• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የማይጠብሪው ድል

August 19, 2021 12:35 am by Editor Leave a Comment

የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል የጸጥታ ኀይል በማይጠብሪ ግንባር ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ መሆኑን የ54ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል የሺበር አዳነ ተናገሩ።

በማይጠብሪ ግንባር ለዳግም ወረራ የተነሳው አሸባሪውና ተስፋፊው የትህነግ ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ በአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ እየተደመሰሰ መሆኑን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የጋዜጠኞች ቡድን በግንባር ተገኝቶ ተመልክቷል።

በማይጠብሪ ግንባር ያነጋገርናቸው የ54ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል የሺበር አዳነ እንደገለጹት ሽብርተኛው ትህነግ ከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ ገብቷል። የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ጠላትን ለማሸነፍ ሰፊ ቅድመ ዝግጅት አድርጎ መግባቱ እየተመዘገበ ላለው ድል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ኮሎኔል የሺበር አስታውቀዋል።

ኮሎኔሉ ሽብርተኛው ትህነግ ከዓመታት በፊት የቀየሰውን የጦርነት ስልት እየተከተለ መሆኑን ነው የተናገሩት። ዋና አዛዡ አሸባሪው ቡድን በአሁኑ ወቅት ጦርነቱን በመሣሪያ ሳይሆን በሰው ማዕበል ለመምራት ጥረት እያደረገ ነው፤ አቅሙም እየተዳከመ መጥቷል፤ የትግራይ ወላጆችም ልጆቻቸው የእሳት ራት ከመሆናቸው በፊት ሊታደጓቸው ይገባልም ብለዋል።

እንደ ኮሎኔሉ ገለጻ በመንግሥት የጸጥታ ኃይል ጠንካራ ክንድ የአሸባሪ ቡድኑ አባላት እየተደመሰሱ ነው፤ ሠራዊቱ በቀጣይም ጦርነቱን በድል ለማጠናቀቅ በሚያስችል አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል፤ በአሁኑ ወቅት የጸጥታ ኃይሉ ጠንካራ አደረጃጀት ድል እንዲያስመዘገብ አስችሎታል ብለዋል። ጠላትም በገባበት እንዲቀር እንዳደረገው እና የህልውና ዘመቻው በቅርቡ በአመርቂ ውጤት ይደመደማል ነው ያሉት ኮሎኔሉ።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይል  ጠላትን ለመደምሰስ በሚያደረገው ተጋድሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያልተቋረጠ  ድጋፍ  ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አስረድተዋል። ሠራዊቱ ሰንሰለታማ ተራሮችን ተጋፍቶ እያሸነፈ የመገስገሱ ምስጢርም ሕዝባዊ ደጀን በመኖሩ ነው ብለዋል። ሕዝቡም በቅርቡ ወደ ተረጋጋ ሰላም ይመለሳል ነው ያሉት የ54ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል የሺበር።

ዘጋቢ፦ አዳሙ ሽባባው – ከማይጠብሪ ግንባር

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: operation dismantle tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule