በብሮድካስት ባለስልጣን የህግና ማስታወቂያ ተወካይ ዳይሬክተር ዮናስ ፋንታዬ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የመገናኛ ብዙሀን አራት መገናኛ ብዙሀን ላይ የገንዘብ ቅጣት እንደተላለፈባቸው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
ይሁንና ዳይሬክተሩ ቅጣቱ የተላለፈባቸውን መገናኛ ብዙሃን ስም ዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል።
ቅጣቱ የተላለፈባቸው ጥራቱን ያልጠበቀ ምርት ማስታወቂያ በመልቀቃቸው እንደሆነ ተጠቁሟል። በዚህም ኃላፊነታቸውን ተወጥተው ባለመገኘታቸው በሚል በማስታወቂያ አዋጁ መሰረት ከ10 እስከ 23 ሚሊዮን ብር እንዲቀጡ ተደርጓል።
በተመሳሳይም ማስታወቂያውን በግድየለሽነት በመስራት ለመገናኛ ብዙሀኑ ሰጥተዋል የተባሉት የማስታወቂያ ድርጅቶችም ላይ ቅጣት እንደተፈጸመባቸው ተገልጿል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
shiferaw berkineh says
በጣም ተደስቻለሁ።በቀጣይም በተለይ የበረሮ ማጥፊያ እየተባለ ምንም በረሮ የማይገሉ ኬሚካሎች በትላልቅ ሱፐር ማርኬቶች ሳይቀር እየተሸጠ ነው።