• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሕገ-ወጥ የዶላር መንዛሪዎች ተያዙ፤ ዳያስፖራው እንዳይተባበር ጥሪ ቀረበ

August 19, 2021 12:50 am by Editor Leave a Comment

በሀገራችን ላይ የተለያዩ ሴራዎችን ሲያካሂድ የቆየው የአሸባሪው የህወሃት ጁንታ ቡድንና ተላላኪዎቹ ፊት ለፊት ከሚያካሂዱት ሀገር የማፍረስ ሴራ ጎን ለጎን በሀገሪቱ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት እንዲፈጠርና ህዝብ በመንግስት ላይ እንዲማረር የተቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ መሆናቸው ተደርሶበታል።

በዚህ መሰረት የሽብር ቡድኑ ስልጣን ላይ በነበረባቸው አመታት በዘረጋቸው ኔትዎርኮችና ቅጥረኞች አማካኝነት ከአዲስ አበባ ቶጎ ውጫሌን፣ ሞያሌን፣ መተማንና ሌሎች የመውጫ በሮችን በመጠቀም ኮንትሮባንድ ዝውውር ላይ በመሳተፍና ዶላርን በጥቁር ገበያ እየገዛ የዶላር እጥረት እንዲከሰት ከማድረግ ባሻገር በርካታ የጥፋት ተግባራትን ሲያካሄድ የቆየ መሆኑን ቀደም ሲል በህገ-ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው የተገኙ ስድስት ድርጅቶች ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ስለመሆኑ ባስተላለፍነው መረጃ ተደራሽ ማድረጋችን ይታወሳል።

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል ጋር በአዲስ አበባና በአንዳንድ የክልል ከተሞች ባካሄደው የተቀናጀ ኦፕሬሽን ለሽብር ቡድኑ የኢኮኖሚ ምንጭ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩ 117 የንግድ ድርጅቶች እና መኖሪያ ቤቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ የአሸባሪው ቡድን የፋይናንስ ምንጭ እንዲደርቅ የሚያደርጉ ተግባራትን አከናውኗል።

ውድ በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፡- የአሸባሪው ቡድን ከፍተኛ የገቢ ወይም የፋይናንስ ምንጭ በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት የዘረጋቸውን ኔትዎርኮች በመጠቀም ዶላርን በጥቁር ገበያ በውድ ዋጋ መሰብሰብ እና የሃዋላ አገልግሎትን መጠቀም እንደሆነና ከዚህ በሚያጋብሰው ገቢም የጦር መሳሪያ ግዥን በመፈፀም ለጥፋት ተልዕኮው እንደሚጠቀምበት ፌዴራል ፖሊስና የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል በሀገር ውስጥና በውጭ ሃገርም ባካሄዱት ረጅም ጊዜ የፈጀ ጥናትና በተደረገ ምርመራና ክትትል ደርሰውበታል።

በጥናቱም ኔትዎርኮቹን የመለየት ስራ የተከናወነ ሲሆን በኔትዎርኮቹ ውስጥም፡-

  1. አርዓያ (የዞማ የውበት ሳሎን ባለቤት) አሜሪካ የሚኖር
  2. ሳሙኤል (ሳሚ ዶላር) አሜሪካ የሚኖር
  3. ጣዕመ መርከብ አሜሪካ የሚኖር
  4. ሄኖክ (ዲሲ)- አሜሪካ የሚኖር
  5. ሃብቶም ዶላር (ፈረንሳይ የሚኖር)
  6. ኤሊያስ (ዱባይ የሚኖር)

የተባሉት ግለሰቦች የሚገኙበት መሆኑ ተረጋግጧል። እነዚህ ግለሰቦች በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚልኩትን ዶላር አየር በአየር ግብይት በመፈፀም እንዲሁም ዶላሩን እዚያው ውጪ እንዲቀር በማድረግ ለሽብር ቡድኑ ድጋፍ የፋይናንስና የሎጀስቲክ ምንጭ በመሆን እያገለገሉ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባችኋል።
በህገ-ወጥ መንገድ ዶላርን ከደቡብ አፍሪካ ወደ ኢትዮጵያ እየተላላኩ ሀገራችን ማግኘት የሚገባትን የውጭ ምንዛሬ እንድታጣ በማድረግ ረገድ፡-

  1. መንግስቱ ወርቁ (እስራኤል፣ ቴል አቪቭ የሚኖር)
  2. አቪ ፈጠነ (እስራኤል የሚኖር )
  3. አስቴር ባልትና (ፕሪቶሪያ የምትኖር )
  4. እቴነሽ (ፕሬቶሪያ የምትኖር)
  5. ዮናታን ትሬዲንግ ጂፒ (ጆሃንስበርግ የሚኖር)
  6. ሄኖክ ባልትና (ጆሃንስበርግ የሚኖር)
  7. እሙ (ደርባን የምትኖር)
  8. መሐመድ ሼክ ጀማል እና ፋሚ ሼክ ጀማል (ደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ)
    ግለሰቦችና ድርጅቶች እጃቸው እንዳለበት በምርመራ ስለተረጋገጠ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ብሄራዊ ኢንተርፖል እነዚህን ግለሰቦችና ድርጅቶች ለህግ ለማቅረብ ስም ዝርዝራቸውን ለአለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል) ልኮ በጋራ እየሰራ ይገኛል።

ስለዚህ ውድ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ይህ አሸባሪ ቡድን ለሽብር ድርጊቱ ማስፈፀሚያነት የሚጠቀመውን ገንዘብ የሚያገኘው በዚህ መንገድ መሆኑን በመገንዘብ ከዚህ ፀረ ኢትዮጵያ ቡድን ጋር ባለመተባበር ሀገር ወዳድነታችሁን እንድታስመሰክሩ እንዲሁም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በዚህ ህገ-ወጥ ድርጊት ላይ የተሰማራችሁ ዜጎች ጉዳቱ ለመላው ሀገሪቱ ነውና ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል።

ነሐሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Filed Under: News, Right Column Tagged With: operation dismantle tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule