የትግራይ ህዝብ በአሸባሪው ህወሀት ቡድን የተጋረጠበትን የመጥፋት አደጋ መታደግ አላማውን ያደረገ ንቅናቄ ተመሰረተ። ንቅናቄው "ራዕይ የተጋሩ ኢትዮጵያዊያን ሀገር አቀፍ ህዝባዊ ንቅናቄ" የሚል ስያሜ እንዳለው ተገልጿል። ንቅናቄው በትግራይ ክልል ተወላጆች የተመሰረተ ሲሆን ለጥቂት የህወሓት አሸባሪ ቡድን ተብሎ የትግራይን ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያውያን ጋር እንዲለያይ ለማድረግ እየተሰራ ያለውን ስራ እንደሚቃወም በንቅናቄው ይፋዊ ምስረታ መግለጫ ላይ ተጠቅሷል። የህወሓት የሽብር ቡድን ከጥንት ጀምሮ ትግራይን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል እቅድ እንዳለው በማኒፌስቶው ጭምር ያስቀመጠ መሆኑን ያስታወሱት መግለጫውን የሰጡት የክልሉ ተወላጆች ይህ እንዲሆን መፍቀድ በትግራይ ህዝብ ላይ ክህደት መፈጸም ነው ብለዋል። በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን አይደለንም የሚሉ ዜጎች … [Read more...] about ትግራይን ከትህነግ ለመታደግ አዲስ ንቅናቄ ተመሠረተ
News
ዜና
በጋምቤላና ቤንሻንጉል የትህነግ ተላላኪዎች እርምጃ ተወሰደባቸው
በጋምቤላ ከተማ በአሸባሪዎቹ ህወሃት እና ሸኔ ተላላኪነት የተጠረጠሩ ሶስት ግለሰቦችን ከጦር መሳሪያና ሌሎች ቁሳቀሶች ጋር በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የክልሉ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ቱት ኮር ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በቁጥጥር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል ሁለቱ የቀድሞውን የሀገር መከላከያ የደንብ ልብስና ጫማ እንዲሁም የሕክምናና ሌሎች ቁሳቁስ ይዘው ከጋምቤላ ከተማ ወደ ጫካ ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸው ነው። ቀሪው ተጠርጣሪ ደግሞ ከህዝብ በደረሰ ጥቆማ በቤቱ በተደረገ ፍተሻ አንድ ዘመናዊ የጦር ሜዳ መነጽርና አንድ ሽጉጥ ተገኝቶበት እንደሆነ አመልክተዋል። ተጠርጣሪው ካሁን በፊትም ከአሸባሪው ህወሃት ጋር ግንኙነት እንዳለው ተጠርጥሮ እንደነበር አስታውሰዋል። በተጠርጣሪዎቹ ላይ እየተደረገ ያለው ተጨማሪ ምርመራ ሲጠናቀቅ ጉዳያቸው ወደ … [Read more...] about በጋምቤላና ቤንሻንጉል የትህነግ ተላላኪዎች እርምጃ ተወሰደባቸው
የመሬትና መሬት ነክ አገልግሎቶች ላልተወሰነ ጊዜ ታገደ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ከአርብ ነሐሴ 7 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለመሬት አስተዳደር ተቋማት፣ ለመሠረተ ልማት ቅንጅት እና ግንባታ ፈቃድ ባለስልጣን እንዲሁም ለ11ዱም ክፍለ ከተሞች ባስተላለፈው ሰርኩላር፣ የመሬት እና መሬት ነክ አገልግሎቶች ላልተወሰነ ጊዜ ሙሉ በሙሉ እንዳይሰጡ ውሳኔ አስተላልፏል። ካቢኔው ዕግዱን ያስተላለፈው በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ትኩረታቸውን በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲያደርጉ ለማስቻል ሲሆን አንዳንድ ስግብግብ ግለሰቦች ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታውን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም በአቋራጭ ለመክበር በመሬትና መሬት ነክ አገልግሎቶች ላይ ትኩረት በማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን የከተማ አስተዳደሩ በመገንዘቡም ጭምር ነው ተብሏል። በዚህም ምክንያት ማንኛውም የመሬትና መሬት ነክ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ የታገደ ሲሆን ስድስቱም … [Read more...] about የመሬትና መሬት ነክ አገልግሎቶች ላልተወሰነ ጊዜ ታገደ
“ምዕራቦች በምዕራብ —– የትንታጎች ድል”
