በወሎ ግንባር የተገኙት በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ አሸባሪዎቹ ሸኔ እና ህወሓት ለኢትዮጵያ የማይጠቅሙ በመሆናቸው መደምሰስ አለባቸው ብለዋል።
የወያኔ እና ሸኔ ጥምረት ለኦሮሞና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ነው ያሉት ዶ/ር ዓለሙ ስሜ ትህነግም ሸኔን በአንድ ላይ መደምሰስ አለባቸውም ነው ያሉት።
የሸኔና የህወሓት ጋብቻ አዲስ ሳይሆን ህወሓት መንግሥት ሆኖም ሳለ ኦሮሞን ለማተራመስ ሲፈልግ ሸኔን ይመሩት እንደነበር ነው ያስታወሱት።
አሸባሪው ህወሓት በግንባር ጀግንነት እንደሌለው የገለጹት ዶክተር ዓለሙ ለሚያሠራጨው የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ጆሮ ሳይሰጥ ህብረተሰቡ እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል።
አሸባሪው ህወሓት ወጣቶችን በሀሽሽ እያደነዘዘ እየላከ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ዓለሙ ስሜ ብዙ የአሸባሪው ታጣቂዎች እየተደመሰሱ የተሳካ ግዳጅ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ጦርነቱ በአጭር ጊዜ አልቆ ወደ ሀገር ግንባታ እንደንመለስ እንፈልጋለን ያሉት ዶ/ር ዓለሙ ሕዝቡም ልጆችን እየላከ፣ ስንቅ እያቀበለና እየተዋጋ አስደናቂ ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል።
የሠራዊቱና የሕዝቡ ዝግጅት አሸባሪው ህወሓትን በአጭር ጊዜ ቀብሮ ሀገር ሰላም እንዲሆን የማድረግ አቅም እንዳለው መመልከታቸውንም ገልጸዋል።
ለሀገር ክብር ሲሉ ቤትና ንብረት ጥለው በግንባር ላይ ያሉ ሚሊሻዎችን የልማት ሥራ ሕዝቡ እንዲሠራም ጠይቀዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply