
ከህገወጥ የገንዘብ ምንዛሬ ጋር ተያይዞ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሰሞኑን ባከናወነው የክትትል እና ቁጥጥር ተግባር 7ሚሊዮን 243 ሺህ 385 የኢትዮጵያ ብር ይዣለው ብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እንደገለጹት ለህገወጥ የገንዘብ ምንዛሬ የተዘጋጁ 117ሺህ 703 ዶላር፣ 400 ዩሮ፣ 740 ፓውንድ፣ 700 የደቡብ አፍሪካ ራንድ፣ 8ሺህ 50 የአረብ ኤምሬት እና የሌሎች የተለያዩ ሃገራት ገንዘቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አብራርተዋል፡፡
በአጠቃላይ ከህገ-ወጥ የገንዘብ ምንዛሬ እና የብር ኖት ቅያሪ ጋር ተያይዞ ከ15 ሚሊዮን በላይ የኢትዮጵያ ብር በቁጥጥር ስር መዋሉንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜና በልደታ ክፍለ ከተማ ከ35 ሺህ ብር በላይ ነባሩ ባለ ሃምሳ ሀሰተኛ የብር ኖት ከነ ተጠርጣሪው ተይዞ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጿል፡፡
የአዲስ አበባ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ከጥርጣሬ በመነሳት በአንድ ግለሰብ ላይ ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ በእጅ ቦርሳው ውስጥ 35 ሺህ 50 የቀድሞውን ባለ ሃምሳ ሀሰተኛ የብር ኖት ከአንድ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ቲተር ጋር ከነተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር አውለዋል ብሏል ኮሚሽኑ፡፡
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply