መስከረም 23 እና 24 የሚከበረውን የኢሬቻ በአል ለመበጥበጥ የተዘጋጁ 503 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ መሳሪያም ተገኝቶባቸዋል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ኮማንደር አራርሳ መርዳሳ ትላንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት፤ የኢሬቻ በዓል ላይ የሚሳተፉ የበዓሉ ታዳሚዎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ኮሚሽኑ በጥብቅ እየሰራ ነው። የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት በተለያየ አቅጣጫ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሀይሎች እንዳሉና ኮሚሽኑም እንደደረሰባቸው የገለፁት ኮማንደሩ፤ እስካሁን ድረስ 503 ሰዎች፣14 ክላሽ ፣ 26 ቦምብ እና 103 ሽጉጦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡ ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የኢሬቻ በዓል በኮረና ምክንያት እንደ ከዚህ ቀደሙ በርከት ባለ ሰው የማይከበር ሲሆን በገዳ … [Read more...] about የኢሬቻ በዓልን ለመረበሽ የተዘጋጁ 503 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
Archives for October 2020
በአዲስ አበባ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ በላይ ሕገወጥ ገንዘብ በቁጥጥሥር ዋለ
ከህገወጥ የገንዘብ ምንዛሬ ጋር ተያይዞ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሰሞኑን ባከናወነው የክትትል እና ቁጥጥር ተግባር 7ሚሊዮን 243 ሺህ 385 የኢትዮጵያ ብር ይዣለው ብሏል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እንደገለጹት ለህገወጥ የገንዘብ ምንዛሬ የተዘጋጁ 117ሺህ 703 ዶላር፣ 400 ዩሮ፣ 740 ፓውንድ፣ 700 የደቡብ አፍሪካ ራንድ፣ 8ሺህ 50 የአረብ ኤምሬት እና የሌሎች የተለያዩ ሃገራት ገንዘቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አብራርተዋል፡፡ በአጠቃላይ ከህገ-ወጥ የገንዘብ ምንዛሬ እና የብር ኖት ቅያሪ ጋር ተያይዞ ከ15 ሚሊዮን በላይ የኢትዮጵያ ብር በቁጥጥር ስር መዋሉንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜና በልደታ ክፍለ ከተማ ከ35 ሺህ ብር በላይ ነባሩ ባለ ሃምሳ ሀሰተኛ የብር ኖት ከነ ተጠርጣሪው ተይዞ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን … [Read more...] about በአዲስ አበባ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ በላይ ሕገወጥ ገንዘብ በቁጥጥሥር ዋለ
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ400 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ400 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ማፅደቁን የገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል። የገንዘብ ድጋፉ በኢትዮጵያ የከተማ የሴፍቲ ኔት ፕሮጀክትን ለመደገፍ ይውላል ተብሏል። ከድጋፉ ውስጥ 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላሩ ስደተኞች ለሚገኙበት አካባቢና እና በኢትዮጵያ ለሚኖሩ ስደተኞች የስራ እድል ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ነው የገንዘብ ሚነስቴር በትዊተር ገፁ ያስታወቀው። ከዚህ በፊት የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ገንዘብ አገደ፤ ከለከለ እየተባለ በተለያየ ሚዲያ ሲወራ ቆይቷል። ይህ ባንኩ የፈቀደው ገንዘብ ኢትዮጵያ ከባንኩ የምታገኘው ሁሉንም የሚጠቀልል ባይሆንም ባንኩ ከኢትዮጵያ ጋር የገባው ውዝግብ እንደሌለውና ቀሪውንም ገንዘብ በወቅቱ እንደሚፈቅድ ጠቋሚ ነው ተብሏል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ400 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ
ቪኦኤና ጀርመን ድምጽ – የክልሎችን ኅልውና እንደ ህወሓት እየጣሱ ነው
በተለይ ካለፉት ሦስት ወራት ወዲህ የአሜሪካና የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ብሎ የሚጠራውን መቀሌ የመሸገውን የወንበዴዎች ስብስብ (ትህነግን) እያገለገሉ ስለመሆኑ ከሚያቀርቡት ያልተመጣጠነ መረጃ መረዳት አያዳግትም። ለዚህም ይመስላል የተጠቀሱት ሚዲያዎች በተለይም የጀርመን ድምጽ ተቃውሞ እየቀረበበት ይገኛል። የጎልጉል የአዲስ አበባ መረጃ አቀባይ እንዳለው “አለቃና ተቆጣጣሪ ያለ አይመስልም” ሲል በተጠቀሱት ሚዲያዎች ከሚሰሩ ዜና አቅራቢዎች ጋር ቅርብ መሆኑንን የጠቀሰ አስተያየት ሰጪ እንደነገረው ይገልጻል። የአንድ ጋዜጣ ኤዲተር እንደነበር ገልጾ አስተያየት የሰጠው ባለሙያ “ሚዲያዎቹ አንዳንድ ጊዜ የሚያቀርቧቸው፣ በተለይም ከክልል ሪፖርተሮቻቸው የሚተላለፉት መረጃዎች ያስደነግጡኛል። ሁሉም እንዳሻቸው ሪፖርት የሚያቀርቡና የኤዲተሮች ሚና የሚታይባቸው … [Read more...] about ቪኦኤና ጀርመን ድምጽ – የክልሎችን ኅልውና እንደ ህወሓት እየጣሱ ነው