አሸባሪው የትህነግ ቡድን በኃይል በወረራቸው አካባቢዎች ላይ በተሰወሰደ ወታደራዊ እርምጃ ታላላቅ ጀብዱዎች መፈጸማቸውን የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ገለፁ፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓታት በወልድያና አካባቢው፣ ጋይትና አካባቢው፣ ዛሬማና አካባቢው፣ ሰቆጣና አካባቢው፣ ጋሸናና አካባቢው በትህነግ የሽብር ቡድን ላይ በተወሰደ ወታደራዊ እርምጃ ታላላቅ ጀብዱዎች መፈጸማቸውን ተናግረዋል፡፡ በዚህም የሽብር ቡድኑ የደረሰበት ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ከባድ መሆኑንም ነው አቶ ሙሉነህ የገለፁት፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ የማህበረሰብ አንቂዎች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በማህበራዊ ተስስር ገፆች የትህነግ የሽብር ቡድንን ለመደምሰስ የሚደረገውን ጥረት የሚያደናቅፉ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲታቀቡ አቶ ግዛቸው … [Read more...] about ባለፉት 24 ሰዓታት የትህነግ የሽብር ቡድን ላይ በተወሰደ እርምጃ ጀብዱ ተፈጽሟል፡- የአማራ ክልል
News
ዜና
በክምር ድንጋይ የተሠራ ጀብድ
በክምር ድንጋይ አንድ የአማራ ጀግና 11 የአሸባሪው ትህነግ ታጣቂዎችን ደመሰሰ። የአሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን ታጣቂዎች በክምር ድንጋይ ከተማ ወደ አንድ ግለሰብ ቤት በመሄድ ለማጥቃትና ለመዝረፍ ተዘጋጁ። ታጣቂዎች ግለሰቡ ቤት ደረሱ። ይህንን ቀድሞ የተረዳው ግለሰብም በጥበብና በብልሃት የመጡትን የአሸባሪውን ቡድን ታጣቂዎች አዘናጋቸው። ሌላ ኃይል አብሯቸው እንደሌለ ወደ ውጪ ወጣ በማለት ካረጋገጠ በኋላ ወደ ጓዳው በመግባት ተቀባብሎ የነበረውን መሣሪያ ይዞ በመውጣት እርምጃ ወስዶባቸዋል። ሊያጠቁትና ሊዘርፉት እንደመጡ የተረዳው ይህ ግለሰብ ያለውን መሣሪያ በመጠቀም በቤቱ የተሰበሰቡትን 11 የአሸባሪውን ትህነግ ታጣቂዎች እንዳልሆኑ በማድረግ ጀግንነቱን አሳይቷል። አሁን ላይም ይህ ጀግና ቀሪ የአሸባሪውን ቡድን አባላትን እያሳደደ ይገኛል። ጠላትን አይቀጡ … [Read more...] about በክምር ድንጋይ የተሠራ ጀብድ
የሁርሶ ሠልጣኞች በብቃት እየተዘጋጁ ነው
"ሀገርን ለማዳን እዘምታለሁ የትም መቼም በምንም" በሚል መሪ ቃል ፀረ ሰላም ሀይሎችን ለመፋለም ቆርጠው የተነሱ የቁርጥ ቀን ልጆች በሀገሪቷ በሚገኙ የውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶች በመግባት ስልጠናቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡ የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ከዚህ ቀደም በርካታ የሰራዊት አባላትን በሁለት ዙሮች አሰልጥኖ ያስመረቀ ሲሆን÷ በአሁኑ ጊዜም የ3ኛ ዙር ሰልጣኞችን በማሰልጠን ላይ ይገኛል፡፡ አሰልጣኝ የ22ኛ ሻለቃ ዘመቻ ሀላፊ መቶ አለቃ ዲኔ መሀመድ የዚህ ዙር ሰልጣኞች ከሁለቱ ዙር ሰልጣኞች ለየት የሚያደርገው ሀገርን ለማፈራረስ የተነሱት የሀገር ሀዲዎች የህወሓት እና የሸኔ የሽብር ቡድኖችን ለመፋለምና ሀገርን ከመፈራረስ ታድጎ አንድነቷን ለማስቀጠል ለሀገሬ እዘምታለሁ በማለት ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለው ወደ ስልጠናው የተካተቱ መሆናቸው ነው … [Read more...] about የሁርሶ ሠልጣኞች በብቃት እየተዘጋጁ ነው
ሀብትና የገቢ ምንጫቸውን ያላስመዘገቡ በህግ ሊጠየቁ ነው
ሀብትና የገቢ ምንጫቸውን ለማስመዝገብ ፈቃደኛ ያልሆኑ 62 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ሰራተኞች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በኮሚሽኑ የፀረ-ሙስና ህግ ምክር፣ ትግበራና ልምድ ቅመራ ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ጋሻው እንደገለፁት ሀብትና የገቢ ምንጫቸውን ለማስመዝገብ ፈቃደኛ ያልሆኑት 16 የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የኒቨርሲቲና 46 የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች ናቸው፡፡ ማንኛውም የመንግስት ተሿሚ፣ የህዝብ ተመራጭ እና የመንግስት መስሪያ ቤቶችና የልማት ድርቶች እንዲሁም የህዝባዊ ድርጅት ሰራተኞች የቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ ሀብትና የገቢ ምንጫቸውን ማስመዝገብ እንዳለባቸው ቢደነገግም ህጉን የሚተላለፉ በመኖራቸው ተጠያቂ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ዳይሬክተሩ … [Read more...] about ሀብትና የገቢ ምንጫቸውን ያላስመዘገቡ በህግ ሊጠየቁ ነው
ቢያንስ 1564 የተጨፈጨፉበት የማይካድራ ግፍ
የምዕራባውያን ሚዲያዎች በማይካድራ የተፈፀመውን የዘር ጭፍጨፋ አስመልክቶ እውነቱን መዘገብ እንደሚገባቸው ጋዜጠኛ ጄፍ ፒርሰን ተናገረ https://www.youtube.com/watch?v=q7mjD3_ucUw … [Read more...] about ቢያንስ 1564 የተጨፈጨፉበት የማይካድራ ግፍ
አሸባሪዎቹ ሸኔ እና ህወሓት መደምሰስ አለባቸው፡- ዶ/ር ዓለሙ
በወሎ ግንባር የተገኙት በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ አሸባሪዎቹ ሸኔ እና ህወሓት ለኢትዮጵያ የማይጠቅሙ በመሆናቸው መደምሰስ አለባቸው ብለዋል። የወያኔ እና ሸኔ ጥምረት ለኦሮሞና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ነው ያሉት ዶ/ር ዓለሙ ስሜ ትህነግም ሸኔን በአንድ ላይ መደምሰስ አለባቸውም ነው ያሉት። የሸኔና የህወሓት ጋብቻ አዲስ ሳይሆን ህወሓት መንግሥት ሆኖም ሳለ ኦሮሞን ለማተራመስ ሲፈልግ ሸኔን ይመሩት እንደነበር ነው ያስታወሱት። አሸባሪው ህወሓት በግንባር ጀግንነት እንደሌለው የገለጹት ዶክተር ዓለሙ ለሚያሠራጨው የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ጆሮ ሳይሰጥ ህብረተሰቡ እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል። አሸባሪው ህወሓት ወጣቶችን በሀሽሽ እያደነዘዘ እየላከ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ዓለሙ ስሜ ብዙ የአሸባሪው … [Read more...] about አሸባሪዎቹ ሸኔ እና ህወሓት መደምሰስ አለባቸው፡- ዶ/ር ዓለሙ
ሕገ-ወጥ የዶላር መንዛሪዎች ተያዙ፤ ዳያስፖራው እንዳይተባበር ጥሪ ቀረበ
በሀገራችን ላይ የተለያዩ ሴራዎችን ሲያካሂድ የቆየው የአሸባሪው የህወሃት ጁንታ ቡድንና ተላላኪዎቹ ፊት ለፊት ከሚያካሂዱት ሀገር የማፍረስ ሴራ ጎን ለጎን በሀገሪቱ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት እንዲፈጠርና ህዝብ በመንግስት ላይ እንዲማረር የተቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ መሆናቸው ተደርሶበታል። በዚህ መሰረት የሽብር ቡድኑ ስልጣን ላይ በነበረባቸው አመታት በዘረጋቸው ኔትዎርኮችና ቅጥረኞች አማካኝነት ከአዲስ አበባ ቶጎ ውጫሌን፣ ሞያሌን፣ መተማንና ሌሎች የመውጫ በሮችን በመጠቀም ኮንትሮባንድ ዝውውር ላይ በመሳተፍና ዶላርን በጥቁር ገበያ እየገዛ የዶላር እጥረት እንዲከሰት ከማድረግ ባሻገር በርካታ የጥፋት ተግባራትን ሲያካሄድ የቆየ መሆኑን ቀደም ሲል በህገ-ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው የተገኙ ስድስት ድርጅቶች ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ስለመሆኑ ባስተላለፍነው መረጃ ተደራሽ … [Read more...] about ሕገ-ወጥ የዶላር መንዛሪዎች ተያዙ፤ ዳያስፖራው እንዳይተባበር ጥሪ ቀረበ
የማይጠብሪው ድል
የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል የጸጥታ ኀይል በማይጠብሪ ግንባር ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ መሆኑን የ54ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል የሺበር አዳነ ተናገሩ። በማይጠብሪ ግንባር ለዳግም ወረራ የተነሳው አሸባሪውና ተስፋፊው የትህነግ ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ በአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ እየተደመሰሰ መሆኑን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የጋዜጠኞች ቡድን በግንባር ተገኝቶ ተመልክቷል። በማይጠብሪ ግንባር ያነጋገርናቸው የ54ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል የሺበር አዳነ እንደገለጹት ሽብርተኛው ትህነግ ከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ ገብቷል። የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ጠላትን ለማሸነፍ ሰፊ ቅድመ ዝግጅት አድርጎ መግባቱ እየተመዘገበ ላለው ድል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ኮሎኔል የሺበር አስታውቀዋል። ኮሎኔሉ ሽብርተኛው ትህነግ ከዓመታት በፊት የቀየሰውን የጦርነት … [Read more...] about የማይጠብሪው ድል
በአምቦ ከተማ ጥይቶችን በአምቡላንስ ሲያጓጉዙ የተገኙ ተያዙ
በአምቦ ከተማ 1 ሺህ 377 ተተኳሽ ጥይቶች በህገ ወጥ መንገድ በተሽከርካሪ ጭነው ሲያጓጉዙ የተገኙ አራት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። ግለሰቦቹ ጥይቶቹን በመንግስት አምቡላንስ ተሽከርካሪ ጭነው ሲያጓጉዙ እንደተገኙ የከተማዋ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሲሳይ ሂርጳ ገልጸዋል። ከከተማዋ ወጣ ብሎ በሚገኘው አዋሮ ቆራ አካባቢ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ትናንት ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ተኩል አካባቢ ነው ግለሰቦቹን ከነጥይቶቹ መቆጣጠር የተቻለው ብለዋል። ኮማንደር ሲሳይ እንዳመለከቱት፤ ግለሰቦቹ ጥይቶቹን በሴቶች "ታይት" አልባሳት ጠቅልለው በማዳበሪያ ውስጥ መድሃኒት አስመስለው በመጫን ከቡራዩ ከተማ ወደ አምቦ ለማሳለፍ ሲሞክሩ ነው የተደረሰባቸው። በዚህም አሽከርካሪው፣ ፋርማሲስት እና ሁለት የጥይቱ ተቀባዮች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳዩ እየተጣራ … [Read more...] about በአምቦ ከተማ ጥይቶችን በአምቡላንስ ሲያጓጉዙ የተገኙ ተያዙ
ዘመቻ: “እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ – #Handsoffethiopia”
ባለፉት 24 ሰዓታት “እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ - #Handsoffethiopia” በሚል መሪ ቃል በተካሄደ የትዊተር ዓለም አቀፍ ዘመቻ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች የነቃ ተሳትፎ ማድረጋቸው ተገለፀ። 100 ሺህ ገደማ የትዊተር መልዕክት በተሰራጨበት ዘመቻ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እንዲከበር የሚጠይቁ እና አሸባሪው ህወሓት አገር ለማፍረስ እየሰራ ያለውን ሴራና ግፍ የሚያወግዙ መልዕክቶች ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ እና መገናኛ ብዙሃን ጭምር ተላልፈዋል። በትዊተር ዘመቻው በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት እየተንቀሳቀሱ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የሚጠይቀው መልዕክት ዐቢይ አጀንዳ ነበር። የትዊተር ዘማቾቹ በተለይም ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡትን የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፊልትማን እየጠቀሱ፣ … [Read more...] about ዘመቻ: “እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ – #Handsoffethiopia”










