርዓት
Archives for October 2020
መከላከያ ፈጣን ምላሽ የሚሰጡ ሁለት ዕዞች አቋቋመ
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት የሚሰጡኝን ግዳጆች በፍጥነት ማከናወን ያስችሉኛል ያላቸውን ተጨማሪ ሁለት ዕዞች ማደራጀቱን ትላንት አስታውቋል። አዲሶቹ ዕዞች በዚህ ዓመት ወደ ስራ ይገባሉ ተብሏል። ዕዞቹ በውስጥም በውጭም የሚቃጡ ጥቃቶችና ችግሮችን ፈጥነው ለመከላከል እንዲችሉ ታስቦ የተደራጁ እንደሆኑ ተገልጿል። ማዕከላዊና ሰሜን ምዕራብ አዲስ የተደራጁት ዕዞች ሲሆኑ የቀደሙት ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዕዞች መኖራቸው ይታወቃል። ዕዞቹ አዲስ አበባና ባሕር ዳር ላይ እንደሚደራጁ ሁለቱ ጄኔራሎች በመግለጫቸው አስታውቀዋል። (ኢዜአ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about መከላከያ ፈጣን ምላሽ የሚሰጡ ሁለት ዕዞች አቋቋመ
በአደገኛ እፅ አዘዋዋሪነት የተጠረጠሩ 14 የሚሆኑ የውጭ ሀገር ዜጎች ተያዙ!
በጥናት ላይ የተመሰረተ ክትትል በዓለም አቀፍ በአደገኛ እፅ አዘዋዋሪነት የተጠረጠሩ 13 ናይጄሪያውያንና አንዲት ብራዝላዊት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የኮሚሽኑ ወንጀል መከላከል ዘርፍ የአደገኛ እፅ ቁጥጥር ምክትል ዳይሬክቶሬት አባላት በዛሬው ዕለት በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ባደረጉት ፍተሻ ነው መነሻቸውን ላቲን አሜሪካ፣ ሳኦፖሎ ከተማ፣ መዳረሻቸውን ደግሞ የተለያዩ ሀገራት ለማድረግ በአውሮፕላን ሲጓዙ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ያዋሏቸው፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከ14 ኪ.ግ በላይ የሚመዝን ኮኬይን የተሰኘ አደገኛ ዕፅ ይዘው የተገኙ ሲሆን አደገኛ ዕፁ በላቲን አሜሪካ አካባቢ የሚመረትና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚዘዋወር መሆኑን የወንጀል መከላከል ዘርፍ የአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር ኦፕሬሽን ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር መንግስትአብ … [Read more...] about በአደገኛ እፅ አዘዋዋሪነት የተጠረጠሩ 14 የሚሆኑ የውጭ ሀገር ዜጎች ተያዙ!
የትህነግ አዲሱ ሤራ – አማራን በውክልና እልህ ውስጥ መክተት
* የአማራ ክልል ሰላም መሆን ለትህነግ ሤራ ስኬት ዕንቅፋት መሆኑ ተገመገመ ስብሃት ነጋ የሚባለው የትህነግ (ህወሃት) ማፊያ ቡድን አውራ ገና ወደ በረሃ ከመግባቱ በፊት አዲስ አበባ ፒያሳ ከገብረ ትንሳኤ ኬክ ቤት ዝቅ ብሎ ፍሎሪዳ ቡና ቤት መጠጥ ጠግቦ ሲወጣ ሽንት ያዘው። ከዚያም ከፍሎሪዳ እንደወጣ ያለው አደባባይ ላይ ለመሽናት አብሮት ከነበረው ባልደረባው ጋር በመሆን በሞቅታ እያወጋ ተጠጋ። አደባባዩ ላይ ሲሸና እየገለፈጠ “አማራ ላይ እንሽና” ማለቱን በወቅቱ አብሮት ከነበረው ሰው በጀብድ ሲወራ መስማቱን የመረጃ ምንጫችን ይናገራል። ራሱን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ብሎ በመሰየም አገር ሲያተራምስና ሲዘርፍ ኖሮ መንግሥት እንዲሆን ባዕዳን ኢትዮጵያ አናት ላይ አስቀምጠውት የነበረው የጥቂት ወንበዴዎች ጥርቅም ከጅምሩ የአማራን ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ ለማጥፋት … [Read more...] about የትህነግ አዲሱ ሤራ – አማራን በውክልና እልህ ውስጥ መክተት
ኦሮሚያን አቋርጠው የሚያልፉ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ፈተና
ከቅርብ ወራት ወዲህ ከአማራ ክልል በደጀን መስመር ወደ አዲስ አባባ የሚሄዱና የሚመለሱ ከባድ የደረቅ የጭነት ተሸከርካሪ አሽከርካሪዎች በተለይ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከጎሐጽዮን ደብረጉራቻ ባለው መስመር ማለፍ ፈተና ሆኖባቸዋል። አስተያየታቸውን ከሰጡት አሽከርካሪዎች መካከል አንዱ ”ከፍቼ ከተማ የቅርብ ርቀት ከምትገኝ ‘አሊ ዶሮ’ ከተባለች ቦታ ላይ መስከረም 30/2013 ዓ. ም የክልሉን የፀጥታ ኃይሎች የደንብ ልብስ የለበሱ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው የቆሰሉና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው አሽከርካሪዎችና ከ10 በላይ የተሰባበሩና የተቃጠሉ መኪናዎች አሉ” ብሏል።እየደረሰ ያለውን ጉዳት በዝርዝር ያስረዳው ይኸው አስተያት ሰጪ፣ በአሽከርካሪዎችና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ሰሞኑን እስከ 70ና 80 የሚሆኑ አሽከርካሪዎች ከነተሸከርካሪዎቻቸው ለአማራ ክልል የተለያዩ … [Read more...] about ኦሮሚያን አቋርጠው የሚያልፉ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ፈተና
አዲሱ የኢንሳ አርማ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የቀድሞዉን አርማ የቀየረ ሲሆን የቀድሞውን የኤጀንሲዉን አርማ (logo) እና ብራንዲንግ ለመቀየር ዲዛይኑን ለመስራት እንደ መነሻ የተወሰዱ ሃሳብ በአዲስ መልክ ከተሻሻለዉ የተቋሙ ተልዕኮ እና ራዕይ ጋር በማዛመድ የተሰራ ነዉ። ከእነዚህም ውስጥ በዋነኝነት ጋሻ (Shield)፡ ሳይበር(Cyber Security)፡ ቁልፍ (Key)፡የንስር አይን (An Eagle Eye)፡ የትክክል ምልክት (Right sign) የሚባሉትን ሃሳቦች አካቷል። ለተመረጠው የአርማ (logo) ዲዛይን ማብራራያ እንደ ሚከተለው ቀርቧል። የቀድሞዉ አርማ 1 ጋሻ (Shield) በኢትዮጵያ ታሪክ ብሎም በዓለም አቀፍ ታሪኮች ጥቃትን የመከላከያ መሳሪያ ቀዳሚ ተደርጎ የሚወሰደው አንዱ ጋሻ ነው፤ ስለዚህም በአርማው ላይ የሚታየው ጋሻ ማንኛውም አይነት ጥቃትን በብቃት መከላከል … [Read more...] about አዲሱ የኢንሳ አርማ
አራት የብዙሀን መገናኛ እስከ 23 ሚሊዮን ብር ተቀጡ
በብሮድካስት ባለስልጣን የህግና ማስታወቂያ ተወካይ ዳይሬክተር ዮናስ ፋንታዬ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የመገናኛ ብዙሀን አራት መገናኛ ብዙሀን ላይ የገንዘብ ቅጣት እንደተላለፈባቸው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል። ይሁንና ዳይሬክተሩ ቅጣቱ የተላለፈባቸውን መገናኛ ብዙሃን ስም ዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል። ቅጣቱ የተላለፈባቸው ጥራቱን ያልጠበቀ ምርት ማስታወቂያ በመልቀቃቸው እንደሆነ ተጠቁሟል። በዚህም ኃላፊነታቸውን ተወጥተው ባለመገኘታቸው በሚል በማስታወቂያ አዋጁ መሰረት ከ10 እስከ 23 ሚሊዮን ብር እንዲቀጡ ተደርጓል። በተመሳሳይም ማስታወቂያውን በግድየለሽነት በመስራት ለመገናኛ ብዙሀኑ ሰጥተዋል የተባሉት የማስታወቂያ ድርጅቶችም ላይ ቅጣት እንደተፈጸመባቸው ተገልጿል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about አራት የብዙሀን መገናኛ እስከ 23 ሚሊዮን ብር ተቀጡ
ለ6 የህወሓት ተጧሪዎች በ150 ሚሊዮን ብር የተገነቡት ቤቶች በ1.2 ቢሊዮን ብር ሊሸጡ ነው
ወሳኔው የተላለፈው በዚያን ጊዜው ህወሓት እንደፈለገ በሚዘውረው ፓርላማ ነበር። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “የኢህአዴግ ከፍተኛ ሹሞችን ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅም የሚያስከብር አዋጅ ጸደቀ” በሚል ርዕስ (February 13, 2017) ባተመው ዜና መረጃውን ሲዘግብ ይህንን ብለን ነበር፤ ከሁለት ዓመት በፊት በጭምጭምታ ደረጃ ወሬዉ ወደ አደባባይ የወጣዉ ባለሥልጣናት “ጡረታ” ሲወጡ የሚከበርላቸዉ ጥቅማጥቅም አሁን “ህጋዊ ዕዉቅና” አግኝቷል። ሐሙስ ዕለት በዋለዉ የኢህአዴግ “ፓርላማ” የህወሃት/ኢህአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከኃለፊነታቸዉ ሲነሱ ጥቅማጥቅማቸዉን የሚያስከብር አዋጅ ተሸሽሎ እንዲጸድቅ ተደርጓል። የተሻሻለዉ አዋጅ ከኃላፊነታቸዉ የሚነሱ የመንግስት ባለሥልጣናት እንደ የኃላፊነት ደረጃቸዉ የመቋቋሚያ አበል፣ የሥራ ስንብት ክፍያ፣መኖሪያ … [Read more...] about ለ6 የህወሓት ተጧሪዎች በ150 ሚሊዮን ብር የተገነቡት ቤቶች በ1.2 ቢሊዮን ብር ሊሸጡ ነው
ከጥቅምት ወር ጀምሮ ለትግራይ የበጀት ገንዘብ አይለቀቅም
ከትግራይ ክልል ጋር በተያያዘ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልሉ የሚገኙ የካቢኔ አባላት ህጋዊ ባልሆነ ምርጫ ተመርጠናል በሚል የሀገሪቱን ህገ መንግሥት በመጣሳቸው አሁን ባለው ሁኔታ የገንዘብ ሚኒስቴር ለትግራይ ክልል መንግሥት በጀት እንደማይለቅ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ተናገሩ። በትግራይ ክልል ለሚገኙ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች በኩል በተጠና ሁኔታ እንዲደርሳቸው ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል። ይህ ለሁለተኛው ሩብ ዓመት (ጥቅምት-ህዳር-ታህሣሥ) ከፌዴራል ለክልሎች የሚለቀቅ በጀት እንደሆነ ይታወቃል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ከጥቅምት ወር ጀምሮ ለትግራይ የበጀት ገንዘብ አይለቀቅም
የፌዴሬሽን ም/ቤት ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ስለ ህወሃት ማብራሪያ ሰጠ
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ህወኃትን በተመለከተ ባሳለፈው ውሳኔዎች ዙሪያ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ማብራሪያ ሰጥቷል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባዘጋጀው በዚህ መድረክ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና የቆንስላ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል ምርጫን በሚመለከት ባሳለፈው ውሳኔ ዙሪያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግሥት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጸሐፊ ወርቁ አዳሙ ማብራሪያ አቅርበዋል። በማብራሪያው በ2012ዓ.ም በኢትዮጵያ ሊደረግ የነበረው ሀገራዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ምክር ቤቱ በሕገ መንግሥት ትርጉም ተመሥርቶ ውሳኔ ማሳለፉ ተነስቷል፤ የትግራይ ክልልን የሚመራው ፓርቲ ህወሀት ውሳኔውን ወደ ጎን በመተው ኢ-ሕገ መንግሥታዊ በሆነ መንገድ ምርጫ በማድረግ ወደ መንግሥት … [Read more...] about የፌዴሬሽን ም/ቤት ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ስለ ህወሃት ማብራሪያ ሰጠ