ሽብርተኛው የህወሀት ሽብርተኛ ቡድን አገራችንን ለመበታተንና ህዝባችንን አንገት ለማስደፋት የከፈተብንን ጦርነት ለመመከት በማይፀብሪ ግንባር የተሰማሩት የምዕራብ ዕዝ ፣ የአማራ ልዩ ሀይል ፣ ህዝባዊ ሚሊሻ ፣ ፋኖ እና የክተት ጥሪውን ተቀብለው የተሰለፉ ሀይሎች አንፀባራቂ ጀግንነት በመፈፀም ላይ ይገኛሉ። ጁንታው ባለፉት ቀናት የሰነዘረውን ማጥቃት በመመከትና ወደ መልሶ ማጥቃት በመሸጋገር በተወሰደው እርምጃ 222 የጠላት ሀይል ተደምስሷል። 01 ዲሽቃ፣ 04 መትረየስ፣ 01 ስናይፐር፣ 04 ተተካይ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 31 ኋላቀር መሳሪያ፣ 25 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 4 ሺ የብሬን ጥይት፣ 3ሺ800 የብሬን ጥይት፣ 100 የዲሽቃ ጥይት በመማረክ በጠላት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ችሏል። የምዕራብ ትንታጎቹ በግንባሩ ከተሰማራው ሀይል ጋር በመሆን … [Read more...] about “ምዕራቦች በምዕራብ —– የትንታጎች ድል”
የ”ከሃዲው” ዳዊት የሌብነት መረጃ
ባለፈው ሳምንት "ከሃዲው ዳዊት ወልደጊዮርጊስን" አስመልክቶ "ዳዊት ወልደጊዮርጊስ – የጸረ ኢትዮጵያዊነት መገለጫ" በሚል እርዕስ ዜና ማቅረባችን ይታወሳል። በዜናው ግንባር የተጠቀሰው ሳይጀመር በከሸፈው "የሽግግር መንግሥት" ማመልከቻ ጉዳይ ነበር። ያተምነውን ዜና ተከትሎ አቶ ለማ መገርሳ "ተውኝ። ልኑርበት" ሲሉ ስለጉዳዩ ምንም እንደማያውቁ በይፋ መናገራቸው፣ ፕሮፌሰር ተዘራ ዳዊት የሤራው ስብስብ አገር ለመርዳት መስሏቸው ከገቡ በኋላ ሲያዩት ሃያ ሰባት ዓመታት ኢትዮጵያን ሲዘርፍና ሲያደማ የኖረውን ትህነግን ወደ ስልጣን ለመመለስ እንደሆነ ሲረዱ ራሳቸውን ማግለላቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ ራሱ አስተባባሪውም "የለሁበትም" ሲል ዳግም ክህደቱን አሳይቷል። በዚህ ዜና ላይ ዳዊት ከሃዲና ዘራፊ መሆኑን ለማሳየት ከረሃብ ሰለባዎች ጉሮሮ መንትፎ አገር ስለመክዳቱ መግለጻችን ከተራ … [Read more...] about የ”ከሃዲው” ዳዊት የሌብነት መረጃ
የፎቶ ሌብነትና የአምነስቲ ቅሌት
አምንስቲ ኢንተርናሽናል ለምርጫ ያነሳሁትን ፎቶ ወስዶ የተጠቀመበትን መንገድ እንዲያስተካክል የተቻለውን ጥረት አድርጎ የማይፈታ ከሆነ ጉዳዩን በተመለከተ ተቋሙን ለመክሰስ እገደዳለሁ ሲል የፎቶግራፍ ጋዜጠኛ አማኑኤል ስለሺ አስታወቀ። ጋዜጠኛ አማኑኤል በጉዳዩ ዙሪያ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገረው፤ አምንስቲ ኢንትርናሽናልን ለማነጋገር ጥረት እያደረገ ነው። "በስልክና በኢ-ሜይል ለማግኝት ጥረት እያረግን ቢሆንም እስካሁን ምንም ምላሽ አልሰጡንም። አሁን 22 ሰዓታት አልፎታል። በርካታ አለም አቀፍ ሚዲያዎችና ተቋማት ይህንን የተቀናበረ ምስል ተቀባብለውታል። ለራሳቸው ዓላማ የሚያውሉት እንኳን ቢሆን መቀየር የተከለከለ ነው" ሲል ተናግሯል። አምነስቲ ለመረጃው የተጠቀመውን ፎቶ ግራፍ በተመለከተ በውይይት ለመፍታት ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ … [Read more...] about የፎቶ ሌብነትና የአምነስቲ ቅሌት
በአዲስ አበባ 325 የትህነግ አሸባሪዎች ከነመሣሪያቸው ተይዘዋል
የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በጥናት ላይ በመመስረት እና ከህዝብ የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ በከተማችን በስጋትነት በተለዩ የተለያዩ ንግድ ቤቶች እና ድርጅቶች ላይ ባደረገው ብርበራ እና ፍተሻ ልዩ ልዩ የጦር መሳሪዎችን፣ ሰነዶችን እና የፀጥታ አካላት የደንብ አልባሳትን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ። መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር በህወሃት ጁንታ ቡድን ላይ እርምጃ መውሰዱን ተከትሎ ህግ የማስከበር ዘመቻው በድል ተጠናቆ የሀገር መከላከያ ሰራዊት መቀሌን ጨምሮ መላው ትግራይን መቆጣጠሩ ይታወቃል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ሐምሌ 11 ቀን 2013 ዓ/ም በሰጡት መግለጫ እንዳብራሩት በዚህ ሀገርን የማዳን እና ትግራይን የመታደግ ዘመቻ አብዛኞቹ የጁንታው አመራሮች ሲማረኩ፣ የተወሰኑት ደግሞ ተደምስሰዋል። ወቅቱ … [Read more...] about በአዲስ አበባ 325 የትህነግ አሸባሪዎች ከነመሣሪያቸው ተይዘዋል
“አደንዛዥ ዕጽ የሚሰጧቸው በበርሜል ሻይ አፍልተው ነው”
“አደንዛዥ ዕጽ የሚሰጧቸው በበርሜል ሻይ አፍልተው በመቀላቀል ነው” አሸባሪው ትህነግ (የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር) ዜጎችን ወደ ውትድርና ተመልምለው ለውጊያ የሚያደርሰው በሁለት መንገድ ነው፤ አንዱ ምንም የጦር ዕውቀትና ልምምድ ሳይኖራቸው በግድ ከሽፍታው ቡድን ጋር እንዲቀላቀሉ የተደረጉ ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ አደንዛዠ ዕፅ አፍልተው ነው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው ትህነግ ህጻናት ልጆችን ለጦርነት እየመለመለ እንደሚሰማራ በማስረጃ ተረጋግጦበታል። ልጆቹ በተለይ ለዚህ ግዳጅ እንዲሰማሩ የሚደረግበትን አካሄድ በየኔታ ትዩብ ላይ የተናገረው በቅርቡ በምርጫ የተወዳደረው ማኅበራዊ አንቂ ብሩክ አበጋዝ ነው። ብሩክ እንደሚለው ትህነግ ልጆቹን ከሰበሰበ በኋላ የጠጡት ምን እንደሆነ በማያውቁበት ሁኔታ እንደ መደበኛ የሚጠጣ ነገር ሻይ … [Read more...] about “አደንዛዥ ዕጽ የሚሰጧቸው በበርሜል ሻይ አፍልተው ነው”
ከ 170 በላይ ሴት የጁንታው አባላት በራሱ የጁንታው ታጣቂዎች ተደፍረዋል
በማይካድራ ንጹሃንን ጨፍጭፎ የሸሸው የአሸባሪው የህወሓት ወንጀለኛ ታጣቂ ቡድን በሱዳን መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ሴቶችን መድፈሩን በመከላከያ ሰራዊት የተማረኩት የህክምና ባለሙያና ወታደራዊ አመራር የሆኑት ሻምበል ተክለወይኒ ታረቀ ማጋለጣቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል። በሱዳን የስደተኛ ጣቢያ ውስጥ ከሚገኙ ከ170 በላይ የሚሆኑት የጁንታው አባላት ሴቶች ላልተፈለገ እርግዝናና ለአባላዘር በሽታዎች መጋለጣቸውንም ምረኮኛው ገልጸዋል። ወንጀል ፈፅመው ወደ ሱዳን የሸሹ የትህነግ ታጣቂዎች በስደተኞቹ ላይ ወሲባዊ ጥቃት እንደሚፈፀሙና በዚህም ያልተፈለገ እርግዝናና የአባላዘር በሽታዎች መስፋፋታቸውን ሲታዘቡ መቆየታቸውን ገልፀዋል። ተክለወይኒ ታረቀ ሻምበል ተክለወይኒ ታረቀ ትውልዳቸውና ዕድገታቸው በሰሜን ምስራቅ ትግራይ ታህታይ አዲያቦ በባድመ አካባቢ ሲሆን ከሰራዊቱ … [Read more...] about ከ 170 በላይ ሴት የጁንታው አባላት በራሱ የጁንታው ታጣቂዎች ተደፍረዋል
በአፍራሽ ሥራ የተጠመዱ የረድኤት ድርጅቶች ሊባረሩ ይችላሉ
የዕርዳታ አቅራቢዎች ከኢትዮጵያ ኢትዮጵያ በአፍራሽ ስራ ላይ ተሰማርተዋል ያለቻቸውን አንዳንድ የእርዳታ አቅራቢዎችን ከሀገር ልታባርር እንደምትችል አስጠነቀቀች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥረው ነበር። አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፥ "አንዳንድ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪዎች በሌሎች ሀገራት እንደተለመደው በኢትዮጵያም ከዚህ በፊት እንደታየው ከእርዳታ እህልና ከእርዳታ አቅርቦት ጋር በማያያዝ ሌላኛውን ወገን የማስታጠቅ ፣ ትግሉ፣ እንቅስቃሴው እንዳይቆም፣ ቀውሱ እንዳይበርድ ለማድረግ የሚያስችል አፍራሽ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል" ብለዋል። አክለውም፥ በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ባለፉት 8 ወራት ይህ ሌላኛውን ወገን ለማስታጠቅ የሚደረገው ሙከራ እንዳጋጠመ ፤ ይህ ጉዳይ መልክ መያዝ እንዳለበት መንግስት ሲያሳስብ … [Read more...] about በአፍራሽ ሥራ የተጠመዱ የረድኤት ድርጅቶች ሊባረሩ ይችላሉ










